Get Mystery Box with random crypto!

-አይበገሬዎችን ማንም ማስቆም አልቻለም። በዋግኽምራ ዞን በ3 አቅጣጫዎች ማለትም በዝቋላ ወረዳ በቅ | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

-አይበገሬዎችን ማንም ማስቆም አልቻለም። በዋግኽምራ ዞን በ3 አቅጣጫዎች ማለትም በዝቋላ ወረዳ በቅዳሚት፣ በሰቆጣ ወረዳ በፀመራና በሀሙሲት አቅጣጫ ህወሓት እንደ ባቢሎን የገነባውን ግንብ እየደረመሱና ጠላትን እየማሩኩ ግስጋሴያቸውን ቀጥለዋል። ጀግኖቻችን ትልልቅ የሚባሉ የሰቆጣ ዙሪያና አበርገሌ ምሽጎች ሰብረዋል። ለምሳሌ ቅዳሚት ቀበሌ እና በዚዝ ግምባር የነበረውን ጠንካራ የህውሓት ምሽግ ተቆጣጥረውታል።

-በሁመራ ግምባር በረከት አካባቢ በከባድ መሳሪያ 2 ከፍተኛ ምሽግ ተሰብሯል። እግረኛ ወታደር ወደ ምሽጉ ተጠግቷል። እንደ ማዕበል እየተመመ የሄደው ሚኒሻና ፋኖ "ለጊዜው መከላከያ በቂ ነው" ተብሎ በአንድ ቦታ ሰፍሮ በተጠንቀቅ እየተጠባበቀ ይገኛል።

- ሌላው በሽሬ ዛላምበሳ ግምባር ግስገሳው ቀጥሏል።

-ከባህርዳር ከተማ አስተዳደር ፀጥታ ምክር ቤት በዚህ ወቅት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪ የሚያደርጉ፣ በዓልንና ወቅታዊ ሁኔታውን በመጠቀም በመሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ላይ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች እርምጃ እወስዳለሁ ብሏል!

-በወልዲያ ከተማ ተረጋግታለች፣ ዛሬ የባንክ አገልግሎትም ጀምሯል፣ የተሰደደው ህዝብም ተመልሶ እየገባ ነው።

-ባጠቃላይ በሁሉም አወደ ውጊያዎች ወደ ፊት እና ስትራቴጅክ ቦታዎች በሙሉ በኛ የተያዙ ናቸው። ህዝቡም ደጀንነቱን አጠናክሮ ቀጥሏል፤ ወደ ግምባር የሚሄደው ህዝብም አሁንም አላቆመም፣ በአራቱም አቅጣጫ ወደፊት እየተመመ ይገኛል። እንበርታ፥ እንናነበብ፥ እንደጋገፍ!