Get Mystery Box with random crypto!

ኸሚስ 9 . (ረያን_አቡዲ) አሁን ተረዳሁኝ የፍቅር ትርጉሙን አካል ሚያመነምን የናፍቆት ህመሙ | Reyan Records

ኸሚስ 9
.
(ረያን_አቡዲ)

አሁን ተረዳሁኝ የፍቅር ትርጉሙን
አካል ሚያመነምን የናፍቆት ህመሙን
እሱን ያዩ ለታ ሚገረስስ ጥሙን፥

ትንሽ ስለሱ.......

የፍንጭቱ ነገር
የሚያደነጋግር
የግንባሩማ ኑር
ይገዳል ለመንገር
የፊቱማ ማማር
አስፈዝዞ ሚያስቀር፥

አንደበተ ርቱዕ አፈ ማር ዘነቡ
አዛኝ ቸር ለጋስ ገራገር ለአስሀቡ
የጀነት በር ከፋች ንጉስ ከነዘቡ፥

የሱን ውበት ሊገልፅ ያነሳ ሁሉ መድ
ቃላት እያጠረው ለማቆም ሲገደድ
ብሎ ያሳርጋል፥
ሙሀመድ ፍቅር ነው ፍቅርም ሙሀመድ።
━━━━✦✗✦━━━━━━━
   ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

አዘጋጅ፦ ግጥም እና ቅኔ

➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ
@Mejnun_Leyla_poem