Get Mystery Box with random crypto!

#ሼር_ፖስት! ደብረ ማርቆስ የጳጉሜ ነፀብራቅ፣ የአዲስ ዓመት ማብሰሪያ የሆነውን የእንግጫን በዓል | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

#ሼር_ፖስት! ደብረ ማርቆስ የጳጉሜ ነፀብራቅ፣ የአዲስ ዓመት ማብሰሪያ የሆነውን የእንግጫን በዓል ለማክበር መሠናዶዋን ቀጥላለች፣ እንግዶችም ወደ ከተማዋ እየገቡ ናቸው። በዚህ አጋጣሚ ይህ ተረስቶና ተቋርጦ የነበረን በዓል ለማስተዋወቅ አክቲቪስቶች፣ የመንግሥት ሚዲያዎች ማንኛውም የፌስቡክ ተጠቃሚ ልዩ ትኩረት እንድትሰጡት ለማሳሰብ እወዳለሁ። ሌላው ከካሽሚር የሚሰሩ የሴቶች ልብስና ወንዶች የሚለብሱት በተለምዶ ጎጃም አዘነ የሚባል ልብስ የጎጃም ዐማራን ህዝብ የሚወክል የባህል አልባሳት አይደለም፣ በተለይ የጎጃም ሙዚቃ የምትሰሩ ሰዎች እርምት ልታደርጉ ይገባል። ከሙዚቃው በፊት የማኅበረሰቡን ባህል፣ ወግና ልማድ ልታውቁ ይገባል። የቴዲ አፍሮ "ማር እስከጧፍ" ቪዲዮ ጥሩ ተሞክሮ ነው። በተለይ ጎጃም አዘነ የሚባለው አልባሳት እንዴት እንደተስፋፋ የተሰራውን ደባና ሸፍጥ ወደፊት በማስረጃ የማቀርበው ይሆናል።