Get Mystery Box with random crypto!

ሰንበት ት/ቤት

የቴሌግራም ቻናል አርማ sundayschool16 — ሰንበት ት/ቤት
የቴሌግራም ቻናል አርማ sundayschool16 — ሰንበት ት/ቤት
የሰርጥ አድራሻ: @sundayschool16
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.73K
የሰርጥ መግለጫ

የአባቶቻችንን ትምህርት እናስተምራለን ፤ ተስፋቸውንም ተስፋ እናደርጋለን ፤ የምናምንባት፤ የተማርናት፤ ተስፋ የምናደርጋት ሃይማኖት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትናችን ይቺ ናት። እንኖርባታለን፤ እንሞትባታለን፤ በእግዚአብሔር ፈቃድ እንነሣባታለን።

(ሐይማኖት አበው ፤ አባ ገብርኤል)
ተዋሕዶ ሐይማኖቴ የጥንት ነሽ የእናትና አባቴ !

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-18 08:00:59 ​​​​ሰኔ 12 #የቅዱስ_ሚካኤል ዓመታዊ በዓል!

እንኳን ለመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ለእናታችን ቅድስት አፎሚያ አመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ። ሰኔ 12 ቅዱስ ሚካኤል እናታችን ቅድስት አፎሚያን ከጠላት ዲያብሎስ እጅ ያዳነበት ፣ እናታችን ቅድስት አፎሚያ እረፍቷ ነው ።እግዚአብሔር ከቅዱሱ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ፣ ከእናታችን ቅድስት አፎሚያ በረከት ተካፋይ ያድርገን ።

በወርኃ ሠኔ መታሰቢያ ከሚደረግላቸው ቅዱሳን መካከል እግዚአብሔርን የሚፈራ የአስተራኒቆስ ሚስት የሆነች የቅድስት አፎምያን ታሪክ በአጭሩ እንዳስሳለን፡፡

ቅድስት አፎምያ በትዳር በነበረችባቸው ዘመናት እግዚአብሔርን ከሚወድ ባለቤቷ ጋር እግዚአብሔርን ስታገለግለው የኖረች ሴት ነበረች፡፡ በየወሩ በ29 ቀን የጌታችንን የልደቱን፣ ወር በገባ በ21 የእመቤታችንንና ወር በገባ በ12 የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያደረጉ ነዳያንን ይጎበኙ እንደነበር ታሪካቸው ይነግረናል፡፡

ባለቤቷ አስተራኒቆስ ከዚህ ዓለም የሚያርፍበት ጊዜ እንደደረሰ ባወቀ ጊዜ ይሰጡት የነበረውን ምጽዋት እና የሦስቱን በዓላት መታሰቢያ ማድረግ እንዳታስታጉል ከአደራ ጋር አዘዛት፡፡ እሷም የመልአኩን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል ያሥልላት ዘንድ ባለቤቷን ጠይቃ አሠርቶ ሰጣት፡፡ በከበረ ቦታም አኖረችው፡፡

ባሏ ካረፈ በኋላ ያዘዛትን መንፈሳዊ ሥራ ከወትሮው አስበልጣ መሥራት ቀጠለች፡፡ የሰው ልጆች ጠላት የሆነው ሰይጣንም በመልካም አገልግሎት ስትበረታ ባያት ጊዜ ዝም ብሎ ሊተዋት አልወደደም፡፡ በመጀመሪያ ባል ሳታገባ ማገልገሏን ትታ፣ ሌላ ባል አግብታ፣ ልጅ ወልዳ እንድትኖር በብዙ ማባበል ጠየቃት፡፡ ባሏ መንግሥተ ሰማያትን ስለወረሰ ምንም ምጽዋት እንደማይሻ አስመስሎ ነገራት፡፡

ቅድስት አፎምያ ግን ዳግመኛ ትዳር ላለመመሥረት ቃል ኪዳን እንደገባች ርግብንና ዖፈ መንጢጥን አብነት አድርጋ፤ እነሱ እንኳ በሕይወት ዘመናቸው ከአንድ ባል ውጪ ሌላ ባል እንደማያውቁ በመጥቀስ አሳቡን እንደማትቀበለው ገለጸችለት፡፡ ሰይጣንም አስመሳይ መሆኑ አላዋጣ ሲለው ማንነቱን ቀይሮ ሊያንቃት ቢሞክር የእግዚአብሔርንና የቅዱስ ሚካኤልን ስም ጠርታ አባረረችው፡፡ እሱም ተመልሶ መጥቶ እንደሚያጠፋት ዝቶባት እንደአቧራ በኖ፤ እንደ ጢስም ተኖ ጠፋ፡፡

በሠኔ ፲፪ ቀን የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያዘጋጀች ሳለች ሰይጣን ብርሃናዊ መልአክ መስሎ መጣ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ገልጾ የመጀመሪያውን የመሰለ ከንቱ ምክሩን አሰማምሮ አቀረበላት፡፡ አሳቡንም የእግዚአብሔር ፈቃድና አሳብ እንደሆነ አድርጎ ለማሳመን ሞከረ፡፡ ሰይጣን አስቀድሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በገዳመ ቆሮንቶስ መጻሕፍትን እየጠቀሰ እንደተፈታተነው ሁሉ ቅድስት አፎምያንም ለማሳመንም አብርሃምን፣ ይስሐቅን፣ ያዕቆብን፣ ዳዊትን የመሳሰሉ ደጋግ አባቶችን ታሪክ እየጠቀሰ ወደ ትዳር እንድትገባ ደጋግሞ ወተወታት፡፡

ቅድስት አፎምያም በእግዚአብሔር ኃይል ጸንታ በቅዱስ ሚካኤልም ተራዳኢነት ታምና “የእግዚአብሔር መልአክ ከሆንክ መንፈሳዊ ማረጋገጫህ የሆነው የመስቀል ምልክት የታለ?” በማለት በምድራዊ ንጉሥና በጭፍራው መካከል የሚኖርን የጋራ መግባቢያ መንገድ ዋቢ አድርጋ ጠየቀችው፡፡

ለጊዜው “በኛ በመላእክት ዘንድ እንዲህ አይደለም” ብሎ ሊሸነግላትና አቋሟን ሊያስቀይራት ሞከረ፡፡ ከቤቷ ያለ የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ላይ ያለውን ምልክት አብራርታ የእሱ ግን ከዛ ጋር አንድነት እንደሌለው አረጋገጠችበት፡፡ ከቤቷ ላለው ለቅዱስ ሚካኤል ሥዕል እጅ እንዲነሣ ጠየቀችው፡፡ በዚህ ጊዜ መልኩ ወደ ትክክለኛ ማንነቱ ተለወጠና ጨለማ ለብሶ እየዛተ አነቃት፡፡ ቅድስት አፎምያም የከበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤልን “ድረስልኝ” እያለች በጠራችው ጊዜ መልአኩም ፈጥኖ በመድረስ ከሰይጣን እጅ አዳናት፡፡

የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ለሰይጣኑ ተገቢውን ቅጣት ሰጥቶ ቅድስት አፎምያን ባረካት፡፡ የዕረፍት ቀኗ በዚህ ቀን መሆኑን ነግሮ ቤቷን እንድታዘጋጅ አዘዛት፡፡ የበዓሉን ዝግጅት አከናውና ሥጋ ወደሙን ተቀብላ ኤጲስ ቆጶሱንና ካህናቱን እንደየመዓርጋቸው ጠርታ በቤቷ አክብራ ተቀበለቻቸው፡፡ ለነዳያንና ለጾም አዳሪዎች በኤጲስ ቆጶሱና በካህናቱ እጅ ገንዘቧን መጽውታ መንገዷን አሳመረች፡፡ ስለ ኃጢአቷ እንዲጸልዩላት ተማፅና በፊታቸው ተንበርክካ ጸለየች፡፡ ባሏ ያሠራላትን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አቅፋ ስማ ከተማጸነች በኋላ ሠኔ ፲፪ ቀን በሰላም ዐረፈች፡፡

ይህች የታመነች ቅድስት አፎምያ በሰላም እስክታርፍ ጊዜ ድረስ የተጓዘችበትን መንፈሳዊ ጎዳና አስተውለን ይሆን? አስቀድማ ከባሏ ጋር አንድ ሆና በታማኝነት ፈጣሪዋን አገለገለችው፡፡ በኋላም የባሏን ኑዛዜ አክብራ ምንም እንኳን ኃጢአት ባይሆንባትም በሁለተኛ ትዳር ራስዋን ማጠላለፍ አልፈለገችም፡፡ በጎ ሥራ አብልጣ በመሥራት እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት ተፋጠነች እንጂ፡፡

ሰይጣን ልጅ አለመውለዷን ተጠቅሞ ያቀረበላትን የጋብቻ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ “መንፈስን ሁሉ አትመኑ፤ መናፍስት ከእግዚአብሔር እንደሆኑ መርምሩ” ተብሎ በቅዱሳት መጻሕፍት የታዘዘውን መመሪያ ተጠቅማ ሰይጣንን በተወክሎ እግዚአብሔር ተቃውማ አሸነፈችው፡፡ የቅዱስ ሚካኤልን ርዳታ ያገኘችውና በሰላም ዐርፋ ወዳገለገለችው እግዚአብሔር በክብር የሔደችው በጽናት ተጋድላ ነው፡፡

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ እኛንም በጸሎቷ ይማረን፤ የቅዱስ ሚካኤል የረድኤቱ ኃይል ሁላችንንም ይጠብቀን፣ ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
465 views05:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 00:51:36 #ጥያቄ ፦

ጠያቂያች ወለተ ጊዮርጊስ እንዲ የሚል ሀሳብ አዘል ጥያቄ በውስጥ መሰር ወርወር አድርገውልናል:: ወቅቱ አንተ የእነ እንታ ዘር አንተ የእነ እንትና ዘር እየተባባሉ እርስ በእርሳቸው በጎራ የሚሻኮቱበት እንደሠሆኑ መጠን ዘረኝነትን አስመልክታችሁ አጠር ያለህ ትምህርት ብታስተምሩን የሚል ነው::

