Get Mystery Box with random crypto!

“ረጋፊ ጠፊ ፡ አላፊ ነው ውበት” የሚል ቃል ቢዘራም የሰባኪ አንደበት ምን ቀሪ አለውና፡ ዘላለም | በራሪ ሐሳቦች

“ረጋፊ ጠፊ ፡ አላፊ ነው ውበት”
የሚል ቃል ቢዘራም የሰባኪ አንደበት
ምን ቀሪ አለውና፡
ዘላለም ዓለሙን ሰው የሚከርምበት!?
የሞትን ክራንቻ፡ በጥበብ በኪነት፡ በቃል አሞኝቶ
የሚቀር ይመሥል ውበቱን ሸኝቶ፤
ጠባይ ላያከርመው፡ ዕውቀት ላያዘልቀው
ካላፊ ሰውነት... መበጅቱን ሲያውቀው
ሒያጁ አይደለም ወይ...
ቀድሞ እሚሔደውን ቆሞ እሚጠብቀው?
#RD