Get Mystery Box with random crypto!

የትኛውን መውሊድ? እንደሚታወቀው በኢስላም የታዘዙት ሁለት አመታዊ በኣላት፣ ኢድ አል-ፊጥር እና ኢ | SadatKemal Abu Meryem

የትኛውን መውሊድ?
እንደሚታወቀው በኢስላም የታዘዙት ሁለት አመታዊ በኣላት፣ ኢድ አል-ፊጥር እና ኢድ አል-አድሃ ናቸው፡፡ ኢድ አል-ፊጥር አንድ ቀን ብቻ ሲሆን፣ ኢድ አል አድሃ ደግሞ 4 የበኣል ቀናቶች ናቸው፡፡ ታድያ በሀገራችን ተጨባጭ አላህ 4 ቀን እንዲከበር ያዘዘውን አንድ ቀን ብቻ እያከበርን ያልታዘዝነውን መውሊድ ግን ከአንድ ቀን በላይ በተለያዩ ሰዎች ስም ሲከበር ይታያል፡፡
ለምሳሌ ሀገራችን ላይ በተለያየ ቀናት ከሚከበሩ የመውሊድ አይነቶች ውስጥ
1) የነብዩ መውሊድ፣
2) የአሊ ጎንደር መውሊድ፣
3) የአባድር መውሊድ፣
4) የዳንግላው መውሊድ፣
5) የአብሬት መውሊድ፣
6) የቃጥባሬ መውሊድ፣
7) የአልከሶ መውሊድ፣
8) እና ስፍር ቁጥር የሌላቸው መውሊዶች……
ለምን ይሆን በኢስላም የታዘዝነውን ትተን ያልታዘዝነውን የምንሰራው?
እውነት ይህ ነው የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ውዴታ?
በፍፁም፡፡
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “አደራችሁን አዳዲስ ነገሮችን (በዲን ላይ ከመጨመር) ተጠንቀቁ፡፡ ሁሉም አዲስ ነገር ጥመት ነው፡፡” ብለው ሲያበቁ
አሁንም ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “የእኛ ትእዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ ሰው ስራው ተመላሽ ነው (ተቀባይነት አያገኝም፣ ውድቅ ነው)” ብለው ሳለ

ዛሬ እሳቸው ያዘዙትን ትተው ያላዘዙትን የሳቸውንም ይሁን ሌሎች ጥሩ ሰዎች ናቸው ብለው የሚገምቷቸውን የአሊ ጎንደር መውሊድ፣ የአባድር መውሊድ፣ የዳንግላው መውሊድ፣ የአብሬት መውሊድ፣ የቃጥባሬ መውሊድ፣ የአልከሶ መውሊድ እና የመሳሰሉትን እያሉ በውዱ ሃይማኖታችን ላይ ቅጥፈትን ይቀጥፋሉ፣ የክህደት ንግግሮችን መውሊዶች ላይ ይናገራሉ፣ ይጨፍራሉ፣ ይህን አደንዛዥ ቅጠል ያላምጣሉ፡፡

ሱብሃነላህ ይህ በፍፁም ነብዩን መውደድ አይሆንም፡፡ ነብዩን ከማንም በላይ የሚወዱት ሰሃባዎች የነብዩን ፈለግ ህይወታቸው ላይ ተላበሱ እንጂ እንዲህ ልደት እናክብር አላሉም፡፡

ለሙስሊሙ ከታሰብ መውሊድ ብሎ በሺርክ፣ በቢድኣ፣ በጭፈራ እና አደንዛዥ ቅጠል ጫትን መቃም እና ማስቃም ሳይሆን፣ መስጂዶችን ማስፋፋት፣ መድረሳዎች መገንባት፣ እውነተኛውን የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አስተምህሮት ማሰራጨት፣ ከሱስ የፀዳ ሃይማኖቱን እና ሀገሩን የሚጠቅም ትውልድ ማነፅ ይጠበቅብናል፡፡

ይሄ እውነተኛ የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ውዴታ የሚገለፀበት ተግባር ነው፡፡
አላህ ሱናቸውን ከሚከተሉት ከቢድኣ ከሚርቁት ትውልዶች ያድርገን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts