Get Mystery Box with random crypto!

++ ሥነጽሑፍ - ግጥም !! ( ለደስታችን_ዜና_ለልደትሽ_ብሥራት ) #ለደስታችን_ዜና_ለልደትሽ_ | ቤተ ቅዱስ ሚካኤል

++ ሥነጽሑፍ - ግጥም !!

( ለደስታችን_ዜና_ለልደትሽ_ብሥራት )

#ለደስታችን_ዜና_ለልደትሽ_ብሥራት
#ምን_ስጦታ_እናምጣ_ለፈጣሪ_እናት፤
በመኑ ድንግል ሆይ በማን እንመስልሽ
ቃላት ቢረቃቸው አበው ወዳጆችሽ
በአርምሞ ሆነው እንዳመሰገኑ የልጅሽን ስራ
ከትውልዱ የሆንን በልደትሽ ደስታ እኛም ስንጠራ።
ዝም እንበል እንጂ ክብርሽ ቢረቅብን
ላንቺ ያልነው ሁሉ ስጦታ ቀሎብን
እንውደድሽ እንጂ እናድንቅሽ እንጂ በዕንባችን ዘለላ
ለልደት ስጦታ አንቺን የሚመጥን ምንም የለን ሌላ!
#ለደስታችን_ዜና_ለልደትሽ_ብሥራት
#ምን_ሻማ_እናብራልሽ_የብርሃን_እናት፤
ጨረቃችን ማርያም ተስፋችን እኮነሽ
በጨለማ ሳለን ጸሐይን የወለድሽ፤
የጸሐይ ማደርያው በእውነት ጸሐይ ነሽ
ከፍጥረታት ሁሉ መተኪያ የሌለሽ፤
ስለ ልዩ ፍቅርሽ ስለእናትነትሽ ያውም በልደትሽ
ሻማ ብናበራ የብርሃን እናት ከቶም ባይመጥንሽ
ታውቂናለሽና አቅም እንደሌለን አሰናብቺን ባርከሽ
በልደት ስጦታሽ በኛ ተደስተሽ #ለደስታችን_ዜና_ለልደትሽ_ብሥራት #ምን_ቅኔን_እንቀኝ_ለመላእክት_እህት
#ያልታደለ_እኮነው_አንቺን_ያላወቀ
#በሥጋ_እየኖረ_በነፍስ_የደቀቀ፤
አንቺን ለማመስገን ያልታደለስ ወየው
ልቡናው ታውሮ ልደትሽ ያልታየው፤
በቅዱስ ጋብቻ ቢሆንም ልደትሽ
ሰማያዊ ጸጋን አድሎሻል ልጅሽ፤
እንደምድር ልደት የሚያቃልሉሽን
አትነፍጊያቸውም ድንግል ሆይ ምልጃሽን፤
ባያውቁሽ ነው እንጂ እንዲህ ሚያቃልሉሽ
አንቺስ ከመላእክት ሁሉ ትበልጫለሽ
የመላእክት እህት ዛሬ የተወለድሽ
ምን ቃል አለንና ቅኔ እንዝረፍልሽ፤ #ለደስታችን_ዜና_ለልደትሽ_ብሥራት
#ምን_ሻማ_እናብራልሽ_የብርሃን_እናት፤
ያንቺ ልደት ማርያም ለኛም ልደታችን
የተሸነፈበት ሰይጣን ጠላታችን
ልደትሽ ብሥራት ነው ለክርስቶስ ልደት
እግዚአብሔር የሚያውቀው እረቂቅ ነው በእውነት።

አብርሃም በላይ

ከእለታት አንድ ቀን
https://t.me/halhjab2345