Get Mystery Box with random crypto!

ይህ የአባታችን ጥሪ በየፌስቡኩ፣ በየግሩፑ፣ በየቴሌግራሙ #ሼር_ፖስት እንዲሆን እጠይቃለሁ። መረጃዎ | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

ይህ የአባታችን ጥሪ በየፌስቡኩ፣ በየግሩፑ፣ በየቴሌግራሙ #ሼር_ፖስት እንዲሆን እጠይቃለሁ። መረጃዎችን ማሰራጨትም አንዱ የእገዛ ዘዴ ነው።

ለጽርሐ ጽዮን አንድነት ገዳም ድጋፍ እንዲያቀርቡ የቀረበ የበረከት ጥሪ
=============
እንደሚታወቀው የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ድንባቄ ተራራ ስር ላይ ጽርሐ ጽዮን ቅድስት ማርያም አንድነት ገዳም ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የጠበቀ፣ በስፋቱ እንደ ሀገረ ስብከቱ ብቸኛ የሆነ፣ በርካታ ምዕመናንን ሊያስተናግድ የሚችል እና ለቤተ ክርስቲያኒቱም ሆነ ለሀገራችን በቅርስነት ተመዝግቦ አገልግሎት ሊሰጥ የሚችል ህንፃ ቤተ ክርስቲያን እየተገነባ ይገኛል። ይህ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን እንደሚታወቀው እስከ አሁን የሚሠራው በአብዛኛው በአሜሪካ እና ከኢትዮጵያ ውጭ ባሉ የቤተ ክርስቲያን ልጆች በሚያደርጉት ድጋፍ ነው።

በዚሁ መሠረት የሚሠራው ቤተ ክርስቲያን በጣም ግዙፍ እንደመሆኑ መጠን ሀገረ ስበከቱ ከአስተባባሪ ወጣቶች ጋር በጋራ በመሆን ለሥራው ማስፈጸሚያ የሚሆን በተለያዩ እንቅስቃሴዎች ድጋፍ ማሰባሰብ ግድ ሆኖበታል።

ስለሆነም ለተጠቀሰው ቤተ ክርስቲያን ማስፈጸሚያ የሚሆን ቲሸርቶችን በማሳተም መንፈሳዊ የሕዝብ ጉባኤ እና ሩጫ ስለአዘጋጀ እርስዎ ወይም ድርጅትዎ ቲሽርቱን በመግዛት፣ አስፈላጊ የሆኑትን ማቴርያሎች በማቅረብና ገንዘብ በመደገፍ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000495251997 የልጅነትዎትን ድርሻ እንዲወጡ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ አብርሃም ጥሪ አቅርበዋል።

ታስታውሱ እንደሆነ ገና የዚህ ቤተክርስቲያን መሠረት ሲጀምር መረጃውን ጽፌ ነበር፣ የተወሰነ ሳንቲምም አሰባስበናል፣ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ዛሬ ከዚህ ደርሷል!

ለበለጠ መረጃ
========
ቀሲስ ፋሲል አጥናፉ
0913174483 የገዳሙ ጸሓፊ
ቀሲስ ጥበቡ ክበር
0918022235 የሊቀ ጳጳሱ ልዩ ጸሓፊ.

ስለሚያደርጉት ድጋፍም በእግዚአብሔር ስም ከልብ እናመሰግናለን። የሚሰጥ በልግስና ይስጥ ሮሜ 12፥8

ለሀሳብ ለአስተያየት በዚህ ሊንክ
@Tadeletibebut