Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ዉድድር አሸናፊ የነበረዉ ቅዱስ ጊዮርጊስ በዉድድሩ ድንቅ የነበሩ ልጆቹን | ስካይ ስፖርት ET™

በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ዉድድር አሸናፊ የነበረዉ ቅዱስ ጊዮርጊስ በዉድድሩ ድንቅ የነበሩ ልጆቹን ወደ ዋናዉ ቡድን እንዲያድጉ አድርጓል ።

በዉድድሩ እጅግ ማራኪ አቋምን በማሳየት መመረጥ የቻሉት የቡድኑ ተጫዋቾች ሀብቶም ገ/እግዚአብሔር ፣ አቢሰሎም ዘመንፈስ ፣ ሚራጅ ሰፋ ፣ ብሩክ እና ፉኣድ ወደ ዋናዉ ቡድኑ ያደጉ እና በደብረዘይት የሚገኘዉን ዋናዉን ቡድን ተቀላቅለዉ ዝግጅታቸዉን የሚጀምሩ ተጫዋቾች ሆነዋል።

ቡድኑን ከተቀላቀሉ በኋላም ቀናቶች በቀሩት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጫወት እድልን እንደሚያገኙም ሲነገር በቡድኑ ከዚህ ቀደም ያደጉ ተጫዋቾች መኖራቸዉም ይታወቃል።

እድል ከተሰጣቸዉ የሚሰሩትን የሚያዉቁት እነዚህ ታዳጊዎች አቋማቸዉ ምን ይመስላል የሚለዉን ቀናት የቀሩት ፕሪሚየር ሊግ የሚያሳየን ይሆናል።

በደረሰኝ መረጃ ሌሎችም ሊጨመሩ ይችላሉ ፤ ባለፈዉ አመትም ያደጉት አብርሃም ፣ አቤል ፣ ሻይዱ እና አላዛር በቡድኑ ዉስጥ መሆናቸዉም ይታወቃል።

በርቱ

ምንጭ፦ Yonas Amare

@SportEthiopia1 @SportEthiopia1