Get Mystery Box with random crypto!

መጥፎ የአፍ ጠረን ጠዋት ላይ ብዙ ሰው ከእንቅልፉ ሲነሳ መጥፎ የአፍ ጠረን ያጋጥመዋል። | Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ

መጥፎ የአፍ ጠረን

ጠዋት ላይ ብዙ ሰው ከእንቅልፉ ሲነሳ መጥፎ የአፍ ጠረን ያጋጥመዋል።

ከ 85 በመቶ በላይ የሚሆነው መጥፎ የአፍ ጠረን፣  በድድ በጥርስ እና በአፍ ዙሪያ ባለ ችግር ይጀምራል።

ከዛውጪ የሳይነስ ፣የቶንሲል፣ የሳምባ ፣ የጨጓራ እና  እንዲሁም፣ የጉበት እና የኩላሊት ድክመትን ጨምሮ በተለያዩ የውስጥ ደዌ ህመሞች ምክኒያት፣ አንድ ሰው ላይ መጥፎ የአፍ ጠረን ሊጀምር ይችላል።

መጥፎ የአፍ ጠረን በህክምናው( Halitosis) በመባል ይታወቃል።

ይህ ችግር በተለያየ እድሜ ክልል ሊጀምር ይችላል፣ እንዲሁም ደሞ ፣ እድሜ እየገፋ ሲሄድ፣ አንድ ሰው ላይ መጥፎ የአፍ ጠረን የሚከሰትበት እድል እየጨመረ ይሄዳል።

አንድ ሰው ፣በህክምና የተረጋገጠ ፣ምንም አይነት መጥፎ የአፍ ጠረን ሳይኖረው፣ ነገር ግን፣ መጥፎ የአፍ ጠረን እንዳለው በማሰብ ብቻ ወደህክምና የሚመጣ ከሆነ፣ የስነልቦና ችግር እንዳለ ያመላክታል።

ይህ አይነቱ ችግር ሲኖር በህክምናው (Delusional halitosis) በመባል ይታወቃል

በተፈጥሮ ወይም በተጓዳኝ በሽታ ምክኒያት፣ አንድ ሰው ላይ በህክምና የተረጋገጠ መጥፎ የአፍ ጠረን ሲኖር ደሞ፣ በህክምናው (Genuine halitosis) በመባል ይታወቃል

ምንም አይነት የጥርስ እና የድድ ችግር ሳይኖር፣ ወይም ደሞ ምንም አይነት ተጓዳኝ የውስጥ ችግር በሌለበት ሁኔታ፣ መጥፎ የአፍ ጠረን የሚፈጠር ከሆነ ተፈጥሮአዊ ሊሆንም ይችላል።

ይህ አይነቱ ችግር በህክምናው (Phyisiological halitosis) በመባል ይታወቃል፣ ይህ የሚመጣበት ሁለት አይነት ምክኒያት አለው

የመጀመሪያው፣ በአንድ ጤናማ ሰው አፍ ውስጥ፣ በተፈጥሮ የሚኖሩ ጥቃቅን ተህዋሶች ፣አንድ ሰው ከተመገበ በኋላ በምላስ እና በጥርስ መሀል የሚቀር ጥቃቅን የምግብ ትርፍራፊን ወደ መጥፎ ጠረን ወዳለው ተረፈ ምርት ሲቀይሩት ነው።

ሌላው ምክኒያት ደሞ ፣የምራቅ መጠን እና የምራቅ ዝውውር መቀነስ ነው፣ በአፍ ውስጥ በቂ የምራቅ መጠን የማይኖር ከሆነ ፣በአፍ ውስጥ ያሉ ጥቃቅን ተህዋስያን ፣ አፍ ውስጥ የቀረ ምግብን የበለጠ እንዲያብላሉ ስለሚያስችላቸው፣ መጥፎ የአፍ ጠረንን ይፈጥራሉ።

አንድ ሰው እርግጠኛ የሆነ መጥፎ የአፍጠረን እንዳለው ለማወቅ በሀኪም እገዛ ፣ወይም ደሞ በቤት ውስጥ የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም ማወቅ ይቻላል።

ለምሳሌ፣ መጥፎ የአፍ ጠረን አለብኝ የሚል ሰው፣ ለ 12 ሰአት ያህል ምንም አይነት ቅመማ ቅመም የበዛባቸውን ምግቦች ሳይመገብ እና ለ 6 ሰአት ያህል ጥርስ ሳይቦረሽ ፣ የእጁን ጀርባ አንድ ግዜ በመላስ በምራቁ ካረጠበ በኋላ፣ ምራቁ ሲደርቅ በቦታው ላይ ያለ መጥፎ ጠረን መኖሩን ማረጋገጥ ነው።

ሌላው ደሞ ፣ ንፁህ መጥረጊያን በመጠቀም፣ ምላስን በመፈግፈግ እና ፣ ወይም ደሞ፣ በጥርስ መሀል በሚገባ ገመድ ፣  ወይም dental flos በመጠቀም ፣የጥርስ መሀልን ፈግገፍጎ ገመዱ ላይ መጥፎ ጠረን መኖሩን አሽትቶ በማረጋገጥ ነው።

መጥፎ የአፍ ጠረንን የሚያስከትሉ በሽታዎችንን እና ህክምናቸውን በተመለከተ፣ እንዲሁም በቤት ውስጥ መደረግ ያለበትን ሁኔታ በተመለከተ፣ በ YouTube ቻናሌ ላይ ሰፋ ያለ መረጃ አስቀምጫለሁ።

የሚቀጥለውን ማስፈነወጠሪያ በመጫን መመልከት ትችላላችሁ፣ መልካም ግዜ።