Get Mystery Box with random crypto!

በጠንካራ የአማራ ጀኔራሎች ላይ እየተሰራ ያለውን ሴራ ተመልከቱ 1. ሌተናል ጀኔራል_በላይ_ስዩ | Suleiman Abdella ሱሌማን አብደላ

በጠንካራ የአማራ ጀኔራሎች ላይ እየተሰራ ያለውን ሴራ ተመልከቱ

1. ሌተናል ጀኔራል_በላይ_ስዩም ስንቱን ጦርነት ተሸክሞ ኖሮ ከድል በሗላ ለምን ከምስራቅ ዕዝ አዛዥነቱ ተነስቶ አዲስ አበባ ውስጥ በር ተዘግቶበት እንዲውል ተደረገ?

2. ወያኔ ደብረ ብርሃን ደርሳ አገር በተጨነቀችበት ወቅት ኮማዶውንና እግረኛውን አጣምሮ አዋግቶ ታሪክ የቀየረው ሌተናል ጀኔራል ዘውዱ በላይ ለምን ከአማራ ክልል አስወጥተው ወለጋ ላይ እንዳይንቀሳቀስ አስረው አስቀመጡት? ማዕከላዊ ዕዝ መሆን ያለበት ወለጋ ወይስ መካከለኛው ኢትዮጵያ?

3. ሌተናል ጀኔራል አሰፋ ቸኮልን ለምን ከራያ ግንባር አሰውጥተው ሌላ ዕዝ ቦታውን መጥቶ እንዲረከበው ሰሞኑን ተወሰነ? በራያ ግንባር ሰፍሮ የሚገኘው የሌተናል ጀኔራል አሰፋ ቸኮል ጦር በሌላ ዕዝ እንዲተካ ተወስኗል, ለምን?

4. እውቁ የጦር ገበሬና የወልቃይት ግንባርን አዋግቶ ታሪክ የሰራው የ7ኛ ዕዝ አዛዥና ከእነ ኮሎኔል ደመቀ ጋር እጅግ ምርጥ ግንኙነት የነበረው ሌተናል ጀኔራል ደሳለኝ ተሾመ ይመራው የነበረው የ7ኛው ዕዝ እንዲፈርስ ተደርጎ ዋና አዛዡ ሌተናል ጀኔራል ደሳለኝ ተሾመ ለምን ወታደራዊ አታሸ ትሆናለህ ተብሎ አሁን ያለ ስራ ተቀመጠ?

ጀግና የአማራ ጀኔራሎች እጃቸው ታስሯል ወይም አምባሳደር ወይም ወታደራዊ አታሸ ተብለው ከጥቅም ውጭ ሆነዋል።

መረጃው የወታደር ጌትነት ይስማው ነው

Gionamhara

#IAmFano #VoAS
#WarOnAmhara
#AmharaGenocide
#AmharaWillPrevail
#AmharaResistance
#AmharaUnderAttack
#FreeAmharaDetainees