Get Mystery Box with random crypto!

#ሼር_ፖስት! የወገን ጥምር እስትራቴጂካዊ ቦታ ያዘ እንጂ 'አበርገሌ' ገና አልተያዘም፤ ነገርግን | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

#ሼር_ፖስት! የወገን ጥምር እስትራቴጂካዊ ቦታ ያዘ እንጂ 'አበርገሌ' ገና አልተያዘም፤ ነገርግን የወገን ጦር በከፍተኛ ማጥቃት ወደፊት እየገሠገሠ ይገኛል። በግዳን በኩል በህወሓት የተያዙ አካባቢዎች በወገን እጅ የገቡ አሉ።
በወርቄ በኩልም በተመሳሳይ የወርቄ ጀግኖች ምላሹን እየሰጡት ይገኛሉ።

-በሁመራና ወልቃይት በኩል በ2 ቦታ ነው ጦርነቱ የተጀመረው በበረከትና በሽሬ። በሽሬ ህወሃት ሲገነባው የኖረው አንድ ምሽግ ተሰብሯል። ዝርዝር መረጃው ይቆይ!

-የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ በነቂስ ግልብጥ ብሎ በመውጣቱ "መከላከያ ስላለ በቂ ነው" እየተባለ "ከምድራዊ" ከምትባል ቦታ ላይ ተመለሱ ተብሎ ሲከለከል ነው የዋለው። ይህ ህዝብ ያለ ቅስቀሳ ቁጭት፣ እልህና ወኔ ይዞት ነው መሳሪያውን እየያዘ ለመፋለም የወጣው። ይህ ለሌላው አካባቢ ብዙ ትምህርት የሚሰጥ ነው እንደ ሕዝቡ የመጣውን እንደ ሕዝብ ለመመከት "ሆ!" ብሎ መግጠም ከወልቃይት ትምህርት ሊወሰድ ይገባል። እንደሚታወቀው የወልቃይት ሰው ተኩሶ ኢላማ የሚስት አይደለም፣ እንዲያውም እዛ አካባቢ መሳት ትልቅ የጥይት ብክነትና እንደ ብቃት ማነስ ይቆጠራል። አነጣጥሮ የዥግራ አንገት በጥሶ መጣል እንደ ባህላዊ ጨዋታ ነው፤ ወይንም ተከዜ ወንዝ ዳር ሆነው፤ ተከዜ ወንዝ ውስጥ ያለው አዞ አፉን ሲከፍት በጉሮሮው ውስጥ መክተት የተለመደ ነገር ነው። ወንዱ ብቻ ሳይሆን በሴቱም ይብሳል!

-በነገራችን ላይ ዘገባ የምትሰሩ ሰዎች የአካባቢውን ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ በሚገባ ጠይቃችሁ ቢሆን ይመረጣል። በደፈናው ወልቃይት ወይንም ሰቆጣ የሚል መረጃ ስትሰጡ ያደናግራል። ለምሣሌ በሰሜን ወሎ በኩል ህወሓት ጦርነት የከፈተው በዋግኽምራ ዞን፣ በአበርገሌና ዝቋላ ወረዳ ነው። የዋግኽምራ ዞን ዋና ከተማ ደግሞ "ሰቆጣ" ናት። ይህ ዞን በርካታ ወረዳዎች አሉት ነገር ግን ጦርነቱ እየተደረገባቸው የሚገኙት  አበርገሌና ዝቋላ በዚህ ዞን ስር ናቸው።  በሌላ በኩል በሰሜን ወሎ ራያ ግንባር ወርቄ እና ግዳን እና ሌሎችም ቦታ ጦርነቱ እየተካሔደባቸው ያሉ ናቸው።


-በተመሳሳይ ወልቃይት እጅግ በጣም ሰፊና በርካታ ወረዳዎች ያሉት ነው። ህወሃት ጦርነት የከፈተበት ቦታ "በረከት"፣ ልዩ ቦታው "ሸረሪና" ይባላል፣ ከሁመራ የ20 ኪሜ ርቀት አለው።
ስለዚህ የአካባቢውን ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ ሳያውቁ መረጃ የሚያዛቡ ሰዎች እርምት እንዲያደርጉ ለማሳሰብ እወዳለሁ።

-በዋግ ግንባር የሕወሓትን ወራራ በሚገባ እየመከተ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ጥምር ጦር የዋግ ሕዝብ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ቀጥሏል። በየአካባቢው ያለ ማህበረሰብ ለሰራዊቱ ስንቅ እያዘጋጀ በማቀበል ደጀንነቱን በተግባር እያሳዬ ይገኛል። የወልድያ ህዝብም በተመሳሳይ! እንበረታ፤ እንናበብ!