እለተ አርብ ። በእውነት አብያተክርስቲያናትን ቸሩ ይጠብቅልን በቸርነቱ ይማረን። ✞ እንኩዋን ለዕለተ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንና ለነፍሳተ ብሉይ ዓመታዊ የመታሠቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞ =>ከትንሳኤ ሳምንት ቀናት ይህች ዕለት ቤተ ክርስቲያን አንድም ነፍሳት በመባል ትታወቃለች:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዓለም ሳይፈጠር በአምላክ ልቡና ታስባ : በዓለመ መላእክት ከታየች በኋላ:- ¤አበው ተስፋ ሲያደርጓት ¤ነቢያት ትንቢት ሲናገሩላት ¤ሱባኤ ሲቆጥሩላት ¤ምሳሌም ሲመስሉላት ኑረዋል:: ††† ዘመኑ በደረሰ ጊዜ በአምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ :- ¤በመጸነሱ ተጸንሳ ¤በመወለዱ ተወልዳ ¤በጥበብና በሞገስ አብራው አድጋ ¤በጥምቀቱ ተጠምቃ ¤በትምሕርቱ ጸንታ ¤በደሙ ተቀድሳ ¤በትንሣኤው ከብራ ¤በዕርገቱ ሰማያዊነቷን አጽንታ ¤በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስ ወርዶላት በይፋ ለልጆቿ ተሰጥታለች:: ድንገት የተመሠረተች ሳትሆን ቅድመ ዓለም በአምላክ ልቡና የታሠበች: በዓለመ መላእክት የተወጠነች ናት:: በአማን ጐልታ: ግዘፍ ነስታ የተመሠረተችው ግን በደመ ክርስቶስ ተቀድሳ: በትንሳኤው ከብራ: ንጽሕትና ጽሪት ባደረጋት ጊዜ ነው:: መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ባይነሳ ኖሮ ቤተ ክርስቲያን ሕልውና አይኖራትም ነበርና ይህች ዕለት ቤተ ክርስቲያን ተብላ ትከበራለች:: ነፍሳት =>በብሉይ ኪዳን የነበሩና ለ5,500 ዓመታት በሲዖል የተጋዙ ሰዎችን ያመለክታል:: እነርሱም ከአባታችን አዳም ጀምሮ በዓመተ ኩነኔ የነበሩ ሰዋች ሲሆኑ ደመ ክርስቶስ ቀድሷቸው: የትንሳኤው ብርሃን ደርሷቸው ወደ ገነት ስለ ገቡ በዚሁ ቀን ይታሠባሉ:: =>እግዚአብሔር ከአባቶች ነፍስና ከቅድስት ቤቱ በረከት አይለየን:: =>+" መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ: ተቀበረም:: መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነስቷል... ከዚያም በሁዋላ ለያዕቆብ: ሁዋላም ለሐዋርያት ሁሉ ታየ:: ከሁሉም በሁዋላ እንደ ጭንጋፍ ለምሆን ለእኔ ደግሞ ታየኝ:: እኔ ከሐዋርያት ሁሉ የማንስ ነኝና:: የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ስላሳደድሁ ሐዋርያ ተብየ ልጠራ የማይገባኝ: ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ የሆንሁ እኔ ነኝ:: "+ (1ቆሮ. 15:3-10) > @mekra_abaw #ጸሎት_እያደረግን እርስ በእርሳችን እንጠባበቅ ቤተ-ክርስትያናችን እንጠብቅ፤አከባቢያችን እንጠብቅ ከቻላችሁ ዛሬ አዲስ አበባ ያላችሁ ግርግር በበዛበት፤ረብሻ ባለበት ቦታ አትገኙ አከባቢያችሁ ለሚፈጠሩ ትክክል ያልሆኑ እንቅስቃሴዎችን በመረጃ ያዙ።በቸለልተኝነት አንድም ክርስትያን፤አንድም ቤተ-ክርስትያን ማጣት የለብን። ድንግል ማርያም ከለላትኩነን!!! መልካም ቀን ምክረ አበው 1.5K views06:19