ለጠያቂያችን ለወለተ ጊዮርጊስ የሕይወትን ቃል ያሰማልን እያልን ከክታበ መለከት ካገኘናት ጽሁፍ ለጊዜው ትሆነን ዘንድ ይዘንላችሁ ቀርበናል ተከታተሉን::

( ዘር መቁጠርና መዘዙ )

የሰው ዘር መገኛ መሠረቶች አዳምና ሔዋን መሆናቸውን ቅዱስ መጽሐፍ ይነግረናል:: እኛ የሰው ዘሮች በምልዐት የሰፈርንባት ከመነሻችን ከአዳም መጀመሪያ ሆነን እግዚአብሔር በሰጠን ቡራኬ እየበዛን እስካለንበት ዘመን ደርሰናል::በዘመናችን በተለይ በተለይ በቅድስት ኢትዮጲያ ዲያቢሎስ ያሰለጠናቸው ሰዎች አንደበታቸውን በተቆጣጠረው መንፈስ እየተመሩ የመለያየት መንፈስ እንዲፈጠር በማድረግ ብዙ ጥፋቶችን እየፈጸሙ ነው በዚህ መዘዝ በከንቱ የሚፈሰው ደም ለወደፊቱ አጥፊዎቹ ከስህተታቸው ካልታረሙ የሚያፈሱት የደም ጎርፍ እነርሱኑ አጥፊዎቹን እንደ ባህር ማስጠሙ አይቀርም::

ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ በመለያየት ላይ የነበሩትን የግሪክና የአይሁድ ሰዎችን ሲገስጽ እንዲ ብሏል:: "አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም ባርያ ወይም ጨዋ ሰው የለም ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና" ገላ3÷28

እንግዲህ የተቀደሰው ሐዋርያ እንደነገረን እንኳን ኢትዮጲያዊ ዜጋ ቀርቶ አይሁዳዊና የግሪክ ሰው መላው የሰው ዘር የተፈጠረው በእግዚአብሔር ፈቃድና ቸርነት ሰለሆነ እንደ አንድ ሰው ተቆጥሮ በሰላምና በስምምነት በፍቅር ተከባብሮ በአንድነት መኖር ይጠበቅበታል::

ይህ ጥቅሙ ለህሊና ጤንነት ነው :: በጠብና ባለ መስማማት ምን ትርፍ ይገኛል ::ለመሆኑ በጤነኛ አእህምሮ ስናስበው በተፈጥሮ እኛን የሚመስለውን ሰው በአሰቃቂ ሁኔታ በስለት እንዲወጋ ማድረግ ፣ ማፈን ፣ ዐይኑን እጁን እግሩን ስንቆራርጠው ድርጊቱን ለመፈጸም የገፋፋንን መንፈስ እንዴት ለመመርመር ተሳነን ? እንዴትስ ይህን ድርጊት መፈጸም ሰውነታችን ሊቀበለው ቻለ ድርጊቱንስ ስንፈጽመው ሰው እንኳን አጠገባችን ባይኖር ህሊና የሚባለውን ዳኛ እንዴት ሳናፍረው ቀረን? ከዚህ በላይ የፈጠረንን አምላክ እንደምን ችላ አልነው? ማንም ሰው የጭካኔ ሥራን ለመሥራት ሲነሳሳ ሰውነቱን ወይም ምንነቱን ስለረሳ ነው ወደ ጭካኔ አሰራር የሚገባው የትኛውም ሰው ክፉ ተግባርን በሌሎች ሲፈጽም ድርጊቱን በገዛ ሰውነቱ ላይ እንደፈጸመ ይቆጠራል:: ምክንያቱም ወገኑን የሚቆራርጥበት ስለት ሰውነቱን ቢወጋው ጉዳቱ እንደሚሰማው አከራካሪ አይደለም::

ስለዚህ ሚዛናዊ አእምሮ ማጣት ካልሆነ በስተቀር በጭካኔ ወንድሙ ወይም እህቱ ላይ ስለቱን ሲያሳርፍ በገዛ ሰውነቱ ላይ እዳሳረፈ ለአፍታ ቢሰማው ኖሮ ለክፉ መንፈስ ተላልፎ መሰጠት አይኖርም ነበር::
በትንቢተ ሆሴ 4÷6 ላይ " ሕዝቤ ዕውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቶል " እንዲል የዕውቀት ማነስ ብቻ ሳይሆን የዕውቀት መብዛትም የብዙ ሰዎችን ዐይን አሳውሮ የማንነትን ጉዞ በማተረማመስ በጨለማ ውስጥ ሆኖ የጥፋት ድርጊቱን ማጧጧፉን ቀጥሏል::

በተለይ ምሁራን ለችግሮች ሁሉ መፍትኤ እንደሚሰጡ ይገመት ነበር እንዳለ መታደል ሆኖ ዛሬ በዘረኝነት ጽኑ ህመም ተይዘው የጸናው ሕመም እራሳቸው ላይ ሰለወጣ ስተው የሚያስቱ ከኤች አይ ቪ ኤድስና በጊዜያችን ከተነሳው ወረሽኝ ከኮሮና ቫይረስ ይልቅ ብዙዎችን እየጨረሰ ያለው የዘር በሽታ ሰለባ መሆናቸው እጁግ ያሳዝናል:: ይህ የዘር በሽታ የሕመሙ መተላለፊያ መንገድ መገናኛ ብዙኃን በመሆናቸው የሚሰማቸውና የሚያቸውን እንዲሁ የሚያነባቸውን ሁሉ የመመረዝ ኃይላቸው ከፍተኛ ነው ::እልቂቱም እጅግ የከፋ ይሁናል :: ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ጥበበኞች ወይም ስለ ሙሁራን መሳት እንደሚከተለው ተናግሯል "ጥበበኛ የት አለ ? ጸአፊስ የት አለ? የዚህ ዓለም መርማሪስ የት አለ? እግዚአብሔር የዚህችን ዓለም ጥበብ ሞኝነት እንዲሆን አላደረገምን?"1ቆሮ1÷20

እጅግ የተመሰገነው የእግዚአብሔር አገልጋይ ቅዱስ ጳውሎስ የጻፈልንን ይህን ንግግር ከዘመናችን አንጻር ብንመዝነው ከዓለም አቀፍ እስከ አህጉራችን እና እስከ ትንሿ ሀገራችን ብናይ ጥበበኞች ጸአፊዎች ተመራማሪዎች ጥበባቸው የከበረ የሰው ልጅ ከመጥቀሙ በተቃራኒው አጥፊ እየሆነ እንደመጣ እየተመለከትን ነው::

ማብቂያ የሌላቸው ጦርነቶች ንጹሐን ሕጻናትን አረጋዊያንን ደካሞችን ብቻ ሳይሆን የጎበዛዚትንም ሕይወት እየቀጠፈ ነው ::ዓለም በትርምስ በእልቂት እየተቀጣ ነው የእልቂቱም መንገድ እጅግ ያስገርማል ሰደድ እሳት ፣ የመሬት ነውጥ ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ ፣ ጎርፍ፣ ርሃብ፣ ቸነፈር፣ድርቅ፣ አውሎ ነፋስ ፣የአሸባሪና ተሸባሪ መጠፋፋት ወዘተ በዘመናችን የሚገኙ የእግዚአብሔር ቁጣ መገለጫዎች ናቸው ::

አሁን አያላን ነን ብለው የሚስቡ እኔ ከማን እንሳለው በማለት ዓለም ይጠፋል እንጂ ከሥልጣኔ ከዙፋኔ አልወርድም የታላቆች ታላቅ ነኝ የሚል የመከረ መፍለቂያ ንግግር ወደ ማያባራ የነፍስና የሥጋ መከራ ብዙኃኑን ወደ ሞት መንገድ እየወሰደ ይገኛል ::በልዮ ልዮ ደረጃ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎች እየተባሉ ውይይቶች ይደረጋሉእጅግ የሚገርመው ነገር ግን በጉባኤው የእግዚአብሔር ስም አይጠራም ታዲያ እንዴት ከቁጣና እልቂት ለመዳን ይቻላል? ያልተፈታ እቆቅልሽ ነው :: ከፍ ብለን በዓለም አቀፍ ደረጃ የተገለጠውን በቅድምያ የመቀመጫና መቆሚያን ወይም ቅድሚያ የሀገር ጉዳይ ካልን ደግሞ ወደ ሀገራችን ኢትዮጲያ መለስ ብለን "ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች " የሚለውን አስበን ወደ ፈጣሪ በችግሮቻችን ዙሪያ መለመን ብንጀምር እና ወደ ቀሪው ጉዳያችን ብናልፍ የሚሻለው መንገድ ይህ ነበር :: መዝ 67(68)÷31

ለዚህ በጎ ሀሳብ አዋቂዎች በጥብዐት ስመ እግዚአብሔርን ጠርተው ቢወያዮ መልካም ሁሉ ለቅድስት ሀገራችን ይሆንላት ነበር::ዘር መቁጠሩም ቀርቶ ሁሉም ፊደል ይቆጥር ነበር :: ፊደሉም እ....ን....ስ....ማ......ማ.....የሚል ነው::

ይህችን ጊዜያዊ የእንግድነት መኖሪያችንን ስንለቅ ዘር ጾታ ቀለም የሥልጣን የሀብትና ዕውቀት ጀረጃ ሳይለያዮባት መልካም የሥራ ሁሉ የአዳም ዘር የሚወርሳት ገነት መንግሥተ ሰማያት አስበን በጊዜያዊ ምድራዊ ሕይወት ጥቅም ዘላለማዊ መንግስት እንዳናጣ እንጠንቀቅ ለዚህም የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን ተራዳይነት አይለየን......አሜን

ምንጭ:- መለከት 27 ዓመት ቁጥር2 ገጽ 2012ዓ.ም
520 views21:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 20:56:20 ድንግል ሴት ትፈልጋለህ ?

