2022-10-06 22:27:26
ለጋ የወጣትነት ጊዜውን ለኢስላም ሲል የሰዋ፤ እንደሻማ ቀልጦ የበራን ጀግና ልንዘክር የሻም ምድርን ረገጥን። የጀግንነት ገድሉን ከመተረካችን በፊት ወደ ኋላ እንመለስ። የሻምን ከተማ ለደቂዎች ለቀን ወደኪናናዋ ሚስር በሐሳብ እንክነፍ።
ዘመኑ እንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር በ1798 ዓመት ነው። የእስክንድርያ የባህር ዳርቻዎች በናፖሊዮ በሚመራ ጦር ተጨናንቋል። በቡድን ቡድን ተጭነው ወደ ግብፅ እየገሰገሱ ነው፡፡ ይህ ዘመቻ “ግብፅን በክርስትና የማቅናት ዘመቻ” የሚል መጠርያ ስያሜ ተሰጥቶታል።
ኑ ተከተሉኝ አረመኔያዊ ግፋቸውን እናውሳ! በግብፅ ሙስሊሞች ላይ ያደረሱትን ጥፋት እንዘክር! መሳጂዶችን ምን እንዳደጉ እንተርክ!
ናፖሊዮ በአውሮፓ ውስጥ አብያተ ክርስቲያናትን ማፍረሱን፣ የአላህ መልዕክተኛን እንደሚወድና በእስልምና በእጅጉ መማረኩን ለአል-አዝሃር መሻኢኾችና ታዋቂ ሰዎች በወረቀት ላይ አስፍሮ ሰደደ፡፡ ወደ ግብፅ ከመምጣቱ በፊት የሮማውን ሊቃነ ጳጳሳት ከሥልጣን እንዳወረደ ጠቅሶ ፃፈ። ነገር ግን ይህ የቆየ ብልሃት የግብፅን ህዝብ አልሸወደውም። “የመጀመሪያው የካይሮ አብዮት” ብልጭታ በፈረንሳዮች ላይ ተቀጣጠለ። የባህል እና የሥልጣኔ ተሟጋቾች ነን የሚሉት ፈረንሳዮች ማንነታቸው ተጋለጠ። በልባቸው ውስጥ ያጨቁትን የመስቀለኝነት መንፈስ ከጦራቸው ጋር ሸክፈው አዝሃርን በመውረር የአላህን ቃል ቁርአንን በእግራቸው ረገጡ። “በሞቅታም ተራራ” ላይ መድፎችን አዘጋጁ። የግብፅን ሰፈሮች አፈረሱ። “ቡላቅ” የተባለውን መንደር ወደ ፍርስራሽነት ቀየሩ። የአላህ ቤት መሳጂዶች ወደሙ፡፡ በአንድ ቀን ውስጥ የፈረንሳይ የመስቀል ጦር ሁለት ሺህ የአል-አዝሃር ምሁራንና መሻኢኾችን ገደለ። ዱዓቶችን አረደ። ሙስሊሞች ከቀድሞዎቹ የተለየ ያልሆነ የመስቀል ጦርነት እየገጠማቸው መሆኑን ተገነዘቡ፡፡ በዚህ ጊዜ የአል-አዝሃር ደረሶች በአላህ መንገድ ለመፋለም ተነሱ።
ግብፃዊው የታሪክ ምሁር ፀሐፊ አል-ጀበርቲ “عجائب الآثار في التراجم والأخبار” በተሰኘው መጽሐፉ ላይ የመስቀል ጦር ትብብር እንዴት እንደነበረ ይናገራል። ከዳተኛው ሙ#ናፊ#ቅ "ያዕቁብ ሐና" የአገሬው ሰዎችን አስጨፈጨፈ። ጠንካራ ሙስሊሞች ላይ እየጠቆመ ወደ ቤታቸው ዘልቀው በመግባት ለፈረንሳዮች እየጠቆመ ሙስሊም ወንድሞቹን አስገደለ።
ናፖሊዮን የግብፅን አመፅ መቅበሩን ሲያረጋግጥ መሪነቱን ለሌላ የጦር ወንጀለኛ (ክሊፕተር) አስረክቦ የመስቀል ተልዕኮው መጠናቀቁን ለማበሰር ወደ ፈረንሳይ ተመለሰ።
ይህ የመስቀላዊያን ጦር መሪ ሥነ ምግባር የጎደለው የሙስሊሞች ጥላቻ የተጠናወተው ነበርና የስልጣን ልጓሙን እንደተቆጣጠረ ከውድመት የተረፉትን መሳጂዶች የመስቀል ወታደሮችን ለማዝናናት ወደ ጭፈራ ቤትነት ቀየራቸው። ሙስሊም ልጃገረዶችን በአባቶቻቸው ፊት መስጂዱ ውስጥ ደፈሯቸው። ሕፃናትን በእናቶቻቸው ፊት ገደሉ። ከተማዋ ሰሚ ባጣ የዋይታና የኡኡታ ጩኸት ተሞላች። እስልምና ግብፅ ውስጥ አከተመ ተባለ . . .
