Get Mystery Box with random crypto!

ከዚህ በኋላ ጌታ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል 'ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራን እናቴ ማርያምን ወደ ምት | ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ)

ከዚህ በኋላ ጌታ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል "ወዳጄ ክርስቶስ ሠምራን እናቴ ማርያምን ወደ ምትኖርበት ውሰዳት" አለው። ቅዱስ ሚካኤልም "ጌታ ወደ አዘዘልሽ ቦታ እንሒድ" አላት። ቅዱስ ሚካኤልም ይዟት ሲሔድ እጅግ የሚያስደነግጥና ከፀሐይ ከጨረቃ ከዋክብት ብሃርን ይልቅ ብርሃኑ የሚያበራ መንበር አየች። ይህን መንበር በአየችውም ጊዜ በጣም አድርጋ ወደደችው።

የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም "ክርስቶስ ሠምራ ምን ትመለከቻለሽ" አላት። "ያን ቡሩህ የሆነ መንበር እመለከታለሁ" አለችው። "ይህ መንበር ለአንቺ ቢሆን ትወጃለሽን" አላት። "አዎን ጌታዬ ለእኔ ቢሆን እወዳለሁ" አለችው። "እንግዲያውስ ለአንቺ የተዘጋጀ ነው" አላት። በዚያ ጊዜ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል "ጌታዬ መኖርያሽ እናቴ ከማርያም ጋር ነው ብሎኝ አልነበረምን"። ታዲያ እንዴት ይህ መንበር ለአንቺ የተዘጋጀ ነው ትለኛለህ" አለችው። መላአኩም "ክርስቶስ ሠምራ ሆይ ለምን ቸኮልሽ" አላት። ይህን ካአለ በኋላ ወደ እመቤታችን ወደ ድንግል ማርያም መኖርያ ወስዶ አደረሳትና። "ክርስቶስ ሠምራ ሆይ እግዲህ ተመልከች" አላት። በተመለከተቻት ወይም ባየቻት ጊዜም ማርያም ወይም ሰው አልነበረችም ነገር ግን ከፍታዋ ወይም ቁመቷ የላቀ ተራራ ነበረች እንጂ።

ቅዱስ ሚካኤልም "ማርያም ነች ብኸኝ አልበረምን ታዲያ እንዴት ተራራ ልትሆን ቻለች" አለችው። ያን ጊዜ ምሥጢሯ እስኪገለጽልሽ ድረስ ትንሽ ታገሽ" አላት። ከዚያም ቀና ብላ ብትመለከት እመቤታችን ድንግል ማርያምን አየቻትና እንደአሞራ በራ አንገቷን አቅፋ ሳመቻት። እመቤታችንም "ክርስቶስ ሠምራ ሆይ አንቺ የተባረክሽ ነሽ አንቺንም የሚያፈቅር የገድልሽን ዜና የሚሰሙ ሁሉ የተባርኩ የተመሰገኑ ናቸው" በማለት ሳመቻት። ይህንም ከአለቻት በኋላ በቀኟ አስቀመጠቻት...።

ከዚህ ሁሉ ነገር በኋላ አባ ይስሐቅ የሚባል መነኵሴ ከእናታችን ከክርስቶስ ሠምራ ዘንድ ቢሄድ ሥጋዋ ብቻ ወይም አስከሬኗ በጉድጎድ ውስጥ እንደተተከለ ምሰሶ ወይም ዓምድ ቆሞ አገኘው። ነፍስዋ ከሥጋዋ ያልተለየች ወይም በሕይወት ያለች መስሎት ነበርና "እናታችን ክርስቶስ ሠምራ ሆይ ባርኪኝ" አላት። የሚመልስለት ቢያጣ ወደ ወደርስዋ ቀረበና ሥጋዋን ዳሰሰው። እንደ ዐረፈችም በአወቀ ጊዜ ፈጽሞ ደነገጠ ከመሬት ላይ እየወደቀ እየተነሣ መራራ ልቅሶ አለቀሰ።

መነኰሳቱን ሁሉ ያለቅሱላት ዘንድ ጠራቸው። መነኰሳቱም እየተሽቀዳደሙና እየተሯሯጡ መጥተው አርፋ አገኙአት። በዚህ ጊዜ "አንቺን የተሸከመች ማኅፀን የተባለገች ነች አንቺንም ያጠቡ ጡቶች የተመሰገኑ ናቸው" እያሉ ጽዕኑና መራራ ልቅሶን አለቀሱ።

ከዚህ በኋላ አባ ይስሐቅ ሥጋዋን ወይም አስከሬኗን በንጹሕ በፍታ ገንዞ በሳጥን አድርጎ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ቀበራት። መነኰስ ይስሐቅም ወደ በዓቱ መመለሱ ቀርቶ በዚያው ቤተ ክርስቲያኖ በስተ ምሥራቅ በኩል በቁመቱ ልክ ጎድጎድ አስቆፍሮ በውስጧ ገባ።

ከዚያም ከጎድጎዱ ውስጥ ገብቶ "ከእንግዲህ እስክሞት ድረስ እንደ እናቴ ክርስቶስ ሠምራ ከዚህ ጎድጎድ አልወጣም" በማለት ወሰነ። ይህንንም ካአለ በኋላ መሪር እንባ እያለቀሰ እህል ሳይቀምስ እስከ 40 ቀን ተቀመጠ። ከ 40 ቀን በኋላ ነፍሱ ከሥጋው ተለየችና በእናታችን በክርስቶስ ሠምራ አማላጅነትና ልመና ፍጹም መንግሥተ ሰማያትን ወረሰ።

እናታችን ክርስቶስ ሠምራ በዚህ ዓለም በሕይወተ ሥጋ የኖረችው ሦስት መቶ ሰባ አምስት (375) ነው። ከእናታችን ከቅድስት ክርስቶስ ሠምራ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎቷም ይማረን!። ምንጭ፦ ገድለ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ።

+ + +
አቡነ ጊዮርጊስ ዘግሽ፦ ሀገራቸው ጎጃም ግሽ ዓባይ ሲሆን የታላቁ ጻድቅ አባት የአቡነ ዘርዐ ቡሩክ የአክስት ልጅ ናቸው። የተፀነሱትም ሆነ የተወለዱት በመልአክ ብሥራት ነው፡፡ ሰማዕትነት ለመቀበል ወደ ፋርስ በመሄድ ለ9 ሺህ ሰማዕታት መሪ ሆነው ጣዖትን ካጠፋ በኋላ በሰይፍ ተሰይፈው ሰማዕት የሆኑ ታላቅ አባት ናቸው። እመቤታችን ለዐፄ ካሌብ ተገልጻ የጻድቁን ዐፅም ወደ ሀገራችን እንዲመጣው ስላዘዘችው ዐፄ ካሌብም ዐፅማቸውን አስመጥቶ በጣና ቂርቆስ አስቀምጦታል። ከአባታችን አቡነ ጊዮርጊስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸም ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳንና ቅዱሳን በዓላት።

በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።

@sigewe

https://t.me/joinchat/AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA