Get Mystery Box with random crypto!

#ሼር_ፖስት! -የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ዛሬም ወደግምባር መትመሙን አላቆመም። -'ጃናሞራ ለጠገበ | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

#ሼር_ፖስት! -የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ዛሬም ወደግምባር መትመሙን አላቆመም።

-"ጃናሞራ ለጠገበው ጥይት ለራበው እንጀራ" የተባለለት ከጃሞራም ክተት ብሏል፤ በተመሳሳይ ከጭልጋ የተነሳው ኃይል ወደግንባር ጉዞ ጀምሯል

-የሸዋ ፋኖ ተወርውሮ ወልዲያ ገብቷል።

-የጎጃም ሚኒሻ ወደ ግምባር ከዘመተ ቆይቷል፣ ህዝቡም ደጀንነቱን አጠናክሮ ቀጥሏል።

-ትናንት የነገርኳችሁ የሽሬ ጉዳይ ህወሓት መግለጫ ሰጥቶበታል፤ አንድ ጠንካራ ምሽግ ተሰብሯል፤ የልምምጥ መግለጫ እየሰጡ ያሉት እንደ ካቻምናው ያሰቡት ባለመሆኑና ምቱ ስለከበዳቸው ነው።

-ታጋይ ታደሰ ወረደ (ወዲ ወረደ)." የትግራይ እና ዐማራ ህዝብ ተጎራብቶ መኖሩ ስለማይቀር የተፈጠረው ቀውስ ለማከም ሁሉም ሊሰራ ይገባል፤ ከዚህ በኋላ ግን ሌላ ቁስል መፍጠር ሊያበቃ ይገባል። በመሰረቱ የትግራይ ህዝብ ጠላት የአማራ ህዝብም ጠላት ነው" የሚል መግለጫ ሰጥተዋል።

እውነት ነው. በዐማራና.. በትግራይ ሕዝብ መካከል ልዩነት አለ ከተባለ በቋንቋቻቸው ላይ ያለው ልዩነት ነው። ቋንቋቸውም ቢሆን በሴሜቲክ ቋንቋዎች የሚመደቡ የአንድ ቤተሰብ ልጆች ናቸው። ሁለቱም ሃገራችን በስልጣኔ ማማ በነበረችበት ዘመን በስነ-ህንፃ፣ ስነ-ቅርፅ፣ ስነ-ጥበብ፣ ስነ-ፅሑፍ እና ስነ-መለከት የጋራ ዓሻራ ያረፋባቸው የዓለም ቅርስ ሆነው የተመዘገቡ ቅርሶች ያሏቸው፤ የአኩስም ሥልጣኔ አሻራ ወራሾች፣ የግዕዝ ፊደል ባለቤቶች፣ የግእዝ ስነ-ጽሁፍ ባለሀብቶች፣ የክርስትና እምነት ተከታዮች፣ የተመሳሳይ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ተቋማት ባለቤቶች ብሎም ተመሳሳይ የኑሮ ስልትን የሚከተሉ ሕዝቦች ናቸው።

የዐማራና ትግራይ ህዝብ በባህል፣ በሃይማኖት እና ቋንቋ መተሳሰር ብቻ ሳይሆን ለሀገር የተዋደቁና በአንድ ጉድጓድ የተቀበሩ ናቸው። ብዙሃነታችን በአግባቡ ማስተናገድ ተስኗቸው ከነበሩት የስልጣኔ ከፍታ ቁልቁል ተንደርድረው ሲወርዱ ሆነ በፊዳላዊ የባላባቶች ስርዓተ-ማህበር ሲሰቃዩም ሆነ ሲሸማቀቁ የችግሩ ግፈት ቀማሽ ሁለቱም ህዝቦች ናቸው። በዛን ዘመን በተደራጀና ባልተደራጀ አኳሃን ለውስጥ ገዥዎችና የውጭ ወራሪዎች ሲታገሉ፣ ሲሰውም ይሁን ድል ሲያደርጉ አብረው ታሪክ ሰርተዋል። ባጠቃላይ ተክለጻድቅ መኩሪያ እንዳሉት፣ "ዐማራና ትግሬ በነገድ አንድነት፣ በልማድ፣ በሃይማኖት ከመዋሐዳቸው የተነሳ የመንግሥቱ ዓምድ ሆነው ኖረዋል" (የግራኝ አህመድ ወረራ፣ 15)

ይህን ታሪክ ፈጽሞ መካድና መፋቅ አይቻልም። ነገርግን ይህን የመሰለ የሁለቱን ህዝቦች ለዘመናት የተገነባ አብሮ የመኖር ወርቃማ እሴቶችና ታሪካዊ ዳራ፣ የደም፣ የባህል፣ የታሪክ፣ የቋንቋና ሃይማኖት ትስስር ወደጎን በመተው የዐማራን ህዝብ ነጥሎ በደመኛ፣ በጭቆና፣ በታሪካዊና በስትራቴጂካዊ ጠላትነት ፈርጆ ወደ ትግል የገባው ህወሓት ነው። በደም፣ በአጥንት፣ በጋብቻ የተደባለቀውን፣ ኢትዮጵያዊነትን ከደመ ሥጋው ቀላቅሎና ኮርቶ የሚኖረውን የዐማራና የትግራይ ህዝብ "እኛ" እና "እነሱ"
(Categorization) የሚል ክፍፍል የፈጠረው ህወሓት ነው። ዐማራ በጠላትነት ፈርጆ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል ሰለባ ከመሆን አልፎ፣በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና መሰል እንቅስቃሴዎች ውስጥ የወሣኝነት ቦታ ቀርቶ፣ የተሳትፎ መብት እንዳይኖረው ያደረገው ህወሓት ነው።

ከዚህ በኋላ ህወሓትን ከምድረገፅ እንደ ዳይኖሰር ካልጠፋ በስተቀር የይቅርታ፣የሠላምና የአንድነት ልብ ይኖረዋል ብሎ ማሰብ እባብ ለመድ ብሎ በኪስ እንደመያዝ ይቆጠራል። መግለጫዎችም ሠላም ከመናፈቅ የመነጨ ሳይሆን ከጀርባው ተንኮልና ሴራ ያዘለ ነው።

ዝምብለህ ወጥር ዐማራ!