ሙጃሂዶች በመላ ግብፅ “የላኢላሀ ኢለላህን" ሰንደቅ ዓላማ በማንሳት ከሁሉም አቅጣጫ ተነሱ። በመስቀል ጦር ላይ ጥቃትን ሰነዘሩ። ከመካ እና ከመዲና አጋዥ ኃይሎች መጡ። የሂጃዝ ሙጃሂዶች ለሙስሊም ወንድሞቻቸው ድጋፍ ለመስጠት ወደ ግብፅ የባህር ዳርቻ በመርከብ ተጭነው ተመሙ። በሺዎች የሚቆጠሩ የቱርክ ተዋጊዎች በድብቅ ሰርገው ገቡ። ኦቶማን ኢምፓየር (በደውለተል ዑስማኒያ) መሪ ሰሊም በታወጀው ጂሃድ ለመካፈል ከየአቅጣጫው ሙስሊሞች ወደ ካይሮ ገሰገሱ። አል-አዝሃርም ወደ ካምፕነት ተቀየረ።
የፈረንሣይ መስቀለኞች መስጂዶችን በፈረሶቻቸው እየረጋገጡ ሲያረክሱ የተመለከተው የዛሬው ባለታሪካችን የሀያ ሁለት ዓመቱ ወጣት፣ የኩርዱ ጀግና ነፍሱን መስዋእት የሚያደርግ ቢሆን እንኳ እነዚህ ነፍሰ በላ የመስቀል ጦረኞችን ለማዋረድ ብሎም ለመበቀል ስኬታማ የሆነ ኦፕሬሽንን ለማከናወን አሰበ። ሱለይማን አል-ሀላቢ ይሰኛል። ብቻውን ወደ ፈረንሣይ ካምፕ ዘልቆ በመግባት የጦር አዛዡን ለማጥቃት ወሰነ፡፡ ይህንን ተግባር ለማከናወን እቅድ ነደፈ። አሳቻ ሰዓትም ይጠባበቅ ጀመር። ወቅቱ ደረሰ በመስቀል ጦር ወራሪ ኃይሎች ላይ የተሳካ እርምጃን ወሰደ። የመስቀለኞችን ጦር መሪ በመግደል ፈረንሳዮችን አስደነገጠ። ሙስሊሞችን ከጥቃት ታደገ። ተማረከ! አዎ ተማረከ! እጃቸው ላይ ወደቀ። ግና ሱለይማን አል-ሀላቢን ምን እንዳደረጉት ጆሯችሁን ቀስራችሁ አድምጡኝ ትማሩበት ዘንድም ቀልባችሁ ከፍታችሁ ስሙኝ።
እጁን አጥንቱ እስኪታይ ድረስ በእሳት አቃጠሉት። ከሱ ጋር ተባብረዋል ያሏቸውን ሶስት በፍልስጤም “ጋዛ” ነዋሪ የሆኑ ልጆችን አይኑ እያየ ፊትለፊቱ አቃጠሏቸው፡፡ የዘመናዊነት እና የሥልጣኔ ተሟጋቾች ሱለይማን አል-ሀላቢን ሹላማ ብረት አግለው በጀርባው በኩል እያስገቡ አንጀቱን ቀጥሎም ኩላሊቱን እየጎለጎሉ አወጡት። ሹሉን ብረት በመቀመጫው በኩል እየሰቀሰቁ አሰቃዩት። የብልቱን ፍሬ ቆርጠው ገደሉት። አዎ ገድለው ለብዙ ቀናት ዛፍ ላይ አንጠለጠሉት በወፍና አሞራዎች እንዲበላ አደረጉ፡፡
በዚህም አልረኩም የራስ ቅሉን ወስደው ፓሪስ “musee de ihomme” በሚገኘው ሙዚየም ውስጥ አስቀመጡት ከበድኑ ስርም በፈረንሳይኛ "criminel" በሚል ፅሑፍን አሰፈሩ "ወንጀለኛ" እንደማለት ነው። የዚህ ሙጃሂድ የራስ ቅል በሙዝየማቸው ውስጥ እስከ አሁን ድረስ ይገኛል። ፈረንሳዮች እንደሚሉት ወንጀለኛ አልነበረም። እሱ ለኢስላም ሲሉ ካበሩ ምርጥ የኢስላም ወጣት ጀግኖች መካከል አንዱ ነበር። ወጣትነቱን እንደ አበባ የፈካ እድሜውን በአላህ መንገድ የሰዋ ድንቅ ሰው፡፡ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የአላህን ቃል እየቀደዱ የፈጸሙትን ግፍ በመበቀል ገሎ በክብር የሞተ። ለበደላቸው እና ለጭካኔያቸው ተስማሚ የሆነ የበቀል እርምጃ የወሰደ ወጣት።
አላህ ይቀበለው
═════════════════
ምንጭ
عجائب الآثار في التراجم والأخبار
@sebil_tube
@sebil_tube
═════════════════
205 viewsSadelvat , 19:27