Get Mystery Box with random crypto!

አጋፔ የመውደድ ምስጢሩ ሲጠና ምክንያቱ ለምን እንዴት ብለን ስንፈልግ በከንቱ እኮ በምን በምክንያት | ስለ ህይወት ቃል... 1ኛ ዮሐንስ 1:1

አጋፔ
የመውደድ ምስጢሩ ሲጠና ምክንያቱ
ለምን እንዴት ብለን ስንፈልግ በከንቱ
እኮ በምን በምክንያት ምንስ አድርገን ነው
በእንዲህ አይነት ፍቅር እኛ የተወደድነው
ስንል ጊዜ ወስደን ከቃሉ ጋር ስናስበው በጥሞና
ነገረን ምክንያቱን የፍቅሩን ጣፋጭ ቃና
ያለ ምንም መስፈርት እንዲሁ በፀጋ
ያላንዳች ክፍያ ወደ እርሱ እንዳስጠጋ
ስንጠላው ወዶ ስንርቀው ቀርቦ
እጅ መንሻ ሳንሰጥ ወይም ደሞ ጉቦ
ያላንዳች መነሻ ያለምንም ምክንያት
ወዶ ነው ያፈቀረን ይሄ መልካም አባት።
በሰውኛ ልማድ ስንዋደድ ሰዎች
ምክንያት እንሻለን ስለሆንን ሞኞች
እርሱ ግና ያለ ሰበብ መልካምነት ሳይገኝብን
ይልቁኑ ጠላቶቹ ሆነን ሳለን ምህረቱ ማይገባን
ወደደን መረጠን ልጆቹ እንድንሆን
አፀደቀን ዋጅቶ በደም ርስቱንም አካፈለን።
አጋፔ የተባለው ይህ የፍቅር ትርጉም
ከእየሱስ ውጪ ከሌላ ከማንም ፈፅሞ አይገኝም!
ነፍሱን ሰቶ ለቤዛነት ለጠላቱ እስከ መሞት
በመስቀል ላይ ተቸንክሮ እስከመሆን ሀጢያት
ይህን ያህል ዋጋ መክፈል ያለ ምክንያት
ከአእምሮ በላይ ነው የአምላካችን ስጦታነት
እራሱ ሰቶናል ምን እንፈልጋለን
ለነፍሳችን ቤዛ ሆኗል ምንስ እንሻለን
አለብን ውለታ የማንከፍለው የፍቅር ዕዳ
ባንከፍልም ይህን ውለታ ልንኖርለት እንሰናዳ።
የፍቅር ማብራሪያ የመውደድ ትርጉም ነህ
ለፍቅርህ መግለጫ ቃላት አጣንልህ!
የመውደድ አውራ የፍቅር ራስ አጋፔ ነህ
ከስጦታዎች ሁሉ የምትልቅ ስጦታ ነህ!!

ይ ላ ሉ
Join now

Group : @slehiywetkal
channel : @slehiywet