Get Mystery Box with random crypto!

በማህበራዊ ገፅ ቅፆች 'ፆታ' የሚለው ምርጫ ላይ 'አለመመለስን እመርጣለሁ' የሚለውን ምርጫ ሳይ ዝ | Reyan Records

በማህበራዊ ገፅ ቅፆች "ፆታ" የሚለው ምርጫ ላይ "አለመመለስን እመርጣለሁ" የሚለውን ምርጫ ሳይ ዝግንን የሚለኝ ነገር አለ.... ዙሪያዬንና የምሰማውን ሳሰላው "ጌታዬ የጠላኸው ሁሉ እስከሚለመድበት ዘመን አታቆየኝ" እላለሁ። ታማኝነት መለያችን የነበረበት ዘመን ተገልብጦ መታመን ፋራነት ከሆነ ሰነባበተ። "አልሰግድም" የሚል አመፀኝነት እንደ ጀብድ የሚኮሩበት ሆነ። ልጃገረዶች "ሳያገቡ ወለዱ" የሚባል ዱብዳ እንደ ተራ አሉባልታ ቀለለ። ዝሙትም የህይወት መንገድ ሆኖ "አብረን ነን ግን አንጋባም" መባባል ተከበረ። ሀይማኖት እንደውሎ መጊያጊያጫ መቀያየሩ ጉድ ማስባሉ ቀረ። ግብረዶም እንኳን ለተግባር ለማሰብ እንኳን ፀያፍ የነበረበት ጊዜ እንኳን እኮ ሩቅ አልነበረም....ጌታዬ.... የደረስንበት ያስፈራል.... በየት/ት ገበታው፣ በየስራ ወጉ... "ስትወለጂም ሴት ነበርሽ?"... "ቀጣይ ሳምንት ወደ ወንድነት እቀየራለሁ...".... "ፆታዬን የቀየርኩበት ምክኒያት... ሳልቀይር በፊት.... ከቀየርኩ በኋላ".... የሚሉ በላኦችን እስከምንላመድበት ዘመን አታቆየን። "ልጄ የወንድ ወይስ የሴት ጓደኛ ይይዝብኝ ይሆን?" ለሚል ጭንቀት አትጨን.... ኢላሂ ስትታመፅ እያዩ አለመደንገጥም እኮ ያስፈራል.... እኛንም.... ከኛ የሚወጡና የምንጠየቅባቸውን ትውልዶችም ቅጣትህን ከረሳች ደንዳና ጠጣር ልብ ጠብቅልን።

መድ

@Yeruh_weg