አታውቅም """"""""""""" በሰፈሯ በኩል ስንት ጊዜ እንዳለፍኩ ፣ እሷን ለማናገር እንደተሸማቀቅኩ ፣ በሀሳቤ መሀል እንዳመላለስኳት ፣ በማየው ሁሉ ላይ ሺ ጊዜ እንደሳልኳት ። አታውቅም እሷን በማስታወስ ቀኔ እንደሚጀምር ፣ ባገኛት እያልኩኝ ሌቱን እንደማድር ፣ ቀኑ እንደሚረዝም ሳላያት ከዋልኩኝ ፣ ልነግራት አስቤ ስንቴ እንደፈራሁኝ ። አታውቅም አታውቅም አታውቅም ፣ ምናልባት አንድ ቀን እነግራት ይሆናል በሚል ተስፋ እንደቆምኩ ፣ ናፍቆቷን ስመገብ እህል ሁሉ እንዳቆምኩ ፣ መንገድ ስንገናኝ ብርድ እንዳለበት ሰው አካሌ እንደሚርድ ፣ ይሄን ሁሉ ተዐምር አታውቅም የኔ ውድ ። አታውቅም አታውቅም እንደተሸከምኩኝ የሷን ፍቅር ስቃይ ፣ ሁሌ ተደብቄ ስትስቅ እንደማይ ፣ በፍቅሯ ታምሜ ከህመሜ አልድንም ፣ ምን ብላ ታክመኝ ህመሜን አታውቅም ። @sumi_ya 18 viewsMIA , edited 12:19