ምንም እንኳን ሰዎች ሁሉም ባይሆኑም ብዙ ሰዎች ግን የሚያገቧት ሴት ድንግል እንድትሆን ይፈልጋሉ። አንዳንዶች ደግሞ መፈለግ ብቻ ሳይሆን የመጀመሪያ መስፈርታቸው ያደርጉታል ። ይህ እጅግ ደስ የሚያሰኝ አቋም ነው። ምክንያቱም የኹሉም ሰው አቋም እንዲህ ቢሆን ኖሮ ሴቶች ኹሉ በንጽሕና መኖርን ለወደፊት ትዳራቸው መቃናት ሲሉ ስለሚለማመዱት ነው።

ታዲያ ሚስቱ ድንግላዊት ሆና ቢያገኛት የሚመኝ ሰው እርሱም ድንግልናውን የጠበቀ ሆኖ መገኘት እንዳለበት ለአፍታም እንኳን ቢሆን መዘንጋት የለበትም። ስለዚህ ይህን የሚመኝ ራሱን ይጠብቅ። ካላገባኻት ሴት ጋር አንሶላ መጋፈፍን አትሻ። ልታገባ አንድ ቀን የቀረህ ቢሆን እንኳን ሳታገባት ይኽን መሞከር የለብኽም። በሰዓታትና በቅጽበት ውስጥ በእቅፍኽ ያለች እጮኛህ ያንተ ሚስት መሆን የማትችልበት ሁኔታ ይፈጠር እንደሆነ አታውቅምና። አንተ ራስህ ከነድንግልናህ የምትፈለግበት ጋብቻ ከፊተህ ይጠብቅሀል ።

እርሷም በምትሄድበት ቦታ ባሏ ከነ ሙሉ ክብሯ ይሻታል። ታዲያ ካላገባሃት ሴት ጋር ለምን ትተኛለህ ? ካላገቧት ሴት ጋር ምንጣፍ መጋራት በሰው ቤት መግባትና ከባለ ትዳር ሴት ጋር እንደ ማመንዘር ነው። ያላገባች መሆኗ ልዩነቱ ባሏን መቅደምህ ብቻ ነው። አንተ በሰው ትዳር እንዲህ የምተገባ ከሆነ ሌሎች ደግሞ አንተ የምታገባትን ሴት ከክብር አስንሰው ንጽሕነዋን ገፈው ያቆዪሀል። አንተ ድንግል ሳትሆንና የብዙዎችን ሕግ አፍርሰህ ድንግል ሴት መፈለግህ አያስገርምም ?

ሰው የራሱን ድንግልና ቢጠብቅ እግዚአብሔር ደግሞ በድንግልና የተጠበቀች ሚስት እንደ ፍላጎቱ ሊሰጠው ተስፋ ሰጥቷል። ሰው የራሱን ዕቃ ቢጠብቅ ለእርሱ የሚገባውን ዕቃ እግዚአብሔር በክብር ይጠብቅለታል ። በመጽሐፍ ቅዱስ ዕቃ የሚባለው አባለ ዘርዕ (ኀፍረተ አካል ) ነው። ቅዱስ ዳዊት በእውነት ከመጣን ጀምረን እኛ ሰውነታችንን ከሴቶች ሶስት ቀን ጠብቀናል የብላቴኖችም ዕቃ የተቀደሰች ናት ስለዚህ ዛሬ ዕቃቸው የተቀደሰች በመሆኗ እንጀራው እንደሚበላ እንጀራ ይሆናል 1ኛሳሙ 21:5 በማለት የተናገረው ቃል ኀፍረተ አካል ዕቃ እንደሚባል ያስረዳል።

የራሱን ንጽሕና የጠበቀ ሰው ለእርሱ የምትሆነው ሚስቱ ከነቅድስነዋ ከነንጽሕነዋና ከነሙሉ ክብሯ (ድንግልነዋ) እንደሚያገኛት ማወቅ አለበት ሲል ሐዋሪያው "ከእናንተ እያንዳንዱ የራሱን እቃ (ሚስቱ የምትሆነውን ) በቅድስናና በክብር (ከነድንግልነዋ) ያገኝ ዘንድ እንዲያውቅ" በማለት ይናገራል። "ዕቃ" የሚለው ኀፍረተ አካል መሆኑ ከላይ በማያሻማ መልኩ ተገልጿል። ስለዚህ ድንግልን ማግባት የሚፈልግ ሰው የራሱን ክብር መጠበቅ ይኖርበታል። (1ኛ ተሰሎንቄ 4÷5)

ምንጭ ፦ (ቀሲስ ኅብረት የሺጥላ)
684 views17:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 20:31:21 ​​ጾመ ሐዋርያት/የሰኔ ጾም !

ጾመ ሐዋርያት ሐዋርያት በጽራሐ ጽዮን መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ወደ አገልግሎት ከመግባታቸውና ወደ ሀገረ ስብከታቸው ከመበተናቸው በፊት የጾሙት ጾም ነው፡፡ የጾሙበትም ምክንያት በማርቆስ ፪፥፳ እና በማቴወስ ፱፥፲፬ ላይ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረውን መሰረት በማድረግ ነው፡፡ ይኸውም የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው እኛና ፈሪሳዊያን ብዙ ጊዜ የምንጾመው ደቀመዛሙርትህ ግን የማይጾሙት ስለ ምንድን ነው? አሉት፡፡ ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፡-ሚዜወች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን ? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል ያን ጊዜ ይጾማሉ፡፡››ብሎ እንደመለሰላቸው፡፡

በዚህ ምሳሌያዊ አነጋገር ሙሽራ የተባለው ካባ በመደረብ ፈንታ ዕርቃኑን ሆኖ በአክሊል ፈንታ የእሾህ አክሊል ደፍቶ በሚዜወቹ ፈንታ በጠላት ተከቦ በመዝሙርና በደስታ ፈንታ በልቅሶና በዋይታ ታጂቦ በክብር ዙፋን መቀመጥ ፈንታ በመስቀል ተሰቅሎ በጭንካር ተወጥሮ በቀራንይዎ አደባባይ ስለ እኛ የተሞሸረው/የተሰቀለው/ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ሚዜዎቹ የተባሉት ደግሞ ምንም እንኳን በሰርጉ እለት ከአንዱ በቀር (ከወንጌላዊ ዮሐንስ/ ከጎኑ ባይገኙም ኋላ መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው በሕይወትም በሞትም ሙሽራውን/ኢየሱስ ክርስቶስን/ የመሰሉ ሐዋርያት ናቸው፡፡

ይወሰዳል መባሉም እርገቱን ለመናገር ሲሆን ከዚያ በኋላ ይጾማሉ መባላቸው ደግሞ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ለማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ኢየሱስ ሲያርግ መንፈስ ቅዱስ ይመጣልና፡፡ በዚህ ላይ ልብ ልንል የሚገባን ጉዳይ ጾም በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበረ በሐዲስ ኪዳንም የቀጠለ ሥርዓት መሆኑን ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን የነበረ ስለመሆኑ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት እና አይሁድ ብዙ ጊዜ ይጾሙ እንደነበረ ተጽፏል፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት"እናንተና አይሀድ የጾማችሁት ባለማወቅ ወይም በስህተት ስለሆነ ደቀ መዛሙርቴ አይጾሙም" አላለም፡፡ ነገር ግን ለጊዜው ከእኔ ጋር ናቸው ደስ ሊላቸው ይገባል፡፡ ከሄድኩ በኋላ ግን ይጾማሉ ብሏል፡፡ ይኸውም ጾም ከአዳም ጀምሮ እስከ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እና ደቀ መዛሙርቱ ከዚያም በክርስቶስ ታድሶና ተቀድሶ ለደቀ መዛሙርቱ የተሰጠ ከዚያም ለእኛ ለተከታይዮቻቸው የተላለፈ ሥርዓት መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡

ለጊዜው ሐዋርያት ሊጾሙበት ያልቻሉበት ምክንት ሊቃውንት ሲያብራሩ ፡-አንደኛ ጾም ሐዘን ነውና ሐዘኑም ኃላፊነትን ከመሸከም ጋር ተያያዥነት ያለው ነውና፡፡ ምክናያቱም መጾም አላማው ንስሐ እንደመሆኑ እንደ ቅዱስ ዳዊት ለግል ኃጢያት አሊያም እንደነነዌ ሰዎች ስለሀገር ጥፋት የሚያለቅሱበት የሚያዝኑበት ሁኔታ አለው፡፡ ክርስቶስ ደግሞ በስጋው ወራት ከአምላክነቱና ከሁሉ አባትነቱ ባሻገር ለሐዋርይት እንደ ሥጋ አባትም ወንድምም በመሆን የእነርሱን ኃላፊነት ተሸክሞላቸዋልና እርሱ በአካለ ሥጋ በአጠገባቸው እስካለ ድረስ ማዘን አልተገባቸውም፡፡

በሁለተኛነት ደግሞ ጾም ኃላፊነት ነው፡፡ኃላፊነቱን ለመሸከም ደግሞ ኃይል የሚሆናቸው መንፈስ ቅዱስ ያስፈልጋቸው ነበርና መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ እንዲጾሙ ጊዜ ሰጣቸው፡፡ ሦስተኛው ምክነያት አይሁድ ይጾሙት የነበረው በብሉይ ኪዳን ስርዓት ውስጥ ሆነው ነበር፡፡ ሐዋርያት ደግሞ የሐዲስ ኪዳን ልጆች ስለሆኑ መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው አሊያም አዲሱ ሰው በተባለው በክርስቶስ ደም ተጽናንተውና ሥጋውንና ደሙን ተቀብለው አዲሱን ሰው ለብሰው በአዲስ መንፈስና ኃይል በአዲስ ስርዓት መጾም ስለነበረባቸው በጊዜው አልጾሙም ነበር፡፡/ማቴ ፱፥፲፮-፲፯/

