Get Mystery Box with random crypto!

ፋሲል ከ ድሬደዋ ምን ይመስል ነበር? Isaih Gardner እንደላከልን.... የጌታነህ ከበ | SKY ስፖርት ET™

ፋሲል ከ ድሬደዋ ምን ይመስል ነበር?

Isaih Gardner እንደላከልን....

የጌታነህ ከበደ ሁለት ጎሎች እና ናትናኤል ገ/ጊዮርጊስ አክርሮ መቶ ያስቆጠራት ኳስ ፋሲል ከነማን በ ድሬደዋ ከነማ ላይ የ3 ለ ምንም ድል እንዲቀዳጅ አድርጎታል።

ጨዋታው ከተጀመረ ከ11 ደቂቃዎች በኋላ ኳስን በጥሩ መልኩ ከሚጫወቱ ተጫዋቾች አንዱ የሆነው ሱራፌል ዳኛቸው ከ16ከ50 ውጭ አክርሮ የመታት ኳስ አደገኛ ብትመስልም ጎል መሆን ሳትችል ወደውጭ ወታለች።

58ኛው ደቂቃ ላይ ጌታነህ ከ18 ያርድ አካባቢ ያገኛት ቅጣት ምት የአንግሉን የውሰጠኛ ክፍል ነክታ የግብ መስመሩን ለማለፍ የተቃረበች መስላ ወደውጭ ወታለች።

63ተኛው ደቂቃ ላይ ጌታነህ ከተመሳሳይ ቦታ ላይ ቅጣት ምት የመታ ሲሆን ኳሷ ከተከላካዮቹ ግድግዳ በላይ አልፋ ጎል ለመሆን ችላለች።

አይምሬው አጥቂ ጌታነህ በቅጣት ምቱ ብቻ ሳያበቃ ከሽመክት ጉግሳ የተላከለትን ኳስ በማስቆጠር ለራሱም ለቡድኑም ሁለተኛ ጎል ማስቆጠር ችሏል።

85ተኛው ደቂቃ ላይ ተቀይሮ የገባው ናትናኤል ገ/ጊዮርጊስ የፋሲሎችን ጥሩ የኳስ ሂደት ያሳየች ጎል በማስቆጠር ድሉን 3 ለ ምንም በማድረግ የበለጠ አስተማማኝ ማድረግ ችሏል።

በዮናታን/ utopia የቀረበ...

@skysport_ethiopia
@skysport_ethiopia