Get Mystery Box with random crypto!

#ሼር_ፖስት ጥዋት እንደነገኳቸው የሁመራ ወጣት፣ ሚኒሻና ፋኖ በቁጣ ነው ወደግምባር እየሄደ ያለው። | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

#ሼር_ፖስት ጥዋት እንደነገኳቸው የሁመራ ወጣት፣ ሚኒሻና ፋኖ በቁጣ ነው ወደግምባር እየሄደ ያለው። ጥዋት በስልክ ሳነጋግራቸው "በሬሳችን ተረማምደው ካልሆነ ወልቃይት ከዚህ በኋላ ረመጥ ነው፥ ይፋጃል" ነበር ያሉኝ። በወልቃይት ጉዳይ መንግሥትም መግለጫ ሰጥቷል።

-አሁን ከዳንሻ፣ ከሳንጃ እየተመመ ያለው ኃይል ከምታስቡት በላይ ነው። ስትፈልጉ ብትውሉ አንድ መሳሪያ ያልያዘ ጀሌ አታገኙም። ሁሉም ገዝቶ ያስቀመጠውን መሳሪያ ይዞ ለማይቀረው የአርማጌዶን ጦርነት ወደግምባር እየተመመ ነው።

-ሴቶችና ወጣቶች ስንቅ ይዘው ከኋላ እየተከተሉ ናቸው። የዛ አካባቢ መኪናዎች ሰውን በማጓጓዝ ተጠምደዋል። በየሱቁ ውሃ እየተፈለገ በገፍ እየተጫነ ይገኛል።

-በጣም ያስገረመኝን ልንገራችሁ በቦታው የሚገኘው የመከላከያ ኃይል የህዝቡን ወኔና ደም ፍላት አይቶ በመገረም ነው። በህዝብ ብዛት አካባቢው በመጥለቅለቁ የመከላከያ አመራሮች "ይህ ሁሉ ህዝብ ለዚህ ትንሽ ቡድን ምንም ስለማይሰራ እባካችሁ ተመለሱ" እያሉ ልመና ላይ ናቸው። ህዝቡ ግን ወይ ፍንች..."ላለፉት 50 ዓመታት ወያኔን ከኛ በላይ የሚያውቀው የለም፤ ይህን ወሰን አልፎ ቢመጣ አይምረንም። ማይካድራ ላይም አልማረንም። እንዲያውም ከትህነግ የምናወራርደው ሂሳብ አለን። እናተንም ሆነ አካባቢውን ለቀን የትም አንሄድም" ብሎ ንቅንቅ አላለም። አሁንም ወደ ወልቃይት ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ኃይል እየገባ ነው።