ሐዋርያት የጾሙት ጾም የኢየሱስ ክርሰቶስን ፈለግ መከተላቸውን የሚያሳይነው፡፡ መምህራቸውና አምላካቸው ኢየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ወንዝ በዮሐንስ እጅ ከተጠመቀ በኋላ ሌላ ሥራ ሳይጀምር ወደ ገዳመ ቆርንቶስ ገብቶ እንደጾመ ሁሉ እነርሱም በመንፈስ ቅዱስ ከተጠመቁ በኋላ አገልግሎታቸውን ከመጀመራቸውና ወደየሀገረ ስብከቶቻቸው ከመበተናቸው በፊት እግዚአብሔር መንገዳቸውን የተቃና ሥራቸውንም የተሳካ ያደርግላቸው ዘንድ ጾመዋል፡፡

ይህን ጾም ሐዋርያት ጾመው በረከት ያገኙበት ከመሆኑ ባሻገር ጌታችን ጾሞ ጹሙ እንዳላቸው እነርሱም ደግሞ ተከታይዎቻቸውን ያንኑ መልዕክት የደገሙበት ነው፡፡ በክርስቶስ ደም መሰረት ላይ እና በሐዋርያት ትምህርትና ትውፊት ላይ የተመሰረተችው ቤተ ክርስቲያናችንም ይህንን ጾም በዐዋጅ እንድንጾመው ሥርዓት ሠርታልናለች፡፡

ጾሙ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ የጾሙት እንደመሆኑ መጠን ከጌታ ትንሣኤ ከሃምሳኛው ቀን በኋላ ማለትም ከጰራቅሊጦስ ዕሁድ ማግስት ሰኞ ጀምሮ በቅዱስ ጳውሎስና በቅዱስ ጴጥርስ በዓለ እረፍት መታሰቢያ በሆነው ሐምሌ አምስት ቀን ፍጻሜውን ያገኛል፡፡ የቀናቱ ብዛትም በዐቢይ ጾም መባቻ ሁኔታ የሚወሰን ይሆናል፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን ጾሙን የበረከት፣ የንስሐ ፣ ደዌን ማራቂያ፣ ዲያቢሎስን ድል መንሻ ያድርግልን!!!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
አሜን!
490 views17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 06:12:54 ፍቅር ይዞኛል ለምትሉ ሁሉ !

አንተ ፍቅር ይዞኛል የምትለው፤ አዎ አንተ በፍቅሯ አብጃለው፣ ስነሳም ስተኛም ስለእርሷ ነው የማስበው የምትለው! በዓይኗ ሰረቅ አድርጋ ድንገት ስታየኝ ልቤ ቀጥ ይልብኛል የምትለው፤ እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ? አያድርገውና በመጀመሪያ ያየሃት ቀን ያፈዘዘህ ዓይኗ ቢፈስ፣ ቀልብህን ስቦ ያስደነገጠክ መልኳ ቢጠቁር እና ቢጠፋ፣ እስከ ወገቧ የረዘመው ፀጉሯ ቢቆረጥ፣ አቅርበሃት ጓደኛህ ካደረካት በኋላ የወደድክላት ፀባዩዋ እና ሥርዓቷ ተለውጦ ክፉ እና ደረቅ ብትሆንብህ፣ አንጀትህን ያርሰው የነበረው አረማመዷና ቅልጥፍናዋ በበሽታ ተቀምቶ አልጋ ላይ ሆና ብታቃስት አሁንም ከእርሷ ጋር ትሆናለህ? እንደ ድሮ ከእርሷ ጋር ለመሆን ትሽቀዳደማለህ? ሁሌ እንደምታፈቅራትና እንደምትሳሳላት መንገርህን ትቀጥላለህ? ለእርሷ የምታሳየው ትህትናና ክብር ይቀንስብሃል? አንቺስ ብትሆኚ? መጀመሪያ ያየሽው ዕለት ደስ ያለሽ መልኩና ቁመናው እንዳልነበረ ቢሆን፣ ሁሌ አንቺን ለማስደሰት ብሎ አንቺን በመጋበዝ እና በማዝናናት ያጠፋው የነበረው ገንዘብና ሀብት ጠፍቶ ፍጹም ደሃ ቢሆን፣ መጀመሪያ የተዋወቃችሁ ሰሞን ሲያሳይሽ የነበረው ፍጹም ትህትና እና አክብሮት ተለውጦ በትዕቢት አንቺን መማታት ቢጀምር፣ ጤንነቱን አጥቶ በበሽታ ቢንከራተት፣ በመጀመሪያ ወደ እርሱ ስቦ ያመጣሽ ነገሮቹ ሁሉ ቢጠፉ አሁንም ከእርሱ ጋር ትሆኚያለሽ? አሁንም እርሱ ጋር ስልክ መደወልሽን ትቀጥያለሽ? እህቴ ሆይ እስቲ ንገሪኝ፤ ፍቅርሽ ከአፍሽ ነው ወይስ ከልብሽ? ወንድሜ ሆይ ልጠይቅህ፤ ፍቅርህ በመናገር ነው ወይስ በተግባር?

መልሳችሁ " ይህ ቢፈጠር አብሬ አልቀጥልም" ከሆነ ከመጀመሪያውም ፍቅር እንዳልያዛችሁ ላርዳችሁ እወዳለሁ፡፡ ስትተያዩ እወድሃለሁ፣ እወድሻለሁ ከምትባባሉ ባየሁሽ/ ባየሁህ ቁጥር በውስጤ ያሉት ንጥረ ነገሮች (hormones) ይንተከተካሉ ብትባባሉ የተሻለ ነው፡፡ ምክንያቱም የፍቅር ትርጉም ይህ አይደለምና፡፡

ፍቅርማ ምን እንደሆነ ራሱ ፍቅር የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገባ አስተምሮናል፡፡ እርሱ ከምድር አፈር ካበጃጀን በኋላ የሕይወትንም እስትንፋስ እፍ ካለብን በኋላ ፍጥረት ሁሉ መልካም እንደሆነ ተመልክቷል፡፡ ያኔ አምሮብን፣ ተከብረን ሳለ ወዶናል፡፡ እፀ በለስን በልተን ያበራ የነበረው የጸጋ ልብሳችን ተገፎ ራቁታችንን ስንሆን፣ ደዌ የማያውቀው ሥጋችን በከንቱ ፍትወታት ሲታመምም በፍጹም ፍቅሩ አፍቅሮናል፡፡ ይተወንም ዘንድ ስላልቻለ ፍቅርን ፍቅር ከዙፋኑ ስቦ ስለእኛ እስከ ሞት አደረሰው፡፡ ታመን በኃጢአት አልጋ ተኝተን ሳለ ከጎናችን ሳይለይ ያሳታመመን አምላካችን ነው፡፡ እስከመጨረሻው ድረስ በኃጢአት የከረፋነውን ሳይጸየፈን ተጠግቶን ቁስላችንን በቁስሉ ያከመን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ሊያክመን መጥቶ እንኳን እኛ አልተቀበልነውም፡፡ ቁስላችንን ሳይጸየፍ የቀረበንን ፈጣሪያችንን መታነው፡፡ ኑ ላድናችሁ ሲለን በመስቀል ላይ ሰቀልነው፡፡ ሐኪሙን የሚሳደብና የሚማታ በሽተኛ እንደምን ያለ ነው? የበሽተኛውን ስድብ እና ድብደባ ታግሶስ በትጋት የሚያክም ሐኪም እንደምን ያለ ነው? ለዚህስ አንክሮ ይገባል!!

ወዳጄ ሆይ ፍቅር በደስታ ጊዜ ኖሮ በኃዘን ጊዜ የሚጸና፣ በጤናው ጊዜ አብቦ በደዌ ጊዜ የሚፈካ፣ በሰላም ጊዜ ተኮትኩቶ በጭንቅ ጊዜ የሚበቅል ረቂቅ የአምላክ ስጦታ ነው፡፡ ታድያ ወዳጄ ሆይ በፍቅርሽ ተይዣለሁ ያልካት ሚስትህን ያማረው መልኳ በድንገት ቢጠፋስ ብለህ የምትጨነቅ ከሆነ እንዴት እወዳታለሁ ልትል ትችላለህ? ጤናዋን አጥታ አልጋ ላይ ብትተኛ ጥለሃት ለመሄድ የምታስብ ከሆነ እንዴት እወድሻለሁ ልትላት ትችላለህ? አንቺስ ብትሆኚ፤ ፀባዩ እንዳለ ተለውጦ ቢንቅሽና ቢያቃልልሽ ትተሽው ለመሄድ የምታስቢ ከሆነ እንዴት ዓይኑን እያየሽ እወድሃለሁ ትይዋለሽ? ቢመታሽም እንኳን እንደ አምላክ ምቱን ታግሰሽ እርሱን ለማከም ካልፈቀድሽ እንዴት አፈቅርሃለሁ ትይዋለሽ?

" ፍቅር ያስታግሳልና"(1ኛ ቆሮ 13÷4) የማትታገሱ ከሆነ እንዴት ፍቅር ይዞኛል ትላላችሁ? አምላክ ያሳየንን ፍቅር ለሌሎች በመስጠት ክርስቶስን ልንመስለው ይገባናል፡፡ እህቴ ሆይ ወዳጅሽ በክፉ ሱስ ተጠምዶ፣ በትዕቢትና በንቀት ልቡ ተነድፎ ገብቶ ቢያንቋሽሽሽ ለእርሱ የምትሰጪው ፍቅር እንዲጎድል አትፍቀጂ፡፡ የፈለገ ተለውጦ የማታውቂው ሰው ቢሆንብሽም ለእርሱ የምትሰጪውን እንክብካቤ በትጋት ፈጽሚ፡፡ ያለንግግር ፍቅርሽን የሚነግሩትን ዓይኖችሽን ከዓይኖቹ አታንሺ፡፡ ወንድሜ ሆይ የሚስትህን የምትወድላት ፀባዩዋን ረስታ ደረቅና የምታውክ ብትሆንብህ እንኳን በስስት የምታያትን የፍቅር መመልከት አትንፈጋት፡፡ አምላክስ በሕመማችን ጊዜ ዓይኑን ከእኛ ድንገት ቢያነሳ ኑሮ ወድቀን እንደምንቀር ሁሉ አንተም ዓይንህን ከሚስትህ ላይ አታንሳ፡፡ ጌታ በፍጹም ፍቅር ወዶናልና እርስ በርሳችሁ በሚያስታግሰው እውነተኛው ፍቅር ተዋደዱ፡፡ በፍቅርም ቃል ተነጋገሩ እንጂ አትቆጡ፡፡

ቸሩ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ የአፍ ብቻ ሳይሆን የልቡና፣ በመናገር ብቻ ሳይሆን በተግባር የምንገልጠው እውነተኛውን ፍቅር ስጠን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!
452 views03:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 06:51:19 ዝነኛ አፍቃሪ !

