Get Mystery Box with random crypto!

በጎንደር ከተማ ህገ-ወጥ የነዋሪነት መታወቂያ ሲያዘጋጁ የነበሩ አራት ተጠርጣሪዎች ተያዙ የመምሪያ | ሸገር NEWS

በጎንደር ከተማ ህገ-ወጥ የነዋሪነት መታወቂያ ሲያዘጋጁ የነበሩ አራት ተጠርጣሪዎች ተያዙ

የመምሪያው የመረጃና ክትትል ባለሙያ አቶ ስንታየሁ ተገኘ እንደተናገሩት ህገ-ወጥ መታወቂያዎቹ የተያዙት በማተሚያ ድርጅቱ ውስጥ በተደረገ ድንገተኛ ቁጥጥር ነው፡፡

መታወቂያዎቹ በሀሰተኛ ደብዳቤና ምንም አይነት የይታተምልን የትእዛዝ ደብዳቤ በሌለበት ሁኔታ ታትመው እጅ ከፍንጅ የተያዙ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ህገ-ወጥ መታወቂያዎቹ በላይ አርማጭሆ ወረዳ የአምበዞ ቀበሌ 200 እንዲሁም በምእራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ጉባይ ጀጀቢት ቀበሌ ስም 198 የተዘጋጁ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

በተጨማሪም በማእከላዊ ጎንደር ዞን መሃል አርማጭሆ ወረዳ ፈልፈል ቀበሌ ስም የተዘጋጁ 146 ህገ-ወጥ መታወቂያዎች በማተሚያ ቤቱ ታትተመው ለስርጭት በዝግጅት ላይ እንዳሉ መያዙን ገልፀዋል።

ከህገ-ወጥ የመታወቂያ ህትመቱ ጋር በተያያዘም የማተሚያ ቤቱን ባለቤት ጨምሮ አራት ተጠርጣሪ ግለሰቦች በህግ-ቁጥጥር ስር ውለው በፖሊስ ምርመራ መጀመሩን ገልጸዋል፡፡

@shegernewsbot
@shegernewsETH