Get Mystery Box with random crypto!

ጳጉሜ 05 ቀን 2015 ዓ.ም   ለአዲስ አበባ  ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች በሙሉ   የአዲስ አበባ | School of Commerce, AAU

ጳጉሜ 05 ቀን 2015 ዓ.ም
 
ለአዲስ አበባ  ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች በሙሉ
 
የአዲስ አበባ  ዩኒቨርሲቲ እንኳን ለ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ እያለ ከትምህርት ሚኒስቴር በተላለፈ ትእዛዝ መሰረት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጊቢዎች በሙሉ ከመስከረም 28 ቀን 2015 ዓ.ም  እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም  ለአስራ ሁለተኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና አገልግሎት ስለሚዉሉ በአካዳሚክ ካላንደራችን ላይ ለዉጥ አድርገናል፤ በዚህም መሰረት
 
1ኛ፥ ሁለተኛ አመትና ከዚያ በላይ የቅድመ  ምረቃ  ተማሪዎች ምዝገባ ጥቅምት 22 ቀን እና ጥቅምት 23 ቀን  2015 ዓ.ም  
2ኛ፥ አዲስና ነባር የድህረምረቃ  ተማሪዎች ምዝገባ  ጥቅምት 21 ቀን 2015 ዓ.ም
3ኛ፥ ትምህርት የሚጀመረዉ ሐሙስ ጥቅምት 24  ቀን 2015 ዓ.ም መሆኑን እንገልጻለን፡፡
4ኛ፥ በ2014 ዓ.ም የገባችሁ የአንደኛ አመት ተማሪዎች በአስራ ሁለተኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና ምክንያት የሁለተኛ ሰሚስተር ትምህርት ተቋርጦ መስከረም 21 ቀን 2015 ዓ.ም ከዩኒቨርስቲ ጊቢዎች ትወጡና ጥቅምት 19 ቀን 2015 ዓ.ም  ተመልሳችሁ ጥቅምት 21 ቀን  2015 ዓ.ም ትምህርት ይጀመራል።
 
ማሳሰቢያ
1ኛ፥ ከላይ ከተገለጹት ቀናት ዉጭ ወደ ጊቢ የሚመጡ ተማሪዎችን ዩኒቨርስቲዉ የማያስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባልን::
2ኛ፥ ከመስከረም 28 ቀን 2015 ዓ.ም  እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም በዩኒቨርስቲ ጊቢዎች የተገኘ ማንኛውም ተማሪ የዲስፕሊን ቅጣት የሚወሰድበት መሆኑን ከወዲሁ እናሳዉቃለን::
 
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራር