Get Mystery Box with random crypto!

'በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን'። ነሐሴ ፳፪ (22 | ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ)

"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።

ነሐሴ ፳፪ (22) ቀን።

እንኳን ከዐሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ ለሆነው ለታላቁ ለሞራት ልጅ ለነቢዩ ለቅዱስ ሚክያስ ለዕረፍት በሰላም አደረሰን።

+ + +
የሞራት ልጅ ታላቁ ነቢይ ቅዱስ ሚክያስ፦ ይህም ነቢይ በይሁዳ ነገሥታት በኢዮአታም፣ በአካአዝና በሕዝቅያስ ዘመን ትንቢት በመናገር አስተማረ።

ስለጌታችን መውረድም እንዲህ አለ። "እነሆ እግዚአብሔር ከልዑል መንበሩ ወደዚህ ዓለም ይወርዳል"።

ሁለተኛም ስለ ልደቱ እንዲህ ብሎ ተናገረ "የኤፍራታ ዕጣ የምትሆኚ አንቺ ቤተ ልሔም የእስራኤል ነገሥታት ከነገሡባቸው አገሮች አታንሺም ወገኖቹን የሚጠብቃቸው የእስራኤል ንጉሥ ከአንቺ ይወጣልና"።

ስለ ምኵራብ መቅረት፤ ስለ ቤተ ክርስቲያን በዓለም ሁሉ መታነፅ ትንቢት ተናግሮአል። ዳግመኛም ስለ ሕገ ወንጌል መሠራት "ከጽዮን የእግዚአብሔር ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣል" አለ። የትንቢቱም ወራት ሲፈጸም ወደ በጎ ሽምግልና ደርሶ ወደ ወደደው እግዚአብሔር ሔደ።

የትንቢቱ ዘመን ከጌታችን መምጣት በፊት በስምንት መቶ ዓመት ነው። ማርታ በምትባልም ቦታ ተቀበረ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የነቢዩ የቅዱስ ሚክያስ በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የነሐሴ 22 ስንክሳር።

+ + +
"ሰላም ለሚክያስ ነባቢተ ትንቢት ልሳኑ። ዘይከውን በበዘመኑ። እንዘ ይብል ከመዝ ኂሩተ አምላክ ይዜኑ። መኑ ከማከ እግዚኦ አምሳለ አማልክት ዘኮኑ። አበሳ ርስቱ ዘይትነሐይ መኑ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የነሐሴ 22።


በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።

@sigewe

https://t.me/joinchat/AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA