Get Mystery Box with random crypto!

,,,,.....ጎዶሎ ፀሎት,,.... ሹፌሩ በጉዞዉ አምላክ እንዲጠብቀዉ፡ ጥቅስ ፃፈና በመኪናዉ ለ | ግጥም#🅢🅞🅛🅐 🇵 🇴 🇪 🇲

,,,,.....ጎዶሎ ፀሎት,,....

ሹፌሩ በጉዞዉ አምላክ እንዲጠብቀዉ፡
ጥቅስ ፃፈና በመኪናዉ ለጠፈዉ፡፡
ያሰበዉ ነገር ጥሩ ሆኖ ሳለ፡
የፅሁፉን መልዕክት ግን አላስተዋለ፡፡
እኔም ቀርቤ ፅሁፉን ሳነበዉ፡
"ጌታ ተከተለኝ" እንደዛ የሚል ነዉ፡፡
ምን አይነት ፀሎት ነዉ?
ጌታም ሰምቶት እሱን ስከተል፡
ቀድሞ ብገባ መኪናዉ ከገደል፡
የማነዉ ስህተቱ
ጌታን አላስቀደመ ከፊቱ
ቅደመኝን ትቶ ተከተለኝ ላለዉ;
ይህ ነዉ ውጤቱ ፀሎት ለማያዉቀዉ፡፡
sola