Get Mystery Box with random crypto!

ትናት በምስራቅ ወለጋ ነቀምት ከተማ ላይ ምንም የማያቁ የአማራን ልጆች ፋኖን ትረዳላችሁ ብሎ የኦ | Suleiman Abdella ሱሌማን አብደላ

ትናት በምስራቅ ወለጋ ነቀምት ከተማ ላይ ምንም የማያቁ የአማራን ልጆች ፋኖን ትረዳላችሁ ብሎ
የኦሮሚያ ክልል ልዮ ሀይል የፊጥኝ እመኪና ላይ አስሮ እየደበደበ አይለመደን በሉ እያለ ከተማዋን ሁሉ ሲያዞራቸው የዋሉት አማሮች እነዚህ ናቸው። ለሰርቶ ማሳያ የተሰራን እንጨት አሸክሞ የነቀምት ከተማን ህዝብ ሰብስቦ አማሮች እየተባሉ እፊታቸው ላይ ምራቅ ሲተፋባቸው ያየ አንድ መምህር ቀድሞ ነበር መረጃውን የሰጠኝ።

ልጆቹን ለመረሸን ሲሞክሩ አይሆንም ፎቷቸው ስለተያዘ እሚዲያ ላይ መረጃው ሊወጣ ይችላል ብለው ነው የተዋቸው። በተያያዘ ዜና ሻንብ ላይ የኦሮሚያ ልዮ ሀይል ህዝቡና ሽማግሌዎችን ሰብስቦ ከቱሉ ጋና እስከ ወባንጭ ድረስ ያለውን አማራ ለማፅዳት ሲመክር ውሏል። ወለጋ ላይ ያለው ደመና በህዝባችን ላይ ዳግም ሊወርድ ደም የለመደው አጉሪው ሀይል እያጉረመረመ ይገኛል። አብይ አህመድ እጅግ አደገኛ በሆነ መንገድ ይሄንን ህዝብ ሊያስጨፈጭፈው ጀሌዎቹን ልኮ እያዘጋጃቸው ነው።

ከሦስት ቀን በፊት አውራ ጎዳናን መከላከያ ተብየው አማራን አፅድቶና ዘርፎ ( ገድሎ) ካለስቀቀ ቡኋላ ለኦሆዴድ አስረክቧል። 5ሺ አባወራዎችን አፈናቅለው 31 ንፁሀንን ጨፍጭፈው ነው ነው አውራ ጎዳናን ከአማራ አስለቅቀው ለኦሆዴድ ያስረከቧት።

የተጀመረው ትግል እየተቀጣጠለ በሚኒሊክ ቤተ መንግስት የተቀመጠውን አሸባሪ ቡድን ማፍረክረክ ሲጀምረው መደበቂያውን ኦሮሞን ከአማራ ማጨፋጨፍ እንደሚሆን ቀድሞ የታወቀ ቢሆንም ማለቅ ካለብን ጠቅላላ እናልቃታለን እንጅ በቀላሉ እንደማንለቃቸው ያቃሉ። ይሄ ስረአት እጅግ በደም የተጨማለቀ ማወቅ የለለው በጦርነት መኖር የሚፈልግ ስረአት እንደሆነ እነ አሜሪካ ቀድመው ተናግረዋል።

Suleiman Abdella ሱሌማን አብደላ

ቴሌግራም https://t.me/SuleimanAbdellaNews