Get Mystery Box with random crypto!

Selah

የቴሌግራም ቻናል አርማ selahethiopia — Selah S
የቴሌግራም ቻናል አርማ selahethiopia — Selah
የሰርጥ አድራሻ: @selahethiopia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 751
የሰርጥ መግለጫ

Vulnerable, thought-provoking conversations among Ethiopian women on the Gospel, the mission of the Church, and the life of a Christian
Contact us @SelahContactBot
Follow us on Facebook, Instagram, Pinterest and Twitter
https://selahethiopia.org/follow

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-07 14:50:30
በዚህ ጥቅስ ውስጥ ምን ጎልቶ ይታይሻል? ምናልባት ለአንዳንዶች፣ እግዚአብሔር ሰዎችን ከአፉ ሊተፋ መቻሉ ሊያስደነግጥ ይችላል። ለእኔ ግን ይህንን አንብቤ እግዚአብሔርን የሚረዳኝ እና በሕይወቴ ውስጥ በመንፈሳዊ ነገሮች በቀዘቀዝኩባቸው ወቅቶች ውስጥ የሚይዘኝ አምላክ አድርጌ እንዳየው ያደርገኛል። እግዚአብሔር የእኔን መንፈሳዊ ዝቅጠት ከእኔ ለመራቅ እንደ ምክንያት እንደማይቆጥረው አይቻለሁ። በመንፈው ለብ ያልን በመሆናችን ደስታን እና እረፍትን ስናገኝ ነው እንጂ እግዚአብሔር የሚጠይቀን፤ በመንፈሳዊ ከፍታዎች እና ዝቅታዎች ውስጥ ሁሉ ግን ያየናል።

What stands out to you in this verse? Maybe to some, it's that God can spit people out of His mouth. But to me, I read this and see God as someone who understands and holds me through the spiritually cold seasons of my life. I see that God does not consider my spiritual lows a reason to depart from me. It's when we find comfort in being lukewarm that God takes issue with us. He sees us through the spiritual highs and the lows.

@SelahEthiopia
457 viewsedited  11:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 16:45:34 መጽሐፍ ቅዱስ ሁል ጊዜ በጌታ እንድንደሰት ያዝዛል። ግን ይህ በእርግጥ ይቻላል? የምንኖረው ስሜታችንን ከፍ እና ዝቅ በሚያደርግ ዓለም ውስጥ ነው። ታዲያ በክርስቶስ ያለማቋረጥ ደስተኛ ለመሆን እንዴት እንችል ይሆን?

The Bible commands us to rejoice always in the Lord. But is this really possible? We live in a world that takes our emotions both high and low. Then how can we manage to consistently be happy in Christ?



513 views13:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 18:28:18
አንድ ክርስቲያን ለክርስቶስ ካላት እውነተኛ እና የዕድሜ ልክ ቃል ኪዳን ምን መጠበቅ ትችላለች? አንድ ክርስቲያን በጌታ የሕይወትን መንገድ ማወቅ ትችላለች። ነገር ግን ከምንም ነገር በላይ፣ አንድ ክርስቲያን እጅግ ጥልቅ የሆነ ደስታን፣ በራሱ በጌታ ወደር የለሽ እርካታን ማግኘት ትችላለች። እርሱ ከሁሉም ይበልጣል።

What can a Christian expect from a genuine and lifelong commitment to Christ? A Christian can expect to be shown the path of life. But above all else, a Christian can expect to experience the most profound pleasure, an unrivaled satisfaction in the Lord Himself.

@SelahEthiopia
632 views15:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 21:14:48
ሁላችንንም ያየናል። ሁላችንንም ይይዘናል። ሁላችንንም ይጠብቀን። እግዚአብሔር ሁላችንንም እናቶች ይባርክ።

መልካም የእናቶች ቀን።

@SelahEthiopia
951 views18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-02 17:59:15
ሌሎች ሰዎች ስለእኛ ስላላቸው ግንዛቤ ስንል በምናደርገው የሐሰተኛ አምልኮ ጩኸት ወይም ለታይታ የሚደረግ የእምነት ማሳያ ሳይሆን በቅን ልብ እና በእውነተኛ ተነሳሽነት ነው የአባታችንን ትኩረት የሚስበው ጥሪ የሚገኘው። ለዚህ ለሁላችንም የተጋላጭነት እና እውነተኛነት መንፈስ በጌታችን ፊት እንዲኖረን እጸልያለሁ።

Not with counterfeit cries of worship or displays of deep faith that we do for the sake of others' perception of us, but with a sincere heart and motivation. That's the call that gets the attention of our Father. Praying for this posture of vulnerability and truthfulness for all of us today.

@SelahEthiopia
665 views14:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-25 21:40:12
ክርስቶስ በጥልቅ የጭንቀት ጊዜው ውስጥ በጸሎት ውስጥ ንቁነትን አፅንዖት ሰጥቶ በዚያ ውስጥ ህብረትን ምሳሌ አድርጎ ያሳያል። ይህ የአንቺን የሀዘን ጊዜያት እና የደስታ ጊዜያት እንዴት ይቀርፃል?

Christ, in His time of deepest anguish, emphasizes alertness in prayer and exemplifies community. How does this shape your moments of sorrow and your moments of joy?

