በመምጣትሽ ማግስት.. ጥቁር የነበረ ፡ ጸሊም እልፍኝ ደምቆ ፡ ውበትን ለበሰ ያ‘ነደደኝ ሀዘን ዋይታ ቀን ጎድሎበት ፡ በሳቅ ተጠበሰ : : እንባ ሰቀቀኔ የቀን ሌት ለቅሶዬ ፡ በሳቄ ተረታ ሽምድምድ ጉልበቶ ፡ በፍቅርሽ በረታ ዝል ነፍሴ ጸናልኝ ፡ ጀገነልኝ ልቤ ጥዩፍ ያሉት ሁሉ ፡ ተዋበ ለቀልቤ !! : : አማርኩኝ ተዋብኩኝ ፡ በጠይም ውስጠትሽ ፡ በነፍስሽ ደመቅኩኝ ገዘፍኩኝ ከበርኩኝ ፡ በወዛም መውደድሽ ፡በፍቅርሽ ሰው ሆንኩኝ ፡ መገን መገን አጀብ ! ልኬ ላቀ አጀብ !! ክብሬ ጎላ ፡ ተ......ቀ በብዙ ለካስ ፍቅር ኖሯል ፡ ሰው የመሆ ን ወዙ !! **//* [ ዳግም ሔራን ] Join and share....... @heranawi @heranawi @heranawi 386 viewsሔራ…ቶ…ዳግ, 17:02