2023-04-26 20:01:51
የፀጉር ቀለም
አብዛኛውን ግዜ፣ አንድ ሰው የፀጉር ቀለምን የሚጠቀምበት አንደኛው ምክኒያት፣ ያለግዜው የሚመጣ ሽበትን ለመሸፈን ነው።
ያለግዜው የሚመጣ ሽበት ደሞ፣ በጣም ጥቂት ከሚባሉ የጤና ችግሮች በስተቀር፣ አብዛኛውን ግዜ በተፈጥሮ የሚመጣ ሁኔታ ነው።
እርጉዝ ሴት የፀጉር ቀለም መቀባት ትችላለች እንዴ? ለካንሰር በሽታ አጋላጭ የሆነው የፀጉር ቀለምስ የትኛው ነው?
ከአንድ የፀጉር ዘለላ ተፈጥሮአዊ ክብደት ውስጥ ፣97 % የሚሆነው የፀጉር ይዘት፣ ቀለም አልባ ተፈጥሮ ነው። የፀጉር ቀለም፣ የተቀረውን 3 % ብቻ የሚሆነውን የክብደት ድርሻ ይይዛል።
ታዲያ፣ ምንም እንኳን ተፈጥሮ ለፀጉር ቀለም ያደለው ክብደት በጣም አነስተኛ ቢሆንም፣ ከስነውበት አንፃር በማህበረሰብ ዘንድ የሚሰጠው ድርሻ ግን ቀላል የሚባል አይደለም
የአንድ ሰው ተፈጥሮአዊ የፀጉር ቀለም፣ አብዛኛውን ግዜ ከ ሁለት መሰረታዊ የተፈጥሮ ቀለሞች የተገነባ ነው። እነዚህ ቀለሞች፣ በህክምናው " eumelanin "እና "pheomelanin " በመባል ይታወቃሉ። አንዳንድ ሰው ላይ "oximelanin " በመባል የሚታወቅ ሶስተኛ የቀለም አይነት ሊኖር ይችላል።
አንድ ሰው፣ ምንም አይነት ተጓዳኝ የጤና ችግር ሳይኖርበት በተፈጥሮ ብቻ የመጣ ሽበትን ግዜያዊ በሆነ መልኩ ለመቀነስ ካሰበ፣ ሁለት አይነት አማራጮችን መጠቀም ይችላል።
አንደኛው መንገድ፣ የሽበት መጠኑ 10 % እና ከዛ በታች ከሆነ፣ ሽበቱን መንቀል ይቻላል። ወይም ደሞ የዛ ሰው የሽበት መጠን ከ 10 % በላይ ከሆነ፣ የፀጉር ቀለምን መጠቀም ሌላኛው አማራጭ ነው
ሽበትን ለመሸፈን፣ ወይም ለማቅለም የተዘጋጁ የፀጉር ቀለሞች፣ በሁለት አይነት መንገድ ፀጉሩን ሊያቀልሙት ይችላሉ፣
አንደኛው መንገድ፣ የፀጉሩን ዘለላ የላይኛውን ሽፋን ብቻ በቀለም በመሸፈን ሲሆን፣
ሁለተኛው መንገድ ደሞ፣ ቀለሙ ከፀጉር ዘለላው ውስጥ ገብቶ እንዲቀመጥ በማድረግ ነው።
ፀጉር ውስጥ ሳይገቡ የፀጉሩን ሽፋን ብቻ የሚያቀልሙት የፀጉር ቀለሞች፣ ግዚያዊ ቀለሞች ናቸው፣ በተደጋጋሚ ግዜ በመታጠብ ግዜያቸውን ጠብቀው ከፀጉር ላይ ይነሳሉ።
የፀጉር ዘለላው ውስጥ የሚገቡት ቀለሞች ደሞ፣ በቋሚ መልክ የተዘጋጁ ቀለሞች ናቸው፣ ማስለቀቂያ ኬሚካሎችን በመጠቀም እና ፀጉሩን በመቁረጥ ካልሆነ በቀር፣ ፀጉሩን በተደጋጋሚ ግዜ በማጠብ ብቻ ቀለሙን ማስለቀቅ አይቻልም።
በዚህ መሰረት ታዲያ፣ አራት አይነት የፀጉር ቀለሞችን ገበያ ላይ ታገኛላችሁ
ስለነዚህ የፀጉር ቀለም አይነቶች እና አንዳንዶቹ ቀለሞች የሚያስከትሉትን የጎንዮሽ ጉዳት በተመለከተ አጠር ያለ መረጃ በ YouTube ቻናሌ ላይ አስቀምጫለሁ።
ለመመልከት ከፈለጋችሁ የሚቀጥለውን አድራሻ ተጭናችሁ ማግኘት ትችላላችሁ።
መልካም ግዜ።
43.1K viewsDr. Seife, 17:01