Get Mystery Box with random crypto!

የክርስትና ጦም በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 28፥50 እሺ | አንዳንዴ

የክርስትና ጦም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

28፥50 እሺ ባይሉህም የሚከተሉት ዝንባሌዎቻቸውን ብቻ መኾኑን ዕወቅ! ከአላህ የኾነ መመሪያ ሳይኖረው ዝንባሌውን ከተከተለ ሰው ይበልጥ የጠመመ አንድም የለም፡፡ فَإِن لَّمْ يَسْتَجِيبُوا لَكَ فَاعْلَمْ أَنَّمَا يَتَّبِعُونَ أَهْوَاءَهُمْ ۚ وَمَنْ أَضَلُّ مِمَّنِ اتَّبَعَ هَوَاهُ بِغَيْرِ هُدًى مِّنَ اللَّهِ

አምላካችን አሏህ ከሶላቱ መግሪብ ጀምሮ እስከ ሶላቱል ፈጅር ድረስ ማንኛውም ጀላል ምግብ እንድንበላ እና ሐላል መጠጥ እንድንጠጣ ፈቅዶልናል፦
2፥187 ከጎህ የኾነው ነጩ ክርም ከጥቁሩ ክር ለእናንተ እስከሚገልጽላችሁ ድረስ ብሉ፥ ጠጡም፡፡ ከዚያም ጦምን እስከ ሌሊቱ ድረስ ሙሉ፡፡ وَكُلُوا وَاشْرَبُوا حَتَّىٰ يَتَبَيَّنَ لَكُمُ الْخَيْطُ الْأَبْيَضُ مِنَ الْخَيْطِ الْأَسْوَدِ مِنَ الْفَجْرِ ۖ ثُمَّ أَتِمُّوا الصِّيَامَ إِلَى اللَّيْلِ ۚ

ከዚያ ከሶላቱል ፈጅር ስለ ሶላቱል መግሪብ ድረስ ከምንም ዓይነት ምግብ እንዳንበላ እና ከምንም ዓይነት መጠጥ እንዳንጠጣ አዞናል። "ጦም" የሚለው የግዕዙ ቃል "ጦመ" ማለትም "ተወ" "ታቀበ" "ታረመ" ከሚል የግዕዝ ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን ከምግብ እና ከመጠጥ "መተው" "መታቀብ" "መታረም" ማለት ነው፥ ጦም ማለት ከምግብ እና ከመጠጥ መተው፣ መታቀብ፣ መታረም እንጂ ከሥጋ እና ከሥጋ ተዋእፆ ከሆኑት እንቁላል፣ ወተት፣ አይብ እየተቆጠቡ ነገር ግን በእጅ አዙር የስጋ፣ የእንቁላል፣ የወተት ምትክ የሆኑትን ባቄላ፣ አተር፣ በቆሎ፣ ገብስ የመሳሰሉት በሳይክል ተዙሮ የማያልቀውን ቡፌ መብላት አይደለም። ይህ ሠው ሠራሽ ጦም እንጂ ባይብል ላይ የለም፦
ዳንኤል 10፥3 ማለፊያ እንጀራም አልበላሁም፥ ሥጋና ጠጅም በአፌ አልገባም፥ ሦስቱም ሳምንት እስኪፈጸም ድረስ ዘይት አልተቀባሁም።

ዳንኤል ጦም ሲጦም እንጀራ እና ሥጋ ባለመብላት እና ጠጅ ባለመጠጣት ከሁሉ ነገር ይታቀብ ነበር እንጂ እንደ ኦርቶዶክስ ጦም ከሥጋ ተቆጥቦ እንጀራ አይበላም ነበር፥ ኦርቶዶክሳውያን በጦም ወቅት ቅዳሴ እንዳለቀ በተለይ ዲያቆናት፣ ቀሳውስት፣ ደብተራዎች ደጀ ሰላም ውስጥ ገብተው ሥጋ የሚተኩ ምግቦች ከርሳቸው እስኪወጠር ሲያግበሰብሱ እና ጠላ፣ ጠጅ፣ ፊልተር እንዲሁ ሀብታም ለተዝካር ያመጣውን ውስኪ እና አረቄ ሲጋቱ እና ሲሰክሩ ማየት የአደባባይ ጉድ ነው። ከኦርቶዶክስ ጦም በተቃራኒው ሙሴ ሲጦም እንጀራ ባለመብላት እና ውኃም ባለመጠጣት ነበር፥ ኢየሱስ ሲጦም ምንም አልበላም ነበር፦
ዘጸአት 34፥28 በዚያም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ከከያህዌህ ጋር ነበረ፤ እንጀራም አልበላም፥ ውኃም አልጠጣም።
ማቴዎስ 4፥2 አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ ተራበ።
ሉቃስ 4፥2 አርባ ቀን ከዲያብሎስ ተፈተነ። በነዚያም ቀኖች ምንም አልበላም፥ ከተጨረሱም በኋላ ተራበ።

