Get Mystery Box with random crypto!

  የ #ቴዲዮ ሙሉ የዘፈን                      የወንዜ የወንዜ የወንዜ ትር | Sheger student Union( የአዲስ አበባ ተማሪዎች ህብረት)

  የ #ቴዲዮ ሙሉ የዘፈን
                    

የወንዜ የወንዜ የወንዜ ትርምስ
ጥያቄ ብቻ ነው መልሱ ላይመለስ
የወንዜ የወንዜ የወንዜ አራት ኪሎ
ወንበርሽ ይፋጃል ጠፋ ሁሉን ጥሎ
=====
ልዩ ነሽ አዎ አማላይ
በውበትሽ ሰው ገዳይ
የኔ እንዳሉሽ አለ ከልካይ
ስንቱን አየን ባንቺ ጉዳይ
=====
እውነት እውነቱን እስኪ ልናገር
ሁሉም ይበል ባንቺ ጥንቅር
ተወልደናል እኛ ሸገር
እንደሌለው ሆነን ሀገር
=====
እደጊ ቤቴን ለቀቅኩልሽ
ያላቀና ጎዳና ሲጥልሽ
እትብቴን አንቅረሽ ተፋሽ
ይሁና አንቺን ግን አይክፋሽ
=====
ሰውም አይኖር ያለ መሬት
መሬትም አይሆን ያለ ሰው
ዝም ያለው የሸገር ሰው
ወዴት ይሆን ሄዶ የሚያርሰው
=====
የአራዳ ልጅ እድለኛ
የፀዳ ነው ከዘረኛ
ለመጣሁ ለተረኛ
ማጨብጨብ ነው ለቀማኛ
=====
ሸገር ተወልዶ ማደጉ
የቱጋ ነው አስቲ ጥቅሙ
በስጋት ቤት ማጉረምረሙ
መኖር አፈር እየቃሙ
=====
ይባስ ከአምናው ዘንድሮ
ልቤ ከቀዬው ተባሮ
በቃ እሺ ልጀምር ጉዞ
ክፉ ከማይ ከዚ ብሶ
=====
በፍቅር ስኖር ባንቺ ኮርቼ
አላውቅም ነበር ተከፍቼ
ጊዜ ጌታ ነው ተገፍቼ
ስደት መረጥኩኝ ወገኖቼ
=====
አስቤ አላውቅም ባህር ማዶ
ክፋት ሲበዛ ስር ስር ሰዶ
ከፍቅረኛ ጋር ኪስ ግን ባዶ
በዚህ ቀን አይስቁም ወዶ
=====
አረንጓዴ ቢጫ ቀይ አርማችን
የኛ መመኪያችን
ፍቅር መስጠት ያስተማረችን
ሸገር እናታችን
=====
ቀዬ ፈርሶ ህንፃ ቢደረደር
ላይቀረፍ ችግር
ሰው እየተካ ድንጋይ ቢደራረብ
ጠፍቶ መተሳሰብ
=====
ጎበዝ ንቃ ንቃ ንቃ
ሰግጣ ስቃ ስቃ ስቃ
ከበረች ዝቃ ዝቃ ዝቃ
ሄደች ልቃ ልቃ ልቃ
=====
ሴረኞች አንቺን ለማዋረድ
ሳያውቁሽ ከውጪ ማጎብደድ
ኪሎ ነሽ የአፍሪካችን ዘውድ
ይዘውታል ቅባትን ማላመድ
=====
ስም አወጡልሽ የዳቦ
ዳቦሽን ሳይቀምሱ በጉቦ
ተንሰፈሰፈ ሊበላሽ ተርቦ
ይጠብቅሽ አምላክ አስቦ

ኢትዮጵያ ብቻ
@Sheger_student_union
@Sheger_student_union
Join and Share
የአዲስ አበባ ተማሪዎች ህብረት