Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2016 ዓ.ም ለድኅረ- ምረቃ ትምህርት አመልካቾች አዲስ አበባ ዩኒቨር | AAU, School of Commerce

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2016 ዓ.ም ለድኅረ- ምረቃ ትምህርት አመልካቾች

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2016 ዓ.ም ለድህረ ምረቃ ትምህርት በቀን መርሃ ግብር ለሁለተኛ እና ለሶስተኛ ዲግሪ እንዲሁም በማታ እና በርቀት መርሃ ግብር ለሁለተኛ ዲግሪ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ ስለዚህም በዩኒቨርስቲዉ ድረ-ገጽ (http://aau.edu.et) ላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት ማመልከት እንደምትችሉ ያሳስባል፡፡

የአ.አ.ዩ የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (GAT) የማመልከቻና መፈተኛ ቀናት ከግንቦት 15 እስከ ነሐሴ 06 ቀን 2015 ዓ.ም ሲሆን፤

የአ.አ.ዩ የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና ላለፉ በ(https://portal.aau.edu.et) ላይ የማመልከቻና የትምሕርት ማስረጃዎችን የማስገቢያ ቀናት ከግንቦት 18 እስከ ነሐሴ 10 2015 ዓ.ም፤

የትምሕርት ማስረጃዎችን በማስገባት የማመልከቻ ቦታ ሬጅስትራር ቢሮ ቁጥር 203 መሆኑን ያሳዉቃል፡፡