ስለዚህ ከሥጋ እና ከሥጋ ተዋእፆ ከሆኑት እንቁላል፣ ወተት፣ አይብ እየተቆጠቡ ነገር ግን በእጅ አዙር የስጋ፣ የእንቁላል፣ የወተት ምትክ የሆኑትን ባቄላ፣ አተር፣ በቆሎ፣ ገብስ መብላት ሰው ሠራሽ ጦም ነው፥ ይህንን ሰው ሠራሽ ጦም ይዛችሁ የኢሥላምን ጦም ለመተቸት ሞራሉ ሆነ ዐቅሙ የላችሁም።
"ሁዳድ" ማለት "ሰፊ" ማለት ሲሆን "ሁዳዴ"lent" እራሱ 40 ቀናት የነበረ ሲሆን ቅዳሜ እና እሑድ ተተስቶ 15 ቀናት በ 40 ቀናት ሲጨመር 8 ሳምንት ወይም 55 ቀናት በማድረግ የሚጦሙት "ሶውሙል ከቢር" صَوْم ٱلْكَبِير ማለትም "ዐብይ ጦም" ይባላል። ይህንን ሁዳዴ "ጡሙ" ብሎ የደነገገው በ 339 ድኅረ-ልደት አትናቴዎስ ሲሆን በውጪው ዓለም ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክ እና ጥቂት የፕሮቴስታንት አንጃዎች ይጦሙታል፥ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ያሉት አጥማዋት ማለትም ፅጌ፣ ገና፣ ነነዌ፣ ሁዳዴ፣ ሰኔ፣ ፍልሰታ የቤተክርስቲያን መሪዎች ቀስ በቀስ እና በጊዜ ሂደት የደነገጓቸው ሰው ሠራሽ ሕግ እንጂ የመለኮት ትእዛዞች አይደሉም።
የነነዌ ጦምም ለነነዌ ሰዎች ለሥስት ቀን የተሰጠ እንጂ አማኞች እንዲጦሙ የታዘዘበት አንቀጽ በባይብል ሽታውን አናገኝም።
አምላካችን አሏህ ካፈጠርን በኃላ ከሐላል ጥንዳችን ጋር ተራክቦ ማድረግን ሐላል አድርጓልናል፦
2፥187 በጾም ሌሊት ወደ ሴቶቻችሁ መድረስ ለእናንተ ተፈቀደላችሁ፡፡ أُحِلَّ لَكُمْ لَيْلَةَ الصِّيَامِ الرَّفَثُ إِلَىٰ نِسَائِكُمْ

በባይብል ግን አንድ ሰው ከትዳር አጋሩ ጋር በጦም ጊዜ ተራክቦ ማድረግ "ክልክል ነው" የሚል ፍንጭ ይቅርና ሽታው የለም።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ስለ ጦም ያለው መመሪያ ፍትሐ ነገሥት ላይ ይገኛል፥ ፍትሐ ነገሥት በ1240 ድኅረ-ልደት በግብጽ አገር ውስጥ አቡል ፋዳዒል ኢብኑል አሣል ጠጅ እየጠጣ በዐረቢኛ የጻፈው ድርሰት ነው። ይህ መጽሐፍ ወደ ግዕዝ የተተረጎመው በ 1450 ድኅረ-ልደት በአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ሲሆን በቤተ ክህነት እና በቤተ መንግሥት ሕጉ መዋል የጀመረው በ 1455 ድኅረ-ልደት በበአጼ ሠርጸ ድንግል ዘመን ነው። ይህንን መመሪያ የጻፉት በግልጠተ መለኮት ሳይሆን ዝንባሌአቸውን በመከተል ነው፦
28፥50 እሺ ባይሉህም የሚከተሉት ዝንባሌዎቻቸውን ብቻ መኾኑን ዕወቅ! ከአላህ የኾነ መመሪያ ሳይኖረው ዝንባሌውን ከተከተለ ሰው ይበልጥ የጠመመ አንድም የለም፡፡ فَإِن لَّمْ يَسْتَجِيبُوا لَكَ فَاعْلَمْ أَنَّمَا يَتَّبِعُونَ أَهْوَاءَهُمْ ۚ وَمَنْ أَضَلُّ مِمَّنِ اتَّبَعَ هَوَاهُ بِغَيْرِ هُدًى مِّنَ اللَّهِ

አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም