Get Mystery Box with random crypto!

የእግር እብጠት ሁለት እግር አንድ ላይ የሚያብጥ ከሆነ አንዳንዴ ጥሩ ምልክት አይደለም፣ | Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ

የእግር እብጠት

ሁለት እግር አንድ ላይ የሚያብጥ ከሆነ አንዳንዴ ጥሩ ምልክት አይደለም፣

ለወራት የሚቆይ ተቅማጥ ፣ የጉበት ችግር፣ የኩላሊት በሽታ፣ እና የልብ ድክመት ሲኖር፣  ከተለያዩ ተጓዳኝ ምልክቶች ጋር ሁለቱም እግር ሊያብጥ ይችላል።

እብጠቱ በኩላሊት ድክመት ምክኒያት የመጣ ከሆነ፣ በእግር ላይ እብጠት ከመጀመሩ በፊት፣ የአይን ዙሪያ እብጠት ይኖራል

በልብ ህመም ምክኒያት የሚመጣ የእግር እብጠት፣ እንደ ደረጃው ራስ መሳት፣ አቅም ማነስ፣ ሳል እና አየር ማጠር ሊኖረው ይችላል

የእግር እብጠት በጉበት ድክመት ምክኒያት የመጣ ከሆነ ደሞ፣ ሆድ ማበጥ እና የአይን ቢጫ መሆን ሊከሰት ይችላል።

አንዳንዴ ደሞ፣ የከፋ የጤና ችግር በሌለበት ሁኔታም፣ አንድ ሰው ላይ የእግር እብጠት ሊያጋጥም ይችላል።

ለምሳሌ፣ ነብሰጡር ሴት ላይ እርግዝናው እየገፋ ሲሄድ፣ ሁለቱም እግር ሊያብጥ ይችላል፣

ውፍረት የሚታይበት ሰው በቀን ውስጥ ረጅም ሰአት የሚቆም ከሆነም፣ እግር ሊያብጥ ይችላል።

አብዛኛውን ግዜ እድሜያቸው ከ 50 በላይ የሆኑ ሰዎች ላይ፣ ከደም ስር ድክመት ጋር በተያያዘ ሁኔታ፣ ሁለቱም እግር ላይ እብጠት ሊፈጠር ይችላል።

ታዲያ አንድ ሰው ላይ የሚታይ የእግር እብጠት ፣ በምን ምክኒያት እንደመጣ እንዴት መለየት ይቻላል

የእግር እብጠትን በተመለከተ ከነህክምናው ሰፋ ያለ መረጃ ዩቲዩብ ላይ አስቀምጫለሁ።

የሚቀጥለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን መመልከት ትችላላችሁ።