Get Mystery Box with random crypto!

አንዳንዴ ሰወችን ለማስደሰት ስንል አላህን የሚያስከፋ ተግባር እንፈፅማለን። የሚገርመው ግን አላህን | Reyan Records

አንዳንዴ ሰወችን ለማስደሰት ስንል አላህን የሚያስከፋ ተግባር እንፈፅማለን። የሚገርመው ግን አላህን ያስከፋንለት አካል ለእሱ ስንል የጣስነውን የጌታችንን ድንበር አይቶ ለእሱ ያለንን ቦታ ያቅልናል ብለን ብናስብም የሚሆነው ግን ሁሌም በተቃራኒው ነው። ድንበሩን ከጣስነው ጌታ በላይ ያ ደካማ ሰው የሰጠነውን ቦታ ሳይሆን ደካማነታችንን አይቶ ይንቀናል። ይህን ግዜ አላህን አስከፍተን በጭራሽ የፍጡርን ፍቅር እንደማናገኝ ይገባናል። የሚገርመው ለፍጡር ፍቅር ብለን የገፋነው ጌታ ፍፁም በሆነ ፍቅር ድጋሜ ልባችን ወደ እሱ በተውበት እንዲመለስ እድል ሰጥቶ በፍቅሩ እና በእዝነቱ በፍጡር የተሰበረ ልባችንን ይጠግነዋል። ያኔ መቼም ቢሆን ፍጡርን ለማስደሰት ጌታችንን ማመፅ እንደሌለብን ይገባናል።

የሰውን ፍቅር ለማግኘት የጌታችንን ፍቅር መግፋት ያማል!። አላህ ይቅር ይበለን