Get Mystery Box with random crypto!

አሜሪካና ኢራን ኦሮሚያ በሚባለው ክልል ምዕራብ ወለጋ በዐማራ ተወላጆች ላይ የተፈፀመውን ጭፍጨፋ አ | Tadele Tibebu - ታደለ ጥበቡ

አሜሪካና ኢራን ኦሮሚያ በሚባለው ክልል ምዕራብ ወለጋ በዐማራ ተወላጆች ላይ የተፈፀመውን ጭፍጨፋ አውግዘዋል። የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ሰኢድ ካቲብዛበህ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ለሟች ቤተሰቦች መፅናናትን የተመኘ ሲሆን፣ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት በበኩሉ በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ የዐማራ ማህበረሰብ አባላት በተፈጸመው ግድያ እንዳሳሰበው አስታውቆ፣ በዚህ ዘግናኝ ድርጊት ለተጎዱ፣ በህይወት ለተረፉ እና ዘመዶቻቸውን ላጡ ሁሉ መፅናናትን ተመኝቷል።