Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰሞኑ የተፈፀሙ ግድያዎችን የሚያጣራ ኮሚቴ እንዲቋቋም ውሳኔ | ሲራራ ጋዜጣ

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰሞኑ የተፈፀሙ ግድያዎችን የሚያጣራ ኮሚቴ እንዲቋቋም ውሳኔ አሳለፈ

በኢትዮጵያ በኦሮሚያ እና ጋምቤላ ክልሎችን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች በዜጎች ላይ የተፈጸሙ ኢ-ሰብዓዊ ጭፈጨፋዎችን የሚያጣራ ልዩ ኮሚቴ እንዲቋቋም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወሰነ። በፓርላማው የበላይ አመራር የሚሰመው ይህ ልዩ ኮሚቴ “ለቀጣይ እርምጃዎች የሚረዳ ምክረ ሃሳብ” እንዲያቀርብ ኃላፊነት ተጥሎበታል።

የተወካዮች ምክር ቤት ይህን ውሳኔ ያሳለፈው ዛሬ ረቡዕ ሰኔ 29፤ 2014 ባካሄደው 6ኛ ልዩ ስብሰባ ላይ ነው። በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በዜጎች ላይ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ እና የዜጎችን ጸጥታ እና ደህንነት ለማስጠበቅ በተንቀሳቀሱ የጸጥታ አካላት ላይ የደረሰውን የህይወት መጥፋት “እጅግ የሚኮነን” መሆኑን ፓርላማው አስታውቋል። ምክር ቤቱ በዚህ መሰረት ካካሄደው ውይይት በኋላም ስድስት ውሳኔዎችን አሳልፏል።