Get Mystery Box with random crypto!

Dummy Variables ምንድን ነው? በጥናት ማረጋገጥ የፈለግናቸው ሃሳቦች (Dependent V | Research-ሪሰርች(ጁፒተር-Jupiter)

Dummy Variables ምንድን ነው?

በጥናት ማረጋገጥ የፈለግናቸው ሃሳቦች (Dependent Variable) ቀጥተኛ ልኬት ባላቸው ማለትም Ratio Scale Variables (#ለምሳሌ:- የገቢ መጠን፤ የምርት መጠን፤ ዋጋ፤ ወጪ፤ ቁመት፤ የሙቀት መጠን፤ ወዘተ) ብቻ ተጽኖ በሚያድርባቸው ወቅት አስረጂዎቹን (Explanatory Variables) በቀጥታ እራሳቸውን በመውሰድ ውጤቱን መግልጽ ይቻላል፡፡

በተቃራኒው በጥናት ማረጋገጥ የፈለግናቸው ሃሳቦች (Dependent Variable) በቁጥር በማይለኩ (Qualitative) እና የምርጫ ባህሪ (Nominal Scale) ባላቸው አስረጂዎች (Independent Variables) ተጽኖ ሊፈጠርበት ይችላል:: #ለምሳሌ:- ጾታ፤ ብሄር፤ ቀለም፤ ሃይማኖት፤ ዜግነት፤ የመኖሪያ አካባቢ ወይም ክልል፤ የሚደግፉት የፖለቲካ ፓርቲ፤ ወዘተ በሚገጥሙን ግዜ በጥናት ማረጋገጥ ለፈለግናቸው ሃሳቦች በአስረጂነት የምንወስዳቸውን (Explanatory Variables) Category በማድረግ መጠቀም ይገባል:: የዚህ አይነቶቹ አስረጂዎች Dummy Variables ይባላሉ፡፡ (Dummy variables do not have a natural scale of measurement)::

በኢኮኖሜትሪክስ ሞዴል ጥናት በምናጠናበት ወቅት መጠበቅ ያለበት አንድ ጠንካራ ህግ አለ! እሱም ከተዘረዘሩ አስረጂ (Explanatory Variables) መካከል የአንደኛውን ተጽኖ ለማረጋገጥ በፈለግንበት ወቅት የሌሎቹን ተጽኖዎችን ዜሮ አድርገን ነው የምንነሳው (Holding all other factors constant)፡፡ #ለምሳሌ፡- ሲጋራ ማጨስ በጤና ላይ ስላለው ጠንቅ ለማጥናት አስበን ከምንጠቀማቸው ማመላከቻ ምክንያቶች (Explanatory Variables) መካከል ስለ ጾታ ብቻ እንመልከት ብንል እና ሴት ነው ወይስ ወንድ በብዛት በማጨሱ ምክንያት የሚጎዳው? የሚለውን ለመመለስ ከፈለግን፣ ሲትረስ ፓሪበስ የሚሆነው ጉዳይ የአጫሹ እድሜ፤ የትምህርት ደረጃው፤ የትዳር ሁኔታው፤ የገቢ ሁኔታው፤ ወዘተ ናቸው፡፡ ምን ማለት ነው? በማጨስ ምክንያት ተጎጂው ሴት ወይስ ወንድ? የሚለውን እንጂ ሴት ወጣት፤ የተማረች ሴት፤ ያገባች ሴት፤ ሃብታም ሴት ወዘተ በማለት ላለማነጻጸር ሲባል ነው የሚያስፈልገው፡፡

#ለምሳሌ:- ወንድ ወይም ሴት፤ ሰራተኛ ወይም ስራ- አጥ፤ ክርስትያን ወይም ሙስሊም፤ ነጭ ወይም ጥቁር፤ ድሃ ወይም ሃብታም፤ የተማረ ወይም ያልተማረ፤ የሚያጨስ ወይም የማያጨስ፤ ወዘተ የሚሉ ምርጫዎች ላይ መውደቅ አስገዳጅ ሲሆን Dummy variables ስልትን መጠቀም ግዴታ ነው፡፡ አማራጩ የሚታወቅ ሲሆን ብቻ ሳይሆን ያለ ወይም የሌለ (Mutually Exclusive Categories) ብሎ ለመለየትም መጠቀም ይቻላል፡፡

#ምሳሌ1:- በሴቶች እና በወንዶች መካከል ያለውን የገቢ ልዩነት ለማጥናት ለሚፈልግ ሰው በመጀመሪያ ወንድን እና ሴትን ኮድ አርጎ ማስቀመጥ አለበት:: ለምሳሌ:- ወንድ = 0 ሴትን = 1 ማድረግ ይቻላል::

#ምሳሌ2:- በኢትዮጲያ ሁኔታ በብሄሮች መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ለማጥናት የፈለገ አጥኚ በመጀመሪያ ብሄሮቹን ኮድ አድርጎ ማስቀመጥ አለበት:: ለምሳሌ:- አርጎባ ብሄር= 0 ጉራጌ= 1 አድርጎ ማስቀመጥ ይገባል:: 0 እና 1 ብሎ መሰየም ግዴት አይደለም፤ አጥኚው በፈለገው መንገድ ኮድ ማድረግ ይችላል:: ለምሳሌ:- 1 እና 2 ብሎ መሰየም ይቻላል፡፡

#ለምሳሌ:- ለሙከራ እስቲ አንድ Equation እንፍርጠር
Y(ማጨስ) = β1D1(ሴት = 0 እና ወንደ = 1) + β2D2(አጭር= 0 እና ረጅም= 1) + β3D3(ሃብታም = 0 እና እና ድሃ = 1) +……..+u(error term)

በመጨረሻ ውጤት ሲተነተን ወንዶች ከሴቶች የማጨስ ሁኔታቸው ምን እንደሚመስል፤ አጫጭር ሰዎች ከረጃጅም ሰዎች የማጨስ ሁኔታቸው ምን እንደሚመስል እንዲሁም ሃብታም ከድሃ የማጨስ ሁኔታው ምን እንደሚመስል ገልጾ ለመተንተን ይቻላል ማለት ነው፡፡
WaseAlpha
GOOD NEWS
በማንኛውም የትምህርት መስክ በማስተርስና የመጀመሪያ ዲግሪ ተምረው፣ #የመመረቂያ_ፅሑፍ ለመስራት ልዩ ድጋፍና እገዛ ለሚፈልጉ ተመራቂ ተማሪዎች ሁሉ፥ ያሉበት ቦታ ሳይገድበን #ጥራት ያለው አገልግሎት #በተመጣጣኝ ክፍያና #በተፈለገው_ጊዜ የምንሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን።
Contact us @rese100arch
Phone
+251918533959
+251920256875