Get Mystery Box with random crypto!

ዛሬ በማለዳ ስትነቃ የጠዋቱን ብርሀን አይኖችክ ተከፍተው መመልከት ሲቻላቸው ጆሮዎችክ የአካባቢውን | FAITH HOPE LOVE

ዛሬ በማለዳ ስትነቃ የጠዋቱን ብርሀን አይኖችክ ተከፍተው መመልከት ሲቻላቸው ጆሮዎችክ የአካባቢውን ድምጽ ሲያቀብሉክ የማለዳውን አየር ያለ ማንም ከልካይነት ስትምግ ልብክ በአግባቡ እየመታ የደም ዝውውርክን ሲቆጣጠር እጆችክ ሲወዛወዙ እግሮችክ ለመራመድ ሲንቀሳቀሱ የሆድእቃክ እንኳን ማታ የሰጠከውን ስራ አጠናቆ በጠዋቱ አምጣ እያለ ሲሞረሙርክ ኩላሊትክ በአግባቡ አጣርቶ ከመኝታክ ተነስተክ መፀዳጃ ቤት ስትገባ አእምሮህ ምን እያደረክ እንደሆነ በአግባቡ ሲተረጉምልክ ለቀጣዩ ዉሎክ እቅድና ኘሮግራም ስታወጣ... አስበከዋል ምን ያክል ብዙ ምህረት ፣ እድል ፣ተስፋ እና አዲስ ጅማሬ በማለዳ እንደተሰጠክ ? ትላንት የነበረው ችግር ፣ሐዘን አልተቀየረም ይሆናል ነገር ግን ትላንት ከፈጣሪ የተቸርካቸው የማይቆሩ የማይዳሰሱ እንዲሁም የሚታዩ አካላዊ የሚዳሱ ስጦታዎች አልተቀነሱብክም ክፍያን አልተጠየክባቸውም እና ወዳጄ ዛሬን በምስጋና ጀምረክ ለድልክ መንደርደሪያ ቀንክን ዛሬ እንደሆነች አስብ ያለ ምክንያት ዛሬን እንድታይ አልተፈቀደልክም ነገ በ ድል የምትቆመው አሸናፊው አንተ ነክ ዛሬን አምላክህን በማመስገን ችግሮችና ውድቀቶችክን መማሪያ እንጂ መማረሪያ እንዳልሆነ አምኖ በመቀበል ጀምር ለነገክ ተስፋክን በእምነት ጀምር በፍቅር ስራ

በዚህ ይቀላቀላሉ @stay1stronger

እንማራለን እንማማራለን እንወያያለን