ዛሬ ስለ ስለ ዝነኛ አፍቃሪ ልናወራ ነው። ፍቅር ያልኩት እውነት የሆነ ስሜት ሆኖ አደለም እንድንግባባ እንጂ..። ሁሉንም የውሸት ስሜት አሁን አለም ፍቅር ብላ ስም እየሰጠችው ነው። ግሩም እኮ ነው እንደውም ዝሙት መፈፀምን እኮ ፍቅር መስራት እየተባለ ነው ተሳሳትኩ እንዴ? ዝሙት ፈፀመ ለማለት ፍቅር ሰራ አደል የሚሉት? ብቻ ይገርማል ኀጢአት አሁን ፋሽን ሆኗል እንደ ኖርማል ነገር ነው የሚቆጠረው እንደ ፅድቅም እየተቆጠረ ነው። ዞሮ ዞሮ ወደ ፍቅር ተብየ ከሆኑት የውሸት ስሜቶች ውስጥ አንዱ ወደሆነው ርዕሳችን እንምጣና ዝነኛ አፍቃሪ ምን መሠላችሁ ዝናን መሰረት ያደረገ ፍቅር ነው። ብዙ ጊዜ ሴቶችዬ ናችሁ የምትያዙት በዚህ ፍቅር (አሯሩጦ የሚይዝ ፍቅርም አለ ማለት ነው እንግዲህ) አንድ ሰው ዘፍኝ ስለሆነ፣ በሰዎች ዘንድ የተወደደ ዝነኛ ስለሆነ፣ ሀብታም ስለሆነ......ብዙ ብዙ ብቻ የእከሌ ሚስት ናት እኮ ለመባል አለ አይደል ለጉራ ምናምን....

እሽ ዘፋኝ ምናምን ኧረ ደስ አይለንም ለምትሉ ወደ ቤተክርስቲያን ቀረብ ያላችሁ ( ማለትም ስጋችሁ ቀረብ ያለ ልባችሁን የት አውቄ) ሰባኪ ስለሆነ፣ ሲዘምር ድምፁ የሚያምር ስለሆነ፣ ቤተክርስቲያን ዘወትር ስለሚመላለስ ምናምንም ይሄው ስሜት ይነድፋችኋል ግን ከምር ደስ ይላል ማለት እንደዚህ ያለ ሰው ደስ ካላችሁ ደስ ይላል #ግን ምክንያታችሁ በቃ የሰባኪ ሚስት ናት ለመባል ( ባለቤቷ አገልጋይ ነው እየተባለ እንድትሞገስ መሆን የለበትም ፍላጎትሽ) ሲጀመር አንቺ መልካም አገልጋይ ያልሽው ሰው መልካም ላይሆን ይችላል እሱን ጌታ ነው የሚያውቀዉ አንች እያየሽው ባለ ነገር ብቻ እርግጠኛ መሆን የለብሽም። በሰው ፊት ጻድቅ መምሰል ቀላል ነው።

ወይም ደሞ መልካም ሆኖ ግን የራሱ አጋር ሊኖረው ይችላል እና ፈቃደ እግዚአብሔር ባይሆንስ ምን ታውቂያለሽ? ይቅርታ በሴቶች ብቻ ተጠቅሜ ተናገርኩ አብዛኛውን ሴቶች ስለሚጠቁ ነው በዚህ ወንዶችም ተጠንቀቁ።

ወንዶች እናንተ ደሞ ሮማንቲክ በሚባለው ብዙ ጊዜ ፍቅር ትያዛላቹ በሌላ ክፍል እንማማራታለን። አገልጋዮች ግን የምር ስትፀልዩ ሌሎችን እንዳታሰናክሉ እናንተም እንዳትሰናከሉ ጌታን ልትማፀኑ ይገባል ምክንያቱም በብዙ የውሸት ስሜቶችን ፍቅር አስመስሎ ሰይጣን እየተጠቀመ ነው።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን።

@sundayschool16
ሰንበት ት/ቤት
468 views03:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 10:57:13 ዘመናዊነት Vs መንፈሳዊነት !

ክፍል - 3

ቀድሞ እንደተነጋገርነው፤ ዓለማዊ ሉላዊነት የተስፋፋውና ሚዛንና ጉልበት ያገኘው በእነዚሁ መንገድ ከሆነ መፍትሄው እሾህን በእሾህ ነው እልሃለሁ። የትውልድን ዓይንና ጆሮ በዓለማዊነት ያሰከረ ሚዲያን የራስህ ማድረግና የተቀደሰ እሳቤን የሚያደረጅ ባለ ብዙ አማራጭ ክርስቲያናዊ ቻናሎችን መዘርጋት ነው።

የትውልድን በዓለማዊነት እርሾ የተበረዘ አዕምሮ ማጠብ ፣ መወልወል ማንጻት ያስፈልጋል። እናም በጎ እሳቤን የቤተሰብ ፣ የወገን ፣የሃገር ፣ የሃይማኖትና የማንነት ጉዳይ የሚያንገበግበው የማድረግ ጉዞን ለመመስረት የሚያስችለውን የአዕምሮ ምግብ መመገብ መቻል። የህግ ፣ የትምህርትና ሌሎች ጉዳዮችንም በተመሳሳይ ሃገር በቀል ቅኝት ፤ ማንነትን መሰረት ያደረገና የዋጀ ፍፁም ብልጫና መሰረት መጣል ተገቢ ነው። እንዴት የሚለው ብዙ ትንታኔ ይፈልጋልና ለጊዜው ያዝ ላድርገው። ለእሱ የሚሆን አቅምና የልቦና ትከሻ ላይ አልደረስንም ። አሁን ወተት ወተቱን ብሎም ፍትፍቱን ፥ “ራስን ዘወር ብሎ የማዬትን ሻማ ከማብራት” ብንጀምር ይሻላል።

ትውልድን ከማንሣት ፣ ከመማረክ ና ከማንፃት እሳቤ የሚቀድመው ራስን ከዓለማዊ ምርኮ ማውጣት ነው። እናም መጀመሪያ እስኪ ራሳችን በዓለማዊ ምርኮ ስላለመውደቃችን እንጠያየቅ። ብዙዎቻችን የምንመራበት እሳቤ ና የአኗኗር ዘይቤ ክርስቲያናዊ የሚመስል ግን ደግሞ ዓለማዊነት ያሰጠመው ስለ መሆኑ ፤ የእኛ ሻማ ማብራት ራስን ከመፈለግና ከወዴት እንደወደቁ ከማሰብ ይጀምራል።

ተወዳጁ ወንድሜ ሆይ እስኪ በሕይዎታችን ቁልፍ የምንላቸውና መስዋዕት እስከመሆን የምንጋደልላቸው ፣ የምንተጋላቸው ጉዳዮች በምን ቅኝት የተቃኙ እንደሆኑ መለስ ብለን እንመልከት ። ተከተለኝ ። እብድና ሞኝ ልትለኝ የምትችልበትን ግን ደግሞ መሰረታዊ ጥያቄ ልጠይቅህ። እኔና አንተ ከዝንጀሮ በዝግመት የመጣን ነን ወይስ አይደለንም ? ስለዚህ ምን ትላለህ? ተወዳጁ ወንድሜ ለመለስም እንኳን ጥያቄውን እንደተጠየፍክብኝ እና እንደናቅከው አውቃለሁ። ግዴለም ተከተለኝ። ዓለማዊ ሉላዊነት ይህ አስተሳሰብ እንዲሰለጥንና እንዲያሸንፍ ይሰራል። እኔ ና አንተስ?

ተመልከት ወዳጄ፦ ከዝንጀሮ መጣን የማለት ዝርዝር ጉዳይ ምን እንደሆነ ታውቃለህ? የሕይወት ትርጉሙ እንዲህ ነው። አንድ ሰው ከዝንጀሮ መጥቻለሁ ሲል ከምድር ሌላ ሀገር የለም ብሎ ያስባል ፤ ስለዚህም ደስታን ፣ ውበትን ፣ ስኬትን ፣... የሚተረጉምበት እይታ የዝንጀሮ ትርጉም ነው ማለት ነው። ምን ማለት መሰለህ? ዝንጀሮ/እንሳሳ የለመለመውን ስለ መብላት ፥ የሚያረካ ውሃን ስለመጠጣት ይቦርቃል ፣ ይፈነጥዛል ፤ ዝንጀሮ /እንሳሳ የርሱን እኩያና ታናናሾቹን በማሸነፍና በቀንድ በመውጋት ደስታው ወደር የለውም ፤ የሚመካበት ብቸኛ ነገር ፥ የጉልበቱ መፈርጠም የኃይሉ መደርጀት ነው። እነርሱ በሚያውቁት በሌሎች መፈራት ፣ መከበርና በሌሎች ፊት መኩራራት ያስደስተዋል ። በሩካቤ ይደሰታል ፤ እርቃንነት መገለጫው ነው። ደስታንና ስኬትን ዛሬ ላይ ብቻና ብቻ ... ይልሃል።

