Get Mystery Box with random crypto!

ቀልባችንን አልተፈታተኑም፣ ይልቁኑ ባየናቸው ቁጥር መሰተር እንዳለብን ያስታውሱናል። የተዋረዱ ሆነው | Reyan Records

ቀልባችንን አልተፈታተኑም፣ ይልቁኑ ባየናቸው ቁጥር መሰተር እንዳለብን ያስታውሱናል።
የተዋረዱ ሆነው አልተመለከትናቸውም፣ ግና ምልክት ሆነው ሲያስከብሩን አየተናቸዋል።
በምላሳቸው አልተወጋንም፣ በክብር አንደበታችን ዝቅ እንዲልላቸው ግን ሆነናል።
ሀዘን ብሶታቸውን፣ ህመም መከራቸውን አላወቅንባቸውም፣ እነሱ ግን ዘንበል ስንል አብሽር ብለውናል።
በመንገዳቸው አሜኬላ በዝቶ አላገዝናቸውም፣ እነሱ ግን ተስፋ ስንቆርጥ የአላህን ቃል አስታውሰውናል።
ክብር አልባዎች በበዙበት ክብራቸውን ለመጠበቅ ሲጥሩ በአሽሙር በነገር ሸነቆጥናቸው፣ እነሱ ግን ለክብራቸው ከመታገል በቀር ሲያነውሩን አልገጠመንም።
ውበትን የማክበርን ጥበብ ከእነሱ ብንማር እንጂ አናውቅም!
በጥቃቅን እና አነስተኛ አመለካከት የተደራጁ አላዋቂዎች ስለተሳለቁባቸው ክብራቸውን ዝቅ አናደርግም።
እነሱን የአላህ ህግ እንጂ አመለካከት ወክሎ የሚዳኛቸው አይደሉም።
አስተሳሰቦች ሊያራቁታቸው ይጥሩ ይሆናል ግና በአላህ ላይ ያላቸው እርግጠኝነት ይሸፍናቸዋል።
ክብራቸውን በመጠበቅ ለክብር አልባ ትንኮሳዎች ያልተመቹትን እናከብራቸዋለን። እንወዳቸዋለን።
(አብዱልሀኪም ሰፋ)
:
@Venuee13
@Venuee13