Get Mystery Box with random crypto!

ዓባይ ከፍክክር ወደ ምክክር ጉዞ ጀምሯል። ዓባይ መልኩም፣ ግብሩም፣ ታሪኩም ተቀይሯል። 85 | Suleiman Abdella ሱሌማን አብደላ

ዓባይ ከፍክክር ወደ ምክክር ጉዞ ጀምሯል።




ዓባይ መልኩም፣ ግብሩም፣ ታሪኩም ተቀይሯል። 85% የውሻ ድርሻን በማበርከት የታችኞቹ ተፋሰስ ሀገራት በዓባይ ውሃ የዘመናት መናን ይመገቡ ዘንድ ምክንያት የሆነችው ኢትዮጵያ ዛሬም አዲስ ተስፋና ጸጋን አምጥታለች።

በዓባይ ውሃ ላይ የታላቁ ህዳሴ ግድብን በመገደብ የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት ለኢኮኖሚ እድገታቸው እጅግ አስፈላጊ የሆነውን የሃይል ምንጭ እንዲያገኙ ማድረግ ጀምራለች። ብቻችን እንብላው የሚሉት የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ግብጽና ሱዳን ጥቅማቸው ሳይነካ ተጨመሪ የሀይል ምንጭ የሚያገኙበት ሌላኛው ምዕራፍም ተከፍቷል።

ኢትዮጵያ ለዓባይ ተፋሰስ ሀገራት ተስፋ መሆኗን ቀጥላለች። የዓባይ ውሃ ዓለም እንደፈራው የስጋት ሳይሆን የእድገት ተምሳሌት፣ የሰላምና አብሮነት ውል ማሰሪያ ቀበቶ ለመሆን የሚያስችለው ደረጃ ላይ ደርሷል። ኢትዮጵያ በዓባይ ውሃ ላይ ያላትን አቋም በበሳል ዲፕሎማሲ ስታስኬድ ቆይታ ዛሬ ላይ የመጀመሪያውን የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት የምክክር ጉባኤ መጀመር መቻሏ ግሩም ነው። ይህ ታሪካዊ ጉባኤ እንዲካሄድ ጥረት ያደረጉት የዘርፉ ምሁራንም ለብርሃን ቴሌቪዥን ይህንን አስመልክቶ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።

#BTV_ብርሃን_ቴሌቪዥን የሀገርን ሰላም፣ እድገት፣ አንድነት የሚያጠናክሩ ርዕሰ ጉዳዮችን በበሳል ባለሙያዎቹ አሰናድቶ ለማቅረብ በሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን የተመሰረተ የሚዲያ ተቋም ነው።

#BTV_የብርሃን_ቴሌቪዥን ቻናሎችን ሰብስክራይቭ በማድረግ ቤተሰብ ይሆኑ ዘንድ ተጋብዘዋል።

BTV - ብርሃን ቴሌቪዥን
#ለወቅታዊ፣ ዕለታዊና ትክክለኛ መረጃዎች
Join our #TelegramChannel
https://t.me/BTV_BerhanTelevision
#TelegramGroup
https://lnkd.in/euXpbguE
Subscribe our #YouTube Channel
https://www.youtube.com/c/BTVEntertainment-BTV-Official



Like us on #Facebook
https://lnkd.in/euuPKVeb
Follow us on #LinkedIn
https://lnkd.in/gubbmmhG