Get Mystery Box with random crypto!

ይድረስ ግጠምልኝ ላልሽው ለደንዳና ልብሽ ፍቅር ለማይገባው ሳነባ የጻፍኩት መልክ | ድብቅ ግጥሞች-𝕰𝖙𝖎𝖊𝖑

ይድረስ
ግጠምልኝ ላልሽው

ለደንዳና ልብሽ ፍቅር ለማይገባው
ሳነባ የጻፍኩት መልክቴ ይድረሰው
ካሰኘሽ....
ዜማ አንቺ ስሪለት እኔ ግጥም ጻፍኩኝ
እንዳሻሽ አንብቢው ለኔ ግድ አይሰጠኝ

ልጆችን ሰብስበሽ
አንድ ሰው ነበረ
በፍቅሬ የሰከረ
ሚዛኑን ሳተና
ወድቆ ተሰበረ
ተረቴን መልሱ
አፌንም አብሱ
ብለሽ ቀልደሻል
የመኖሬ ምክንያት የምለውን ፍቅር
አቅለሽ አይተሻል

የኔ ጥልቅ ስሜት
አፈቀርኩሽ ማለት
ላንቺ ቢሆን ተረት
ይብላኝልሽ ላንቺ
መፈቀር ላልገባሽ
ማፍቀርስ ፀጋ ነው
ሰፊው ያልታደለው
ይድረስ ይሄ ግጥም
ግጠምልኝ ላልሽው

እኔን ያብቃኝ እንጂ
ባል ኖሮሽ ለማየት
እጄ አይሰስትም
ብዕሬም አይነጥፍም
አንቺ ያፈቀርሽ ለ'ት።

ተጻፈ በአብዱ (የእሙዬ ልጅ)