ዓለማዊ ሉላዊነት ሲሰለጥንብህ የሕይዎት ትርጉምህ እንዲህ ነው። ከሞት ወዲያ ሕይዎት ፣ ከምድር ሌላ ሀገር የለም ትላለህ። በዚህም ምክንያት የኔና የአንተ የደስታ ፣ ስኬት ፣ ውበት፣ክብር ፣ ... ትርጉም ከዝንጀሮ ለመምጣት ምስክር ታደርገዋለህ።
ስለ ደስታ ስታስብ ፥ ደስታን በመብላት በመጠጣት ውስጥ የምትፈልግ ፤ እስኪ ዛሬስ ደስ ይበለን ስትል የሚመጣልህ ሃሳብ የጣመ የላመውን መብላት ፣ መጠጣት ሆኖ ታገኘዋለህ።

በዝሙት ትደሰታለህ ፣ በእርቃንነት ትረካለህ ፣ በሌሎች ላይ በመታበይ ከሌሎች በመብለጥህ ትደሰታለህ ። ሌሎችን በመጎሰም ፣ በሌሎች ላይ በመታበይና በመኩራራት ሥልጣንህንና ክብርህን የገለጥክ ይመስልሃል። በዚህም ትደሰታለህ። የአንተ ግብ መታወቅ እንጅ ማወቅ አይሆንም። ስለዚህም አንደኛ መውጣት እንጅ ማወቅ ያለብህን ነገር አውቀህ መገኘትህ አያሳስብህም።

በአጠቃላይ ላንተ የስኬት፣ የውበት፣ የደስታ ትርጉም በምድራዊነት ዛቢያ የሚሽከረከርና እንስሳዊ ሆኖ ታገኘዋለህ። ስለዚህም ለምድራዊ ቤት ፣ ለምድራዊ ድልብ ፣ ለምድራዊ ክብር ፣ስልጣን/ሹመት፣ ... እንቅልፍ አጥተህ የምታድርና ራስህን አሳልፈህ ለመስጠትም እንኳ ስትሆን ፤ ሰማያዊ መዝገብ ፣ ሰማያዊ ቤት ፣ ሰማያዊ ክብር ፣ ... ተግባራዊ ምላሽ የነፈግካቸው ጉዳዮች ናቸው። ሌላም ልጨምር ዝንጀሮ መጯጯህ እንጅ መደማመጥን አያውቅም ፤ ለምን እንደሆነ ሳያውቅ እንኳን አንዱ ሲጮህ ተከትሎ መጮኽ የርሱ መገለጫ ነው። ማሰብ የጎደለው የመንጋነት ፣ የዘረኝነት ጩኸትን የሚጮህ ፣ ከማዳመጥ ይልቅ እኔን ስሙኝ ማለትን የሚዎድ ሰውም በዓለማዊ ሉላዊነት የታሸ ምስኪን ሕይዎትን የሚመራ እንደሆነ ግልፅ ነው !

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን !

@sundayschool16
ሰንበት ት/ቤት
420 views07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 10:57:09 ዘመናዊነት Vs መንፈሳዊነት !

ክፍል - 2

ቤተክርስቲያን ለስልጣኔ ትልቅ ክብር አላት። ለሥልጣኔ ካላት ትልቅ ክብር በላይ እጅግ የሚገርመኝ ደግሞ ይህንን እሳቤ ከመንፈሳዊነት አንፃር የምታይበት ነፅሮትና ሥልጣኔን ዋጅታ የምትመራበት ሥልጡን ሃሳብ ነው። ልጆቿ ኑሮን ቀላል በማድረግ ሰበብ በምድራዊነትና በዓለማዊነት አዚም/መርገምት ዓይናቸውና ልቦናቸው ተይዞ እንዳይቀር ፤ የምቾት ሕይዎትንና ቅምጥልነትን ፈልቅቃ ሥልጣኔውን ዋጅታ በሥልጣኔ ላይ ሠልጣና የምድሩን የሰማዩንም ሕይዎት የመውረስ ጥበብ እንዴት ይደንቅ።

ድካምን ለመቀነስ የሚያግዙ የቴክኒዮሎጅ ውጤቶች ፣ ለአፍ የሚጣፍጡ ምግብ መጠጦች ፣ የደስታ ምንጭ ተብለው የተሰሩ እጅግ ብዙ ነገሮች የሥልጣኔ ውጤቶች እንደሆኑ ግልፅ ነው። እነዚህ ብዙዎች የሚጓጉላቸው እንደሆነም እሙን ነው። ቤተ ክርስቲያን ደግሞ እነዚህን እንደ ኢምንት ቆጥራ በሥልጣኔ ላይ ሠልጥና ፤ የበለጠ ሥሉጥ ርዕይን ትገልጣለች። ይህም ይህንን ጥበብ በእኛ ውስጥ ላኖረ አምላክ ፍቅርን የሚገልጡበትን የከበረ እሳቤና ልህቀት ነው። በዚህም ድካምን የሚገባ ድካምና የማይገባ ድካም ብላ ከፍላው ታገኛታለህ። ስለ ክርስቶስ ፍቅር ብለህ ርሱን ስለ ማግኘት መራብ ፣ መጠማት ፣ መነሣት፣ መውደቅ ፥ ስግደት የሚገባ ድካም ስትል ፤ ቴክኒዮሎጅ ጠል የሆነ ትችትንና ድካምን ደግሞ ስንፍና ትለዋለች። በችግር ውስጥ ሆነህ መራብን ታወግዛለች ፤ ስለ ፅድቅ ብለህ መራብን ታወድሳለች።

እናት ቤ/ክን “ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብጹዕ ነው” ማለቷን አንስቶ ፤ ልመናን የሚያበረታታ አቋም እንዳላት የሚያወራ ሰው የአዕምሮ ችግር ያለበት እንደሆነ ይሰማኛል። ይህ ቃል ብጹዕ መባልን ብትወድ ለራስህ የሚበቃህንም ብቻ አይደለም ፤ የሌሎችን ድካም የሚሸከም ስልጡን ስራን ገንዘብ አድርግ የሚል የሚያነቃቃ ሃሳብ እንጅ።

አስተውል ወዳጄ ቤ/ክን የበለጠ ሥሉጥነት ላይ ስትሆን ይሄኛውን ሥልጣኔ ልትንቀው ትችል ይሆናል። ይህ ግን ሥልጣኔን ጠላች አያስብላትም። ለምሳሌ በደመና ተጭነው ለሚበሩ አባቶች አውሮጵላን ምንም ነው። በጸጋ እግዚአብሔር በሳምንት ፣ በወር አንድ ጊዜ ቅጠሉ ጣፍጦላቸው ለሚመገቡ ፥ ብሎም ከምግብና ውጭ ለሆኑ አባቶቸ ፥ የዓለም ጠበብት የሚጓጉለት ምግብ ምንም ነው። ይህንን የበለጠ ጥበብ በሆዳምነትና በዓለማዊነት ሚዛን መዝኖ ፥ አለማወቅ ፥ ኋለቀርነት ከማለት በላይ ድንዛዜ የለም እላለሁ። ከዚህ ያፈነገጠ አስተሳሰብ ያለው ሰው ቢኖር እርሱ ቤ/ክንን አይወክልም።

ሉዓላዊነት ወደ ሚለው ሃሳብ ልምጣ !

ሉዓላዊነት ዓለምን በአንድ የሃሳብ ማዕቀፍ የመምራትና የመጠቅለል እሳቤ ነው። በአሁኑ ሰዓት ዓለምን ወደ አንድ ሃሳብ ለመጠቅለል ፤ አንዳንዶችም የአልሞት ባይ ተጋዳይነት ግብግብ ውስጥ በሚባል የሚደረግ ፍጥጫን እንመለከታለን። እነዚህም የተለያዩ ጎራዎች ናቸው። ወደዚህ ለመድረስ የሚጠቀሙበት መንገድ ልዩ ልዩ ሆኖ እናገኘዋለን። በጉልህና በትኩረት ልናያቸው የሚገቡንን ሦስት አይነት ፍጥጫዎች ብቻ ላሳይ።

1. ዓለማዊ ሉዓላዊነት - በፈጣሪ መኖር የማያምን ፤ ውበትን ፣ ስኬትን፣ ክብርን፣ ደስታን ፣... በምድራዊነት ሚዛን ብቻ፤

2. እስላማዊ ሉዓላዊነት - Islamic world የመመስረት

3. ክርስቲያናዊ ሉዓላዊነት - “እንግዲህ ሂዱና አህዛብን ሁሉ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ ደቀ መዛሙርቴ አድርጓቸው” ማቴ 28፥19 በሚለው የክርስቶስ ሕያው ቃልና ትዕዛዝ መሰረትነት ላይ የቆመ !

ሉዓላዊነትን ለማስፋፋት የሚያስችሉ መንገዶች እንዳሉ ግልፅ ነው ይህም ፦
የት/ምት ካሪኩለም ይዘት ፣ መንግስት ሥርዓት ፣ የቴክኒዮሎጅ ውጤት የሆኑ መገናኛ ብዙኃንና socila media ፣ የህግና የአስተዳደር መርህ ፣ ወዘተ ጥቂቶች ናቸው። የምትማረው ትምህርት ፣ የሚመራህ መንግስትና የሚያስተዳድርህ መንግስት የምታዳምጠው የመገናኛ ብዙኃን ደስታን የሚተረጉምበት ስኬትን የሚረዳበት ፣ ውቡትን የሚያይበት ፣ ሰውነትን የሚተረጉምበት እሳቤ ፥ የየትኛውን ማዕቀፍ እሳቤ እንዲመራና እንዲያሸንፍ የሚተጋ ነው ብለህ ጠይቅ።

እንግዲህ የእኔና ያንተ ሕይወትስ ወደ የትኛው ያዘመመ ነው ፣ በርግጥም ለየትኛው እሳቤ ጉልበት እየሆነና እያገዘ ነው ትላለህ? ራሳችንን እንጠይቅ ። ከዓለማዊነት እሳቤ ጎን እያቀነቀንን እና ይህንኑ እየተጋትን በዚህ እሳቤ ሰክረን ክርስቲያናዊ ሉላዊነትን ለማምጣት ሰርተንም ሆነ አስበን ሳናውቅ ቁጭ ብለን ሉላዊነትን መርገም የቆሙበትን መሰረት አለማወቅና ስንፍና ነው ብዬ አስባለሁ።

እውነት ነው በአሁኑ ሰዓት በዓለማዊ ሉላዊነት ምክንያት እጅግ ብዙ ሃይማኖታዊ ተፅዕኖዎች እየደረሱ ይገኛሉ። ለዚህ ደግሞ መፍትሄው ጨለማን መርገም ሳይሆን ጥቂት ሻማ ማብራት ነው። ቀድሞ እንደተነጋገርነው ፤ ዓለማዊ ሉላዊነት የተስፋፋውና ሚዛንና ጉልበት ያገኘው በእነዚሁ መንገድ ከሆነ መፍትሄው እሾህን በእሾህ ነው እልሃለሁ። ይህም የትውልድን ዓይንና ጆሮ በዓለማዊነትና በምድራዊነት የሀሳብ አዙሪት የያዘ ፥ ያደነቆረ ፤ ልብ ያስሸፈተ ፣ ኅሊና ያሰከረውን ሚዲያ የትውልድን ሕዋስ ፣ልብ ፣ ኅሊና ...በተቀደሰ አኗኗርና በደረጀ ሥልጡን እሳቤ የሚቃኝ የሚሞላ የብዙ ብዙ ባለ አማራጭ ሚድያ ገንዘብ ማድረግ መቻል ነው። የትምህርት ካሪኩለምና የህግ ስርዓትንም እንዲሁ በተመሳሳይ።

ይቀጥላል .....!
378 views07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-04 07:42:18 ዘመናዊነት ና መንፈሳዊነት !

