Get Mystery Box with random crypto!

እጅህ(2*) ከመሥራት አላጠረችም ጆሮህም ከመስማት አልደከመችም ፍርድ ከኛ ርቋል ሃሣባችን በደል ሆ | Spritual Quotation📖

እጅህ(2*) ከመሥራት አላጠረችም
ጆሮህም ከመስማት አልደከመችም
ፍርድ ከኛ ርቋል ሃሣባችን በደል ሆኗል
መዳን ከኛ ርቋል ዓመፃችን ፊትህ በዝቷል
ብቻ ማረን ይቅር በለን የሱስ

እውነት በአደባባይ ላይ ወድቋል እንደዋዛ
ፅድቅ በሩቅ ቆሞ ኧረ መግቢያ አጣ
ቅንነት ወደኛ መግባት ተስኖታል
ሐጢአታችን መስክሮብን ይኸው ርቀኸናል

እንለምንሃለን(3) በፊትህ ዝቅ ብለን
እንደሠፉ ወንዞች በግርማህ ከኛ ጋር ሁንና
በምህረትህ እየን በክፋታችን ላይ ራራ
ወደ ደጅ የወጣው ፅድቅ ይመለስልን
የቀድሞው ፍቅራችን እጥፍ ይምጣልን
በዙሪያችን ላሉ እንሁን የህይወት ሽታ
ብርሃናችን እንዲሁ በሰው ፊት ሁሉ ይብራ

ፊትህን ከኛ አትሰውረው
አበሳችንን ክደነው
የነፍሳችን ምኞት ይህ ነው
ባንተ መንገድ መራመድ ነው
ሳያልቅብን ጊዜ ዘመን
እንመለስ እባክህ መልሰን
ይብቃን በቃ ለብ ያለ ህይወት
የማታየው የማትከብርበት
ክብርህ ይደር የሱስ በምድራችን
ክብርህ አይልቀቅ ከሠፈራችን