Get Mystery Box with random crypto!

ቋቁቻ ቋቁቻ እና ጭርት ሊመሳሰሉ ይችላሉ ፣ ነገር ግን፣ ሁለቱም  የተለያየ ዝርያ ባለው | Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ

ቋቁቻ

ቋቁቻ እና ጭርት ሊመሳሰሉ ይችላሉ ፣ ነገር ግን፣ ሁለቱም  የተለያየ ዝርያ ባለው ተህዋስ የሚፈጠሩ የቆዳ በሽታዎች ናቸው፣

ቋቁቻ ከሰው ወደሰው አይተላለፍም፣ ጭርት ከሆነ ግን ከሰው ወደሰው ብቻ ሳይሆን ከእንስሳት ወደሰውም ጭምር በንክኪ መተላለፍ ይችላል።

ቋቁቻን የሚያስከትለው ተህዋስ፣  አንድ ጤናማ ሰው ቆዳ ላይ፣ ምንም አይነት ቋቁቻን ሳያስከትል ፣ ልከኛ በሆነ መንገድ በተፈጥሮ የሚኖር ተህዋስ ነው፣በህክምናው malassezia ተብሎ ይጠራል።

በተለያዩ ምክኒያቶች ፣ይህ ተህዋስ ከልክ ባለፈ መልኩ ቆዳ ላይ ማደግ ሲጀምር እና የላይኛውን ቆዳ ሲያጠቃ፣ በቦታው ላይ ቋቁቻን ይፈጠራል።

ይህ ቋቁቻን የሚያስከትል ተህዋስ፣ የተለያዩ ዝርያዎች ያሉት ቢሆንም፣ ነገር ግን፣ አንድ ሰው ላይ ቋቁቻን ሊፈጥሩ የሚችሉት በዋነኝነት 3 አይነት ዝርያዎች ናቸው።

እነዚህ ዝርያዎች፣ አንድ ሰው ቆዳ ላይ ፣ ቋቁቻን የሚያስከትሉበት የተለያየ ምክኒያት አላቸው፣

ወዛም የሆኑ ሰዎች፣ ሞቃታማ ቦታ የሚኖሩ ከሆነ እና ፣ የንፅህና ጉድለት ካላቸው
ዘይታማ ቅባቶችን ቆዳ ላይ አዘውትሮ በመቀባት
የአንድ ሰው የበሽታ መከላከል አቅም ሲቀንስ
እንደ ደርሞቬት ፣ቤትኖቬት፣ ቤታሴት የመሳሰሉትን መዳኒቶች ፣ ከሀኪም ትእዛዝ ዉጪ ለረጅም ግዜ አዘውትሮ በመቀባት
ጥራታቸውን ያልጠበቁ እና ፊትን የሚያቀሉ ክሬሞችን ማዘውተር የመሳሰሉት፣ አንድ ሰው ላይ በተደጋጋሚ ግዜ ቋቁቻ እንዲወጣ የሚያደርጉ ምክኒያቶች ናቸው።

ቋቁቻ በቆዳ ላይ ሲወጣ፣ ነጣ ያለ ወይም ደሞ ጠቆር ያለ ገፅያን ሊይዝ ይችላል፣ አብዛኛውን ግዜ ደሞ፣ ከሌላው የሰውነት ክፍል ይልቅ፣ ወዝ በበዛበት የቆዳ ክፍል ላይ የመውጣት ባህሪ አለው።

ፊት ላይ የሚወጣ ቋቁቻ ፣ አብዛኛውን ግዜ በአዋቂዎች ላይ የተለመደ አይደለም፣ ነገር ግን፣ ካዋቂዎች ይልቅ አንዳንዴ የልጆች ፊት ላይ ሊያጋጥም ይችላል።

ቋቁቻ መሆኑን ለመለየት ፣ አንድ ሰው ከታጠበ በኋላ ምንም አይነት ቅባት ሳይቀባ፣ ቋቁቻው በወጣበት ዙሪያ ያለውን ቆዳ በመለጠጥ ፣ወይም ደሞ ፣ቋቁቻው ሲታከክ፣ አመድ የመምሰል ገፅታን ይሰጣል።

እየከሰመ ያለ ቋቁቻ ሲሆን ደሞ፣ አብዛኛውን ግዜ አመድ የመምሰል ባህሪ ላይኖረው ይችላል።

ታዲያ ቋቁቻን ለማጥፋት የሚያስፈልገው መዳኒት ምንድነው? በቤት ውስጥ ቀምሞ መጠቀም የሚቻል ውህድስ አለ?

የቋቁቻ ህክምናን በተመለከተ ሰፋ ያለ መረጃ በ YouTube ላይ አስቀምጫለው። ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን መመልከት ትችላላችሁ። መልካም ግዜ።