@SelahEthiopia
621 views18:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 12:59:55
ክርስቶስም ካልተነሣ እምነታችሁ ከንቱ ነው፤ እናንተም እስከ አሁን ድረስ ከነኀጢ አታችሁ አላችሁ ማለት ነው። እንዲህም ከሆነ፣ በክርስቶስ ያንቀላፉት ጠፍተዋል ማለት ነው። ክርስቶስን ተስፋ ያደረግነው ለዚህች ሕይወት ብቻ ከሆነ፣ ከሰው ሁሉ ይልቅ የምናሳዝን ነን። ነገር ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት ሁሉ በኵራት ሆኖ በርግጥ ከሙታን ተነሥቶአል። ሞት በአንድ ሰው በኩል እንደ መጣ፣ የሙታንም ትንሣኤ በአንድ ሰው በኩል ሆኖአልና። ሰዎች ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ፣ እንደዚሁም ሰዎች ሁሉ በክርስቶስ ሕያዋን ይሆናሉ፤
1 ቆሮንቶስ 15:17 - 22

ሕያው ሆኖ ሕያው አርጎናል! ስሙ ይባረክ!
ተነስቷል!

@SelahEthiopia
518 views09:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-23 10:12:16
ኢየሱስ ከተሰቀለ እና ከተገደለ በኋላ፣ ለደቀ መዛሙርቱ ምን ያህል አሳዛኝ እና ተስፋ ቢስ መስለው ነገሮች እንደተሰሟቸው መገመት እንችላለን። ስለ እርሱ የተነገረውን ትንቢት ቢሰሙም፣ ተአምር ሠሪ መሆኑን ቢያውቁም፣ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ቢናዘዙም፣ ሞቱ በእርግጥ ጨለማን አመጣላቸው።
ሕይወት አንዳንድ ጊዜ አዳኝ የሌላት፤ በጨለማ ውስጥ ያለች መስሎ ሊሰማን ይችላል።
እምነት ማለት ግን ዓይኖቻችን የማያዩትን ማመን ነው። እርሱ ከሞት ተነስቷል፤ ተስፋ እንዲኖረን፣ ለማመን በሚከብድበት ጊዜ እንኳን እንድናምን ሞትን አሸንፏል።

@SelahEthiopia
968 views07:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 10:45:06
እግዚአብሔር ፍትሃዊ ባይሆን ኖሮ ልጁ እንዲሰቃይና እንዲሞት ባላስፈለገው ነበር። እግዚአብሔር የፍቅር አምላክ ባይሆን ኖሮ ልጁ እንዲሰቃይ እና እንዲሞት ባልፈቀደ ነበር። እግዚአብሔር ግን ፍትሃዊ እና አፍቃሪ ነው። ስለዚህ ፍቅሩ የፍትህ መስፈርትንሁሉ ለማሟላት ፈቃደኛ ሆነ።

ፍቅሩን አናቅልለው። የኃጢአታችንን ክብደትና በእኛ ላይ የነበረውን የቁጣውን ትክክለኛነት እስካልተረዳን ድረስ በእግዚአብሔር ፍቅር እና መወደድ አንገረምም። ነገር ግን በጸጋው ወደ አለመብቃታችን ስንነቃ የክርስቶስን መከራና ሞት ተመልክተን እንዲህ እንላለን: "ፍቅር ይህ ነው፤ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው ሳይሆን እርሱ እንደ ወደደንና ስለ ኀጢአታችን ማስተስረያ ይሆን ዘንድ ልጁን መላኩ ነው።" (1ኛ ዮሐንስ 4:10)

@SelahEthiopia
434 viewsedited  07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-21 14:35:55
ኢየሱስ ደሙን የሚያቀርበው አሮጌው ኪዳን በደም እንደታተመ በደም የታተመ አዲስ ኪዳን የመመሥረት ሥልጣን ያለው እርሱ ብቻ ስለሆነ ነው። ደሙንም ለእኛ አፈሰሰ። "እውነት እላችኋለሁ፤ በእግዚአብሔር መንግሥት አዲሱን የወይን ፍሬ እስከምጠጣበት እስከዚያች ቀን ድረስ ዳግም ይህን አልጠጣም።” ሲልም ይናገራል፤ ይህም ኢየሱስ ገና በሰማይ የፋሲካን በዓል እንደገና አላከበረም ማለት ነው። አሁንም ሕዝቡ ሁሉ ወደ እርሱ እስኪሰበሰቡ ድረስ ይጠብቃል ከዚያም ታላቅ እራት ይሆናል፤ የበጉ ሰርግ እራት (ራዕይ 19፡9)።

እየሱስ የከፈለው ዋጋ የማይሻር ዘለዐለማዊ ዋጋ ነው። ወደ ታላቁ እራት እያየን፣ እየተጠባበቅን የፈሰሰውን ደሙን እንደ ተስፋ እንያዝ። ስለ አንቺ የፈሰሰ ሀያል የአዲስ ኪዳን ደም አለ።

Jesus offers His blood as only He has the authority to establish a new covenant, sealed with blood, even as the old covenant was sealed with blood (Exodus 24:8).

@SelahEthiopia
603 views11:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