Get Mystery Box with random crypto!

#ጤናመረጃ ለስላሳ መጠጥ አዘዉትሮ እና በመደበኛነት መጠጣት የሚያስከትለው ጉዳት!! ይህ እውነታ | ሸገር NEWS

#ጤናመረጃ

ለስላሳ መጠጥ አዘዉትሮ እና በመደበኛነት መጠጣት የሚያስከትለው ጉዳት!!

ይህ እውነታ ሊያስደነግጥህ ይችላል። ለስላሳ መጠጥ ያለማቋረጥ እና በመደበኛነት መጠጣት የኩላሊት ጠጠር እንዲፈጠር እንደሚያደርግ ጥናቶች አረጋግጠዋል። ይህ የሚከሰተው በአሲድ እና በማዕድን ራዲካል ሚዛን ምክንያት ነው።

ለስላሳ መጠጦች ለውፍረት መንስኤ ከሚሆኑት ዋና ዋና ምክንያቶች መካከል አንዱ እንደሆነ በሙከራ ተረጋግጧል።

ለስላሳ መጠጥ አዘውትሮ መጠጣት ለአጥንት መዳከም እና ኦስቲዮፖሮሲስን እንደሚያመጣ ተረጋግጧል።

ለጥርስ መበስበስ ያጋልጣሉ። ለስላሳ መጠጦች አሲዳማ ይዘት ያለው የጥርስ መስተዋት በማሟት ደካማ ያደርጋቸዋል።

ለስላሳ መጠጦች ጠንካራ የካፌይን ይዘት አላቸው። ካፌይን ብስጭት፣ እረፍት ማጣት፣ ውጥረት፣የደም ግፊት፣ከመጠን በላይ ሽንት እና ሌሎች የጎንዮሽ ጉዳቶችን ያስከትላል።

ይህን ጠቃሚ መረጃ ለሁሉም እንዲደርስ ሼር|share በማድረግ ይተባበሩ!

"በዶ/ር ሀይለልኡል መኮንን የቀረበ"
@shegernewsbot
@shegernewsETH