Get Mystery Box with random crypto!

ፕሬዝደንት ባይደን እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ አሉ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና ባ | ሸገር NEWS

ፕሬዝደንት ባይደን እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ አሉ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና ባለቤታቸው ጂል ባይደን ኢትዮጵያውያንን እና ኤርትራውያንን እንኳን ለአዲስ ዓመት አደረሳችሁ ሲሉ የመልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።ከዚህ ቀደም ባልተለመደ ሁኔታ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በራሳቸውና በባለቤታቸው ስም ለኢትዮጵያውያንና ለኤርትራውያን እንዲሁም ከእነዚሁ አገራት የዘር ሐረጋቸው ለሚመዘዝ በመቶሺህዎች ለሚቆጠሩ አሜሪካውያን የአዲስ ዓመት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

በዚሁ መልዕክታቸው ላይ ፕሬዝዳንቱ በኢትዮጵያ ውስጥ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ስለሚፈጸሙ ጥቃቶች ሪፖርቶች በእጅጉ እንዳሳሳባቸው ገልጸው፤ አስተዳደራቸው በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ከአጋሮቻችን ጋር ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

ፕሬዝዳንቱ ጨምረውም ሰላምን ማምጣት ቀላል እንዳልሆነ ነገር ግን በውይይት ሊጀመር እንደሚችል በመግለጽ “ታላቋና ባለብዝሃነቷ ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ የገጠማትን መከፋፈል እንደምትወጣውና በድርድር ላይ በተመሰረተ የተኩስ አቁም በማድረግ እየተካሄደ ያለውን ግጭት እንደምትፈታው እንምናለን” ብለዋል።

በመልዕክታቸው ላይ በአማርኛ “መልካም አዲስ ዓመት” በማለት በዓሉን ለሚያከብሩ በሙሉ የተመኙት ፕሬዝዳንት ባይደን “አዲሱ ዓመት በኢትዮጵያ፣ በኤርትራና በዓለም ዙሪያ ላሉ ቤተሰቦችና ማኅበረሰቦች ሰላም፣ እርቅ እና ፈውስ የሚመጣበት እንዲሆን እጸልያሉ” ብለዋል።

@shegernewsbot
@shegernewsETH