ክፍል - 1

ዘመን ስንል የሚቆጠርና የሚለካ ጊዜን የሚያጠይቅ ነው። ዘመናዊነት ስንል ደግሞ በዚያ በሚለካና በሚቆጠር ፥ ይህ ተብሉ ሊጠቆም በሚችል ጊዜ ውስጥ ያለ የማ/ሰብን አዕምሮ የተቆጣጠረ እሳቤ ፣ አኗኗር ፣ ግኝት ፣ ... ተጠቃሚነት አሳቢነትና ተጋሪነትን የሚያሳይ ነው። ለምሳሌ የአዳምና ሄዋን በገነት መኖር ና የአኗኗር መንገድ በአዕምሮአቸው የነበረው ሃሳብ በዘመኑ የነበረና አዲስ ተወዳጅ አዕምሮን የሚቆጣጠር ሃሳብ ነበር።

ስለዚህም ዘመናዊነት በዚያን ጊዜ በገነት ውስጥ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ መኖርና ገነትን ማበጃጀት ነበር። በዘመኑ የብርሃን ልብስን ለብሶ ተጎናፅፎ መኖር ዘመናዊ አለባበስ ዘመናዊነት ነበር። ሰይጣን በእባብ አምሳል ሆኖ በተናገረው መሰረት ደግሞ አምላክ ለመሆን ዕፀ በለስን መብላት ዘመናዊ ሃሳብ የነበረበት ቅፅበት ነበር ፣ ይህንን ተከትሎ ከእውቀት ስለ መጉደል ከእግዚአብሔር ለመሸሸግ ከእግዚአብሔር ፊት መሸሸግ የቆይታ ጊዜው አጭር ቢሆንም አዕምሮን የሚቆጣጠር የዘመኑ እሳቤ ነበር።

በዚህ ጊዜ የዘመናዊ አለባበስ ትርጉም ደግሞ ቅጠልን ማገልደም ሆኖ እናገኘዋለን። ንስሐ ፣ ለእግዚአብሔር ንጹህ መስዋዕት ማቅረብ ፣ ራስን ለእግዚአብሔር መለየት ፣ መገረዝ ፣ ታቦተ ጽዮንን ማክበርና ማገልገል ፣ ነብያትን መከተል ፣ የማ/ሰቡን እሳቤ ለዘመናት የተቆጣጠረበትን እሳቤ እናስተውላለን። በዘመኑ የነበረ ዘመናዊነትና ዘመናዊ ሀሳብ ይህ ነበር ማለት ነው። ጣኦት የተመለከበት፣ ሟርትና ጥንቆላ የጎለመሰበት ዘመን ነበር። በዘመኑ ይህ አዲስ ሀሳብ ዘመናዊ ሀሳብ ነበር። በዮሐንስ እጅ መጠመቅ ፣ ክርስቶስን መከተል ና በእሱ እጆች መፈወስ ከእርሱ በረከት መጥገብ ዘመናዊ ሃሳብ የነበረበት ሀሳብ ነበር። ክርስቲያኖችን ማሳደድ እንደ ዘመናዊ ሃሳብ የተወሰደበት ጊዜም በተመሳሳይ። አርዮሳዊነትም በተመሳሳይ። ... ዘመናዊነት የቆየ ሁሉ የሚያረጅበት ፥ አዲስ ነገር ሁሉ የተሻለ ነው ብሎ የሚያቀነቅኑበት ፥ የትውልድን አዕምሮ የሚቆጣጠር እሳቤ ነው።

መንፈሳዊነት ስንል ደግሞ የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ የሚመራውና እንደ እግዚአብሔር ሃሳብ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሚመሩትን ሕይወት የሚናገር ነው። ይህም የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ መፍሰሻ የሚሆን ና የመንፈስ ፍሬዎችን የሚያዘምሩበት የሕይዎት ጉዞ ነው። እግዚአብሔር አንድ ነው ፣ እግዚአብሔር ለዘለዓለም አይለወጥም ፣ የእግዚአብሔር ሃሳብ ና ትዕዛዛቱም በተመሳሳይ። ከትምህርተ ሃይማኖት አንፃርም ስንመለከት እንዲሁ። ተመልከት ወዳጄ ይሁዳን ቆም ብለህ አድምጠው “አንድ ጊዜ ለቅዱሳን ፈጽማ ስለተሰጠች ሃይማኖት” ሲል ትሰማዋለህ።

መንፈሳዊነት ለቅዱሳን አንድ ጊዜ በተሰጠች ፍፅምት ሃይማኖት ውስጥ ሆነህ ፤ ለፍፁምነት የምትተጋበትና እኔ ቅዱስ እንደ ሆንኩ ቅዱሳን ሁኑ የሚል የሕይዎት ቃልን ከፊት ለፊትህ የሚፈልግ አስቀምጠህ የምትጓዝበት ሕይወት ነው። ፍጽምት በሆነችዋ ሃይማኖት ውስጥ ለፍፁምነት የምትጋደልበት የሕይዎት መንገድ። ፍጹም የሆነ ነገር ደግሞ መታደስም መለዋወጥም አይስማማውም። ስለዚህም ሃይማኖትና መንፈሳዊነት አዲስነትና መታደስ ሳይሆን ፤ ሕይዎትን የሚያድስና የሚታደሱበት ስጦታ ነው። የቆየ ሁሉ የሚያረጅ የሚሆነው የሚለወጥና የሚያረጅ ፍጥረታዊ መሰረት ሲኖረው ነው።የማይለወጥ አምላክ ፈፅሞ የሰጠንና አንዲት ማለት ግን በፍጹምነት እና በአሀቲ ህላዌ ጸንቶ መኖርን የሚያጠይቅ ነው።

ተመልከት ወዳጀ ማንም ቅዱስ ማንም ሊቅ በየትኛውም ዘመን ቢነሳ ፥ በቤተክርስቲያን አስተምህሮ ላይ አዲስ ነገር ያመነጨና የጨመረ አይምሰልህ ፤ ይልቁንም የነበረውን ነገር ግን ያልተገለጠውንና ሰዎች ቀድመው ያልተረዱትን የቤተክርስቲያን ትምህርት ለሰወች የገለጠ ና ሰዎች ሊረዱት በሚችሉት ልክ የረቀቀውን አጉልቶ ያስረዳ እንጅ። ስለዚህም ኦርቶዶክሳዊነት በየዘመኑ የተነሱ ሰዎች አዲስ የራሳቸውን የግል ሃሳብና እውቀት እየጨመሩባት እዚህ የደረሰች አይደለችም ። ይልቁንም በተገለጠላቸው ልክ በየዘመኑ ሲረዷት የኖሯት አሁንም ድረስ ቢሆን ለመዳን ያክል እንጅ ሙሉ በሙሉ ያልተረዳናት በጸጋ ብዛት ስንረዳትና ስናጣጣማት የምንኖር እንጅ። ስለዚህም መንፈሳዊ ሕይዎትና ዘመናዊነትን የምናይበት እይታ በዚህ ሃሳብ ዙርያ የሚሽከረከሩና የተዘወተሩ አንዳንድ ቃላትንና ሀሳቦችን እናንሳ። ሥልጣኔ ፣ ሉላዊነት ፣ ዓለማዊነት ፣ ዘመናዊነት ! እነዚህን ሃሳቦች በኦርቶዶክሳዊ መነፅር በጥቂቱ ለመመልከት እንሞክር። በደንብ አስተውል።

ሥልጣኔ ፥ ሥሉጥ ፥ ስንል የስራ ክንውንን በተቀላጠፈና እጅግ በላቀ ፥ ቀላል በሆነ መልኩ ለመከወን የሚያስችል ጥበብን ገንዘብ ማድረግ ማለት ነው። ምናልባትም በሰለጠኑት ዓለማት ሲባል ሰምተን ይሆናል። በዚህም አንዳንዶቻችን መሰልጠን ማለት ምዕራባዊያን የሆኑትን መስሎ መገኘት የሚመስለን አለን። በዚህም ለሃይማኖቱ ከፍተኛ ቦታ ለሚሰጥ ፣ ወግ ባህልን ለሚጠብቅና ባህሉን የሚያከብር ወንድማችንንና እናት አባቶቻችንን ያልገባቸው ያልሰለጠኑ ኋላ ቀር እያልን ስንተች እንደመጣለን።

