Get Mystery Box with random crypto!

፡ አንዲት ላም ነበረች ብዙ የወለደች፣ ወተቷን አጥብታ መ | Reyan Records


አንዲት ላም ነበረች
ብዙ የወለደች፣
ወተቷን አጥብታ
መኖር ያለመደች፤

ምን ዋጋ አለው ታዲያ
ልጆች አመፁባት፣
ቀንዳቸው ሲበቅል
ጎኗ ላይ ሻጡባት፤
አቆሰሏት ከቶ እየደጋገሙ፣
ስቃይዋን በመናቅ ላንዳፍታ ሳይሰሙ፤

አይ ያቺ ወላድ
ፍሬዋ መከነ ፣
እንደክብሪት ስንጥር
ከሆዷ የወጡት ይጭሯት ነበረ…………!!!

Abu,Alazar Tewodros