Get Mystery Box with random crypto!

የዒድ ተክቢራዎች የዒዱ ሌሊት (ነገ ዒዱ ሊሆን ዛሬ) ፀሀይ ከገባ ጀምሮ ኢማሙ (አሰጋጁ) የዒድን | SHAMIL

የዒድ ተክቢራዎች
የዒዱ ሌሊት (ነገ ዒዱ ሊሆን ዛሬ) ፀሀይ ከገባ ጀምሮ ኢማሙ (አሰጋጁ) የዒድን ሶላት እስኪጀምር ድረስ መስጂዶች ላይ፣ የገቢያ ቦታዎች ላይ፣ መንገዶች ላይ እና ቤቶች ላይ ተክቢራ ማድረግ ሱና ነው፡ ከሶላቶች በኋላ የሚደረገው ተክቢራ ግን ሰጋጁ የዓረፋ ቀን ከሱብሂ ሶላት በሆላ ነው ሚጀምረው ይሄ ተክቢራ የሚያበቃውም ከተሽሪቅ ቀኖች (ከዒዱ ቀንጥለው ከሚመጡት ሶስት ቀኖች) መጨረሻ ቀን ከዓሱር ሶላት በኋላ ነው።

የዒዱ ተክቢራዎችም የሚከተሉት ናቸው፦
الله أكبر الله أكبر الله أكبر لا إله إلا الله
الله أكبر الله أكبر ولله الحمد
الله أكبر كبيرًا، والحمد للّه كثيرًا وسبحان الله وبحمده بُكرةً وأصيلًا
لا إله إلا الله وحده، صدق وعده، ونصر عبده وأعزّ جنده، وهزم الأحزاب وحده، لا إله إلا الله ولا نعبد إلّا إياه مخلصين له الدين ولو كره الكافرون اللّهمّ صلّ على سيّدنا محمّد وعلى آل سيدنا محمّد وعلى أصحاب سيدنا محمّد وعلى أنصار سيدنا محمّد وعلى أزواج سيدنا محمّد وعلى ذرّية سيدنا محمّد وسلّم تسليمًا كثيرًا، ربّ اغفر لي ولوالدي ربّ ارحمهما كما ربياني صغيرًا.
አሏሁ አክበር አሏሁ አክበር አሏሁ አክበር
ላኢላሀኢለሏህ
አሏሁ አክበር አሏሁ አክበር አሏሁ አክበር
አሏሁ አክበር ከቢራ፡ ወልሀምዱሊላሂ ከሲራ ወሱብሃነሏሂ ቡክረተን ወአሲላ
ላኢላሀኢለሏህ ወህደህ፡ ሶደቀ ወዕደህ፡ ወነሶረ ዓብደህ ወአዐዘ ጁንደህ፡ ወሀዘመል አህዛበ ወህደህ፡ ላኢላሀኢለሏህ ወላ ነዕቡዱ ኢላ ኢያሁ ሙኽሊሲነ ለሁ ዲነ ወለው ከሪሀ ልካፊሩን አሏሁመ ሶሊ ዓላ ሰይዲና ሙሀመድ ወዐላ ኣሊ ሰይዲና ሙሀመድ ወዓላ አስሀቢ ሰይዲና ሙሀመድ ወዐላ አንሷሪ ሰይዲና ሙሀመድ ወዐላ አዝዋጂ ሰይዲና ሙሂ ወዐላ ዙሪየቲ ሰይዲና ሙሀመድ ወሰሊም ተስሊመን ከሲራ፡ ረቢ ግፊርሊ ወሊዋሊደየ ረቢርሀምሁማ ከማ ረበያኒ ሶጊራ።
https://t.me/shamilkaml