አለማወቅ ብዙ ደግሞም እንደ ልብ ያናግራል። ምዕራባውያን የሰለጠኑ ያስባላቸው ፤ አምላክ የለም ማለታቸው ፣ ግብረ ሰዶማዊነት ፣ራቁትነት ፣ ግለኝነት ፣ አይደለም። ይልቁንም ሕይዎታቸውን ብቻም ሳይሆን ህይወታችንን በተሳለጠ መልኩ ለመምራት ያፈለቁት ልዑ ል ጥበብ ያገኙት አዲስ የስራ ስነ ዘዴ እንጅ። በእግር በመሄድ ፥ ዓመታትን የሚፈጅብን መንገድ በአውሮፕላን የሰዓታት ጉዞ ማድረግ ሥሉጥነት ነው።

ሌሎች የቴክኒዮሎጅ ውጤቶችና፥ የህክምናው ዓለም ግኝቶችና የመሳሰሉት ሁሉ ለዓለማዊና ለመንፈሳዊ ክንውኖቻችን ልንሰጠው የነበርንን ጊዜ እና ልናፈስሰው የነበረውን ጊዜ በእጅጉ ቀንሰውልናል። ሥሉጥእሳቤ ይሉሃል ይህ ነው። ደግሞ መኖርና መምሰል የተለያዩ ነገሮች ናቸው። የሰለጠኑ ሃገራትን የስራ ባህል ፣ የጊዜ አጠቃቀም ፣ አዲስ ነገርን የማግኘት ልዩ ትጋት ፣ ... አሽቀንጥረህ ትተህ ። የእነርሱን ስም ካልተሰየምኩበት ፣ የለበሱትን ካልለበስኩ ፣ የተመገቡትን ካልተመገብኩ ፣ ከአስተሳሰባቸውና ስራቸው ውጭ ያለውን የእነርሱን ውጫዊ መገለጫ ብቻ የኔ ካላደረግሁ ብሎ ያዙኝ ልቀቁኝ ከማለት የበለጠ የአስተሳሰብ ድህነት አለ ብየ አላስብም። አብነት የምናደርጋቸው ፥ ምዕራባውያንን የሚዎክሉ መስለው እኛን ለማደንዘዝና ተወዳዳሪ እንዳንሆን ለማምከን ታስቦ ፥ የሙዚቃውንና የፊልሙን ኢንዱስትሪ ተቆጣጥረው በሚገለጡልን ጥቂቶች መሆኑ ይገርማል። እነዚህ አካላት የምዕራባዊያን የስይጣኔ እንጅ ፥ የሥልጣኔ ማርሽ ዘዋሪዎች አይደሉም።

“Westernization is not Civilization” ሳይሆኑ በመምሰል አባዜ የምዕራባውያንን ሱሰኝነትና ድንዛዜ ፥ የአዝጋሚ ለውጥ አዝጋሚ ሽባ እሳቤ ካልተጋትኩ ማለትን ብቻ ከሚያቀነቅን ምስኪን የበለጠ ሊታዘንለት የሚገባ ሰው አለ ብዬ አላስብም።

ይቀጥላል .....
549 views04:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 20:34:20 መርጠህ እይ እንዳትሞት !

ሁላችንም የምንበላውን ምግብ፣ የምንጠጣውን መጠጥ ንፅህና ያስጨንቀናል። መቼም የተበላሸ ምግብ መብላት የሚፈልግ ሰው የለም ቆሻሻ ውሀ መጠጣትም እንደዛው። ታድያ ለምን የምናየውንስ አንመርጥም?

ዛሬ ስለምን እንድንወያይ ፈለኩ መሠላችሁ ስለ ፖርኖግራፊ(ትዕይንተ ዝሙት) ፖርኖግራፊ ምንድን ለምትሉ እንግዲህ ሩክቤ ስጋ የሚፈፅሙ ሰዎችን በግልፅ የሚያሳይ ምስል፣ ቪዲዮ ወይም ፅሁፍ ሊሆን ይችላል።

በፖርኖግራፊ ሱስ ወጣቶቿ ከተጠቁባት ሀገሮች ውስጥ አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗን ብነግራቹ ምን ይሰማችኋል አዎ የ Google መረጃ እንዳሳወቀው እንግዲህ ኢንተርኔት ላይ ገብቶ ብዙ ሰው ሰርች የሚያደርገው የ sex video ነው።

እዚህ ሱስ ውስጥ ከመግባታችን በፊት መጀመርያ እንዲሁ እንደ አጋጣሚ አይተንው ሊሆን ይችላል ማለት ድንገት Fb ላይ ሊሆን ይችላል ወይ የሆነ ሰው ስልክ Gallery ገብተን ስናይ ይሆናል ያኔ ወድያው ልናልፈው ይገባል። "ኧረ ምን ጉድ ነው እስኪ ሌላም ልይ" ምናምን ምናምን እያልክ አትመልከት አይጠቅምህም ይገልሀል መርዝ ነው።

አንዴ እዚህ ኀጢአት ውስጥ ግባለት እንጂ ሰይጣን ይጫወትብሀል። መጀመርያ ቀለል አድርጎ ፈታ በል፣ ይሄ ኖርማል ነገር ነው፣ ሁሉም የሚያየው ነው ብዙ ብዙ ይልሀል ከዛ ኀጢአቱ ውስጥ ገብተህ ማጣጣም ስትጀመር እራስህን እንድትጠላ ያደርግሀል፣ ኢየሱስ አይወድህም የሚል ድምፅ በህሊናህ ይነግርሀል፣ ፀሎት ልትፀልይ ስትነሳ የምታደርገውን ኀጢአት እረሳኸው እንዴ ይሄን ቅዱስ ቃል ልትፀልይ አይገባም እጅህ ቆሻሻ ነው ርካሽ ነህ ይልሀል ከዛ ተስፋ ትቆርጣለህ ወደ ረከሰ ኀጢአት ከፍ ከፍ ትላለህ ልክ ማስተርቤሽን (ሴጋ) መፈፀም ትጀምራለህ ፣የሩካቤ ስጋ መሻትህ ይቀጣጠላል ግን መቼም አትረካም፣ ብዙ ሴቶች ጋ ትዘሙታለህ ብዙ ብዙ....... የብዙዎቹ *ልጆቻቸውን የሚደፍሩ አባቶች *ህፃንም ሆነች ትልቅ ሴቶችን የሚደፍሩ ኧረ ህፃናት ወንድሞቻችንም ላይ ይህ እየተፈፀመ ነው *የግብረሰዶማውያን የጀርባ ታሪክ ይኸው ሱስ ነው።

በፖርኖግራፊ የተጠቃ ሰው እንዲህ አይነቱን የረከሰ ምስል በቃ ልክ እንደ ኖርማል ደስ የሚል ፊልም ነው የሚያየው ይህን ሳያይ ከዋለ በቃ በህይወቱ ወሳኝ የሆነ ነገር ሳያደርግ የዋለ ያክል ይሰማዋል ይቅበዘበዛል በቀን በቀን ይህን ሳያይ አይውልም አያድርም።

እህቴ ምን አልባት እዚህ ኀጢአት ውስጥ አልገባሽ ይሆናል ግን ብርሀነ አለም ጳውሎስ የቆምሽ ቢመስልሽ እንዳትወድቂ መጠንቀቅ እንዳለብሽ ተጠንቀቂ ይልሻል ወንድሜ አንተም እዚህ ሱስ አልገባህ ይሆናል ተጠንቀቅ ባይ ባላይ ምንም አይመስለኝ አልወድቅም አትበል አይቼ ሰምቼ እችላለሁ አትበል ይልሀል መፀሀፈ መነኮሳት።

ስለዚህ የምንመለከታትን እያንዳንዷ ነገር ልንመርጥ ይገባል ከትንንሽ ነገሮች እንጀምር የምናየው አለማዊ ፊልም ላይ ምንድን ነው የምናየው? ከንፈራቸውን የሚሳሳሙ ሰዎች? መዳራትን አይነት ነገር የሚያሳይ ምስል የለውም? የምናዳምጠው ዘፈንስ ቢሆን ኧ መተው የለብንም?

የምናነባቸው ፅሁፎችስ ወሲብ ቀስቃሽ አይደሉም? ደግሞ በዚህ ሱስ የመጠቃት ነገር ከ 11 አመት ጀምሮ እንደመሆኑ ታናናሽ ወንድሞቻችን፣ እህቾቻችንንም ልንጠብቅ ይገባል። ትናንሽ ቀበሮዎችን እናጥምድ ሰይጣን ትልቅ ኀጢአት ውስጥ ሊከተን ሲፈልግ ከትንሹ ነው የሚያሰጀምረን ልንነቃ ይገባል።

እዚህ ሱስ ውስጥ የገባን ሰዎች ጌታ አይወድህም የሚለውን ድምፅ አልቀበልህም ጌታ ይወደኛል ኀጢአቴን አንጂ እኔን አልጠላኝም እንበል። ልትፀልዩ አይገባችሁም ሲለን አንስማው አንተን የማሸንፍህ በፀሎት ከጌታዬ ጋር ስገናኝ ነው እንበለው። ሰይጣን ሰው ብትገል፣ ብትዘሙት ምንም ብታደርግ አይረካም እሱ የሚፈልገው እራስህን ጠልተህ ተስፋ እንድትቆርጥ ነው። ተስፋ ካልቆረጥክ ንስሀ ገብተህ ይቅር እንደምትባል ያቃል።

ስለዚህ ተስፋ አትቁረጥ ምንም ኀጢአቱ ውስጥ ጠልቀን ብንገባ ጌታ ኃይል ይሰጠናል ምን ይሳነዋልና እርሱ ጌታ ዝሙተኛ የነበረችው እናታችን ግብፃዊቷን ማርያምን ከኃጢአት የምትወጣበትን አቅም ሰጥቶ 47 አመት በበረሀ እንድትኖር የረዳ ጌታ ምን ይሳነዋል? ለኛ ምንም ጣፍጭ የሆነ ኃጢአት ቢኖር ተስፍ ሳንቆርጥ እኛ ወደ ክርስቶስ እንመለስ እንጂ ኃጢአትን የምንጠላበትን አቅም ይሰጠናል።

የምንመለከተውን፣ የምናዳምጠውን ሁሉንም እንምረጥ።

ወስብሀት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን።
472 views17:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