Get Mystery Box with random crypto!

በዕድሜ ትንሹ ዲያቆን ቤተክርስቲያንን አድሱልኝ ይላል! ~~~~~~ Share ማድረግ እንዳንረሳ በ | የደቡብ ኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናን ኅብረት-አርባ ምንጭ⛪️

በዕድሜ ትንሹ ዲያቆን ቤተክርስቲያንን አድሱልኝ ይላል!
~~~~~~
Share ማድረግ እንዳንረሳ

በ5 ዓመት ከ6 ወሩ ማዕረገ ድቁንና የተቀበለው የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን በዕድሜ ትንሹ ዲያቆን ለመጀርያ ጊዜ ሳገኘው "ምን እንደሚፈልግ " ጠየኩት።

እሱም በተኮላተፈ በሚያባባ ንግግር በአፍ መፍቻ የጋሞኛ ቋንቋ "ኑ ቤተክርስቲያን ኦሲሳ" ሲል ልብ በሚያባባ የተማጽኖ ቃል ነገረን ።

ትርጓሜው "ቤተክርስቲያችንን አሰራልን " ማለት ነው።

በእዚህ የጨቅላ ዕድሜው ከእራሱ ከፍ ብሎ እሱን ስላፈራችለት የገጠሪቷ ቅድስት ቤተክርስቲያን ሲያስብ ሳየው ልቤን ረበሸው።

ድንገት ይህን ብርቱ ህፃኑ ወዳፈራችው የቅድስት ኪዳነምህረት መቅደስ ስንገባ ሊወድቅ አንድ ሀሙስ ብቻ የቀረው ነበር። ኮርኒሶቹ እየተራገፉ፣ግድግዳው በምስጥ ያለቅ ነበር።

ዝናብ የዘነበ ዕለት ዲያቆናት ከጣሪያው አልፎ የሚንጠባጠበው ዝናብ ቅዳሴውን እንዳያስተጓጉል ባዝ ይዘው እንደሚጠብቁ ነገሩን ።

የብላቴናውን ተማጽኖም በአከባቢው ያሉ አረጋዊ ሸማግሌ ምዕመናንን የቅድስት ኪዳነምህረትን ስእል አድኖ ይዘው በአከባቢው ባህል መሰረት የተማጽኖ እርጥብ ሳር ይዘው ተማጸኑ።

ቢበዛ በ100 ሺ ብር መታደስ እንደሚችል ገመትን ። ግን ብሩ ከወዴት ይምጣ።

እንግዲህ ለቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች ነን ያላችሁ የቅድስት ኪዳነምህረት መቅደስ ከ10 ብር ጀምሮ አስተዋጽኦ በማድረግ የገጠሪቷን መቅደስ እንድረስላት።

የኢትዮጽያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር

// ኡሞ ላንቴ ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን .....1000494984923 //

ለቁጥጥር ይረዳን ዘንድ የምታስገቡትን የባንክ ስሊፕ በውስጥ መስመር ወይም በኮመንት ሴክሽን ላይ ያስቀምጡልን ።

ለበለጠ መረጃ :- 0918446260 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ!

Kune Demelash kassaye -Arba Minch