Get Mystery Box with random crypto!

ክርስቲያን በዓለም በዚህ ዓለም የሚኖር ክርስቲያን በውቅያኖስ ላይ እንደሚጓዝ መርከብ ነው መርከ | ስለ ህይወት ቃል... 1ኛ ዮሐንስ 1:1

ክርስቲያን በዓለም

በዚህ ዓለም የሚኖር ክርስቲያን በውቅያኖስ ላይ እንደሚጓዝ መርከብ ነው መርከብ ሊሰጥም የሚችለው በራሱ ኃይልና ክብደት ሳይሆን ውኃ ወደ መርከቡ የገባ እንደሆነ ነው ። እውነተኛ ክርስቲያን በዚህ ዓለም በመኖሩ ክርስቶስን በመከተሉ አይወድቅም በአለም ክፋት አይሰምጥም ነገር ግን ዓለም ወደ ልቡ ውስጥ የገባች እንደሆነ ታሰጥመዋለች በሰው ልብ ውስጥ የገባች ዓለም ብዙ ነፍሳትን አስጥማለችና።

ስለዚህ አማኞች ልባቸውን ለዓለም ሙሉ በሙሉ ዝግ ሊያደርጉ ይገባል ፤ በዓለም ሊኖሩ ይችላሉ ፤ ነገር ግን በዓለም ካለው ክፋት ሊጠበቁ ያስፈልጋል ፤ " ከክፉ እንድትጠብቃቸው እንጂ ከዓለም እንድታወጣቸው አልለምንም " የሚለው የኢየሱስ የሊቀካህናትነቱ ጸሎትም የዓለም ክፋት ወደ ውስጣቸው እንዳይገባ ይጠብቃቸዋል ዮሐ.17:15

ይ ላ ሉ
Join now

Group : @slehiywetkal
channel : @slehiywet