Get Mystery Box with random crypto!

#ሼር_ፖስት ህወሓት በሁመራ በኩል ጦርነት ከፍቷል። ከሁመራ....20 ኪሎ ሜትር 'ዝጓላ' ከሚባለው | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

#ሼር_ፖስት ህወሓት በሁመራ በኩል ጦርነት ከፍቷል። ከሁመራ....20 ኪሎ ሜትር "ዝጓላ" ከሚባለው አካባቢ ነው ጦርነት ከፍቶ ያደረው፤ አሁንም ውጊያ እንደቀጠለ ነው። የሁመራ ህዝብም ወደ ቦታው እየተመመ ይገኛል።

-ወልዲያ ከተማ ሠላም ናት። ትናንት እንደነገርኳችሁ ጦርነቱ ከወልዲያ በስተሰሜን አቅጣጫ ጎብዬ፤ ሮቢት እና ተኩለሽ አካባቢ ነበር። መከላከያ፣ ልዩ ኃይል፣ ፋኖና ሚኒሻ በጥምረት ባደረጉት መልሶ ማጥቃት ወደኋላ ተመልሶ አላውሃን በመልቀቅ ወደ ሮቢትና አካባቢው ሸሽቶ ነው የዋለው። ጦርነት እንደመሆኑ መረጃዎች እንደሚለዋወጡ ልብ ይለዋል! አሁን ከባለፉት ቀናት በተሻለ በወልዲያ መረጋጋት አለ። ሸሽተው የነበሩ ነዋሪዎች ወደቀያቸው እየተመለሱ ይገኛሉ።

-ትናትም እንዳልኩት ዛሬም የምደግመው ህዝቤ ሆይ አንድ ሁን፤ እንደ ዘመነ መሳፍንት ተከፋፍለን ታሪካዊ ስህተት እንዳንፈፅም፤ የልጆቻችን ህልም እንዳናጨልም። ዐማራ ካለፈው የታሪክ ስህተቱ መማር አለበት። በ17ኛው መክዘ መጀመሪያ ርስቱን የተነጠቀው፣ ለም መሬቱን ትቶ እንደ ዝንጀሮ የተራራና የቆለኛ ነዋሪ ሆኖ የቀረው ምድሪቱን እያድለቀለቀ የመጣውን ጥፋት በአንድነት ቆሞ መመከት ባለመቻሉ እንደሆነ አባ ባህሪ ነግረውናል።

-ዐፄ ቴዎድሮስ የተሸነፈው በናፒይር በሚመራው የእንግሊዝ ጦር ሳይሆን በራሱ በዐማራው መሳፍንት ክህደትና አለመተባበር ነው። ቴዎድሮስ ሚያዚያ 3፣ 1860 'በአሮጌ" ጦርነት ማግስት ለባድሉ ጀኔራል ናፒየር በጻፈው ደብዳቤ ለሕዝቡም ሆነ ለዓለም የመጨረሻ ቃሉን አሰምቶ አልፏል። ይህ ደብዳቤ አልገዘ ላለው ሕዝቡ የሟች ወቀሳ ነው። ያ እንዲያ የደከመበት የስነሥርዓት ጉዳይ እስመከጨረሻው አልሠምርለት በማለቱ የተሰማውን ቁጭት እንዲል ይገልጻል።

".... ያገሬ ሰው ገብር ሥራት ግባ ብየ ብለው እምቢ ብሎ ተጣለኝ። እናንተ [እንግሊዞችን] ግን በስራት በተገዛ ሰው አቸነፋችሁኝ። እኔን ወደውኝ የተከተሉኝ ሰዎች አንድ እርሳስ ፈርተው ጥለውኝ ሸሹ ብትቃጧቸው ከሮጡ ሰዎች ጋራ አልነበርሁም ጌታነኝ መስሎኝ ባልሰላ መድፍ ሥታገል ዋልኩኝ።..."


ለቴዎድሮስ መሸነፍ ምክንያት የእንግሊዞቹ የጦር መሳሪያ ጥራት አይደለም፤ ህዝቡን ሥርዓት ግባ ብሉት እምቢ አለ፤ የዐማራው መሳፍንት ከመተባበር ይልቅ በቴዎድሮስ ላይ ሸፈተ፤ ከቴዎድሮስ ጎን የነበሩትም ፈርተው ጥለውት ጠፉ። ቴዎድሮስ ወዲህ ዞር ቢል ሰው የለም፤ ያምኗቸው የነበሩት ሁሉ ከድተውታል፤ እንደ ጀብራ መቅደላ አፋፉ ላይ ብቻውን ቆሞ ቀረ፤ በመጨረሻም "ከተወለድሁኝ እስታሁን ወንድ እጄን ጨብጦት አያውቅም" ብሎ ሽጉጡን ጠጣው።

ይህ ያለፈ የታሪካችን አንዱ አካል ነው። ዛሬ ልንማርበት ይገባል፤ በአንድነት እንቁም፤ በሥርዓት እንመራ፤ የሆነ ከተማ ተያዘ፤ አልተያዘ የሚለው ክርክር የዐማራ ከተሞችን ከመወረር አያድናቸውም። ከተሞቻችን የማይያዙት በአንድነት ስንመክት፣ ለመከላከያ፣ ልዩ ኃይሉና ፋኖ ደጀን ስንሆን ብቻ ነው።